SL INS PR FR የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ

SL INS PR FR የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ 

ቁጥር ም/ስ/ስ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት-01/2013 

በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል

1 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች 
2 የተለያዩ የመብራት ዕቃዎችና የቢሮ ጥገና መገልገያዎች 
3 የሕትመት ዓይነቶች 
4 የተለያዩ የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች 
5 የተለያዩ መፅሐፍቶች 

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል በመሆኑም ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርት ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ 

  1.  በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውናየዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ
  2. . የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ 
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆኑን የምስክር ወረቀት
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ያላቸው
  5. ግብር የመክፍል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል 
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ከሚጫረቱበት 2% በባንክ በተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ
  7. . የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በሰንጠረዥ በየሎቱ የተዘረዘረው ብር በባንክ በተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ 
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መገናኛ አካባቢ የቀድሞ ለም ሆቴል በስተቀኝ ኮሜት ሕንጻ ቁጥር 2 የሚገኘው በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 8-03 ግዢና ፋይናንስ ቡድን አስተባባሪ ቢሮ በአካል ቀርበው መግዛት የሚችሉ መሆኑን 
  9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናውና ኮፒውን በማስያዝ በጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤት አዳራሽ 8ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 8-01ይከፈታል፡፡ 
  10. የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% /አስር በመቶ/ በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡ 
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ስልክ 0116674731 

በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት 

 __________________

Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 8፣2013

Deadline:መስከረም 25 ቀን 2013

__________________
© walia tender



Report Page