Ins fr አልማ

Ins fr አልማ

Walia Tender

የፈርኒቸር ሥራ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ልማት ማህበር /አልማ/ የክልሉን ህዝብና የልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት በማንቀሳቀስ በትምህርት፣ በጤና በስልጠና እና ስራ እድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋጽኦ የማድረግ ተልዕኮን አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡

በመሆኑም ማህበራችን ከግሊመር ጋር በመተባበር በደቡብ ጎንደር ዙሪያ

  • ለ1ኛ ደረጃ ት/ቤት አገልግሎት የሚውል የተለያየ ፈርኒቸር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ፈርኒቸሮች ሰርቶ ከቦታው ድረስ ለማስረከብ በሰነድ ላይ በተያያዘው ዝርዝር መግለጫ መሠረት መስራት የምትፈልጉ ሁሉ፤ ስለሆነም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በዘርፉ በተመሳሳይ ሥራ ስራውን መስራታቸውን የሚገልጽ የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1000.00 በመክፈል አልማ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 108 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች መሰረት በማድረግ ሁሉንም የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነዶች ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎኘ በማድረግ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለመለየት እንዲቻል በግልጽ ፅሁፍ ኢንቨሎፑ ላይ በመፃፍ፣ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር ቢሮ ቁጥር 100 ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን 8፡00 ይታሸጋል በ8፡30 ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበትን ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 413 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 73 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ልማት ማህበር /አልማ/


Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013

Deadline:በ15ኛው ቀን 8፡00


© walia tender

Report Page