HAR CAR CBE18

HAR CAR CBE18

Walia Tender

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሀራጅ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


ማሳሰቢያ 

  1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ሕጋዊ ወኪል የሐራጁን መነሻ 1/4ኛውን በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል:: 
  2. ተሽከርካሪዎቹ ከቀረጥ ነፃ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ሲሆን፤ ጨረታውን ያሸነፈ አካል አግባብ ባለው የጉምሩክ ህግ መሰረት ቀረጥ የሚከፍል ይሆናል:: 
  3. ሐራጁ ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛጉዌ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የባንኩ የሰራተኞች ክበብ ውስጥ ይካሔዳል:: 
  4. ኃ/የተ/የግል ማህበርን ወይም አክሲዮን ማሕበርን ወክሎ መጫረት የሚፈልግ ሥራ አስኪያጅ ወይም ም/ስራ አስኪያጅ የድርጅቱን የመመስረቻ ፅሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ይዞ መቅረብ ያለበት ሲሆን የስራ አስኪያጅ ወይም የም/ሥራ አስኪያጅ ለውጥ ተደርጎ ከሆነ ይህንኑ የሚገልፅ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ ቃለ ጉባዔ ከመመስረቻ ፅሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ጋር ይዞ መቅረብ አለበት:: 
  5. በተሽከርካሪዎቹ ሽያጭ ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ታስቦ ገዥ ይከፍላል:: 
  6. የተሽከርካሪዎቹን ሁኔታ መመልከት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-9 የተጠቀሱትን ተሽከርካሪዎች አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የቀድሞ አማልጋሜትድ ጊቢ) በሚገኘው የባንኩ የመኪኖች ማከማቻ ውስጥ ሲሆን ከተራ ቁጥር 10-33 ያሉትን ተሽከርካሪዎች ደግሞ የቀድሞ ቢራሌ የባንኩ የተሽከርካሪዎች ማከማቻ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት መጎብኘት ወይም በባንኩ የብድር ማገገሚያ ክፍል ድረስ በመምጣት አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ይቻላል::
  7. ንብረቱን ተጫርቶ ያሽነፈና ከፊል ብድር መውሰድ ለሚፈልግ ተጫራች ባንኩ ከፊል ብድር ሊፈቅድ ይችላል:: ሆኖም ብድሩ የሚፈቀደው ባንኩ የሚጠይቀውን ማንኛውንም የብድር መስፈርት ሲያሟላ ብቻ ነው:: 
  8. አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ካልከፈለ ሽያጩ ተሰርዞ ለሐራጁ መነሻ ያስያዘው ገንዘብ አይመለስለትም:: 
  9. ባንኩ ጨረታን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-57-46-46 ወይም 0115-57- 55-09 በመደወል ወይም ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛጉዌ ህንፃ 7ኛ ፎቅ በሚገኘውየባንኩ የብድር ማገገሚያ ንዑስ የስራ ሂደት በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል:: 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 

__________________

Posted:ሪፖርተር  መስከረም 24፣ 2013

Deadline:በሎት የተለያየ

__________________
© walia tender

Report Page