Lb መርከብ ሁለገብ የገበሬዎ

Lb መርከብ ሁለገብ የገበሬዎ

Walia Tender

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

መርከብ ሁለገብ የገበሬዎች ኀብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን/ኃላ.የተ/ ለሰብል ህክምና አገልግሎት የሚውል ሴልፎስ በበኩር ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚቸሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዚህ የንግድ ዘርፎች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣
  2. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፌከት/ቲን/ ማስረጃ/ ማቅረብ የሚችል፣
  3. ተጫራቹ የሞላው የሴልፎስ ዋጋ ብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ ተጫራቹ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት ይህ ማለት ግን በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አጠቃላይ ግዥዎች አለመሆኑ መታወቅ አለበት፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው
  5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ ይውላል፡፡ የሚዘጋው በ10ኛዉ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሲሆን የሚከፈተው ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በዩኒየኑ ቢሮ ሲሆን መገኘት የማይችሉ ቢኖሩ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡ቅዳሜ እስከ 6፡30 የዩኒየኑ የስራ ቀን መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡
  6. በዋጋ ማቅረቢያዉ ላይ የተጫራቹን ስምና አድራሻ በመፃፍ ለመርከብ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ተብሎ በጉልህ ከተፃፈ በኋላ በተሰጠዉ የጊዜ ገደብ ዉስጥ ዩኒየኑ ለዚሁ ባዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ከመክፈቻዉ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርበታል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በፖስታ አሽጎ በመርከብ ዩኒየን ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ዉስጥ ጨረታው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይችላል፡፡
  8. የሴልፎስ ግዥው በ20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊያንስ ይችላል፡፡
  9. የሴልፎስ ግዥው የጥራት ሁኔታ በጨረታ ሰነዱ ላይ ያሉትን የሚያሟላ መሆን አለበት
  10. ተጫራቾች ለሴልፎስ ግዥው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00/ሀምሳ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይቻላል፣፡
  11. ተወዳዳሪዎች በባንክ የተረጋገጠ 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ፤በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ(ጥሬ ገንዘቡ በዩኒየኑ የገቢ ደረሰኝ ገቢ ተሰርቶ የገቢ ደረሰኙ ከፖስታው ውስጥ መታሸግ አለበት)ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  12. የጨረታ አሸናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና አይነቶች የውሉን ዋጋ 10 በመቶ /አስር በመቶ/ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  13. አሸናፊው የተገዛውን ሴልፎስ በራሱ ትራንስፖርት የሚያቀርብ ሲሆን ለማስጫኛ እና ለማራገፊያ ወጭ እራሱ ያሸነፈው ተጫራች የሚሸፍን ይሆናል፡፡
  14. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ስለ ሴልፎስ ግዥው እስፔስፊኬሽን፤ መጠንና ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት ይሆናል፡፡

የመርከብ ሁለገብ የገበሬዎች ኀብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን/ኃላ.የተ/


Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013

Deadline:በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00


© walia tender

Report Page