Ins vi pr ot ANRS የውሀ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ

Ins vi pr ot ANRS የውሀ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ

Walia Tender

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2013

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሀ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተጠቀሱትን ምድብ /ሎት/ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር አመታዊ ውል በመያዝ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡-

  1. ዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ያላቸው እና የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የሚቀርቡ የአገልግሎት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30.00/ሰላሳ ብር ብቻ/ በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሀ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ ቁጥር 83 ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከላይ በሰንጠረዡ ለሚወዳደሩበት የእቃው /ሎት/ ትይዩ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ /CPO / ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የውሀ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 88 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በዚሁ ቀን 11፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀጣዩ ቀን በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 88 በዚሁ ቀን 3.30 ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው የጨረታ ሰነድ /ቅጽ/ ብቻ መሙላት ይኖርበታል፡፡
  10. ሌሎች ተጫራቶች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  11. ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  12. ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ዐ58-22-2ዐ1-32/ዐ58-22ዐ-10-78/ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ ፡፡

በአብክመ የውሀ መስኖና ኢነርጅ ልማት ቢሮ


Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013

Deadline:በ16 ኛው ቀን 11፡00


© walia tender

Report Page