HAR የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ
Walia Tenderየኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ አ.ማ ለሚፈልገዉ የብድር ዕዳ በዋስትና የያዘውንና ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተመለከቱትን ንብረት/ ሆቴል በአዋጅ ቁጥር 97/90 ለባንኮች በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ንብረቱን ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች አንብቦ በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል።
- ጨረታውን በድርጅት ስም የሚጫረት ተጫራች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ወረቀት፣ የንግድ ፍቃድና ከድርጅቱ የተሰጠዉ ውክልና መቅረብ አለበት::
- ተጫራቾች ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት የጨረታውን መነሻ ዋጋ ¼ (25%) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ አ.ማ ስም አሰርተው ወይንም በጥሬ ገንዘብ ይዘው በመቅረብ ንብረቱ በሚገኝበት አድራሻ ቀርበው በመመዝገብ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ከታች ቀንና ሰዓቱ በተገለጸው መሠረት ባለዕዳዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለጨረታ የቀረቡት ንብረቶች በሚገኙበት ቦታ ይካሄዳል፤ ባለዕዳዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል፡፡
- ንብረቱን በሥራ ሰዓት መጎብኘት ለሚፈልጉ ተጫራቾች በስልክ ቁጥር 09-13-44-24-42 ወይም በቢሮ ስልክ 046-110-50-90/6269 የባንኩ ሻሸመኔ ቅርንጫፍ በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሉ መክፈል አለበት፤በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ተሰርዞ እዲስ የሐራጅ ማስታወቅያ ወጥቶ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
- በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወይንም ጥሬ ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል::
- የጨረታው አሸናፊ በሕጉ መሠረት የሚከፈለውን ማናቸውንም ክፍያ ቫትን ጨምሮ እና የስም ማዛወሪያ ከፍሎ ስሙን ወደ እራሱ ያዛውራል፡፡
- ባንክ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ አ.ማ
__________________
Posted:ሪፖርተር መስከረም 24፣2013
Deadline:ህዳር 01 ቀን 2013
__________________
© walia tender