OT የይ/ዴንሣ ወረዳ ገጠር
Walia Tender
የደን ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ጐጃም ዞን የይ/ዴንሣ ወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት በአዴት ከተማ አስተዳደር የ01 እና የ02 ቀበሌ ልዩ ስሙ ጽራፂዮን ባታ አካባቢ እና ምንጭት አካባቢ የሚገኘውን ምድብ 01 ፣ ምድብ 02 ፣ ምድብ 03፣ ምድብ 04፣ የለማ የማህበረሰብ ደን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ፡፡
ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚገባቸው መመዘኛዎች፣
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የቲን/የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጎ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ የቀረበውን ደን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በተገለፀው ቦታ ድረስ በመሄድ ጨረታው ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 የስራ ተከታታይ ቀናት ማየት ይችላሉ፡፡
- የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ ጨረታውን ባወጣው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በመንግስት የስራ ሰዓት በመገኘት ለአንዱ የጨረታ ሰነድ ብር 300 ብር ከፍሎ መግዛት ይችላል፡፡
- የመጫረቻ ሰነዱ ከ25/01/2013 ዓ/ም እስከ 20/02/2013 ዓ/ም ከቀኑ 6፡30 ለ20 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የተሞላውን የዋጋ መሙያ ፣ቲን ፣ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና ሌሎች ማስረጃዎችን በታሸገ ፖስታ አሽጎ ማህተም በማድረግ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት አለበት፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት በ20/02/2013 ዓ/ም በ8፡00 ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በተዘጋበት እለት በ20/02/2013 ዓ/ም በ9፡00 ቢሮ ቁጥር 03 ፍላጐት ያለው ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ እለት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታውን ለመክፈት የሚገድበው/የሚከለከለው/ የለም፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የደን ዓይነት ለመግዛት የሞሉትን ዋጋ 10 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ በባንክ ክፍያ ማዘዣ/ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ለእያንዳንዱ የደን ምድብ ወይም በጥቅል መቅረብ ይኖርበታል ፡፡
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉት የእያንዳንዱ የደን ዓይነትና መጠን እና የሚገዙበትን ዋጋ ከስማቸውና ከአድራሻቸው ጋር በተናጠል በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የምዕ/ጐጃም ዞን የይ/ዴ/ወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ጽ/ቤት የማህበረሰብ ደን ጨረታ ተብሎ በጉልህ ከተፃፈበት በኋላ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር እስከ 20ኛው ቀን 11፡30 በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0583380370 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ማቅረብ አይችሉም፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከ05 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 05 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 10 በመቶ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በተናጠል/በድምር/ ዋጋ ነው፡፡
- ማንኛውንም ወጭ ተጫራች/ገዥዎች/ የሚሸፍን መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታውን ሂደት ለማዛባት የሚደረግ ህጋዊ ያልሆነ ማንኛውም የተጣራቾች ሂደት ካለ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
የይ/ዴንሣ ወረዳ ገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ጽ/ቤት
__________________
__________________
© walia tender