Md መአኤ6

Md መአኤ6

Walia Tender

ከሀገር ውስጥ አምራቾች መድኃኒት ለመግዛት

የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታው ቁጥር: NCB/PSA6/RDF-R/PH/03/20

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ

የመድሐኒት አቅርቦት ኤጀንሲ /መአኤ/

በጨረታው ለመካፈል የሀገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾችከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መሆንይኖርበታል፡፡

  1. ተጫራቾች በመስኩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ስራፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርእንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለበት።
  2. የጨረታው ተሳታፊዎች ከኢትዮጵያ የምግብየመድሐኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥርባለስልጣን የማምረቻ ፈቃድ ሰርተፊኬት ማቅረብይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይየተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን መረጃዎች ፎቶኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብአለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ የማይመለስብር 300 መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸው ዋናውንና ሁለትኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ስምናአድራሻ እንዲሁም አስፈላጊ መረጃዎች በመጻፍማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. የመጫረቻ ሰነዱ ከታች በተገለፀው አድራሻ በአዲስዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15ተከታታይ ቀናት ይሸጥና የመዝጊያው ሰዓትከቀኑ 800 ሰዓት ሲሆን የጨረታው መከፈቻበተመሳሳይ ቀን 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይምሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
  7. በጨረታ ሰነድ ላይ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በኋላየሚመጣ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  8. ተጫራቾች 500,000 ብር የጨረታ ማስከበሪያዋስትና ከኢንሹራንስ ተቋም ያልሆነ ወይምበምክንያት ያልተመሰረተ የባንክዋስትና(unconditional bank guarantee)ወይም በሲፒኦ(CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. የመገምገሚያ መስፈርቱም በዝርዝር በጨረታ ሰነዱላይ መመልከት ይቻላል፡፡
  10. ኤጀንሲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውንበከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው፡፡
  11. በዚህ ያልተካተቱ ሕጎች በሀገሪቱ የግዥ መመሪያእና የጨረታ ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መስፈርትመሰረት ተገዥ ይሆናሉ፡፡

አድራሻ፡- የመድሐኒት አቅርቦት ኤጀንሲ/መአኤ/ የጨረታአስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከጳውሎስ ሆስፒታል ፊት ለፊትአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 የፖስታ ሣጥን ቁጥር21904 የስልከ ቁጥር +251 118 27 65 31 ፋክስ+251 11 275 25 55 አዲስ አበባ፡፡

የመጫረቻ ሰነዱን ከላይ በተገለፀው አድራሻ ከሰኞ እስከአርብ ዘወትር በሥራ ሰዓት 2፡30-6፡30 ሰዓት ጠዋት እናከ7:30-11፡30 ሰዓት ከሰዓት በኋላ መግዛት ይቻላል፡፡

የመድሐኒት አቅርቦት ኤጀንሲ(መአኤ)


Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 11፣2013

Deadline: ለ15 ተከታታይ ቀናት


© walia tender

Report Page