HAR ሕብረት ባንክ4
Walia Tenderየመጀመሪያ ሐራጅ ማስታወቂያ
ሕብረት ባንክ አ.ማ. ጎፋ ቅርንጫፍ በኩል ለሰጣቸው ብድሮች በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች የተመለከተውን ህንፃ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/1992 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
የሐራጅ ደንቦች
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪ ንብረቱ ድጋሚ ለሀራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- በጨረታው ላይ የሚሳተፈው ድርጅት ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ከስራ አስኪያጅ ስልጣን ጋርየተያያዙ የባለአክሲዮኖችን ውሳኔ የያዙ ጉባኤዎች እና የድርጅቱ ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና አስያvች ብቻ ናቸው፡፡
- የሐራጅ ሽያጩ የሚካሄደው የመያዣው ንብረት በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሀራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል፡፡ በሐራጁ ሰላሳ (30) ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም፡፡
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ከሕብረት ባንክ አ.ማ. አክሱም ቅርንጫፍ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- በንብረቱ ሽያጭ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ የታክስና ግብር የስም ማዛወሪያ ጭምር /የጨረታው አሸናፊ/ ገዥ ይከፍላል፡፡
- ቦታው በሊዝ ስሪት የሚተዳደር በመሆኑ የሐራጅ አሸናፊው መከፈል ያለበትን( ውዝፉን ጨምሮ) የሊዝ ክፍያከፍሎ ከተገቢው የመንግስት ተቋም ጋር የሊዝ ውል ይዋዋላል በሊዝ ህጎች ውስጥ የሚኖሩትን ግዴታዎች ለመፈጸም ግዴታ ይገባል፡፡
- ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0347 75 18 04/1994/ 27 93 አክሱም ቅርንጫፍ ወይም 0114-16 3900/16 38 66/99 ጎፋ ቅርንጫፍ ወይም 0114-70 15/69/47 ሕግ አገልግሎት መምሪያ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ሕብረት ባንክ አ.ማ
__________________
Posted:አዲስ ዘመን መስከረም 8፣2013
Deadline:ጥቅምት 12 ቀን 2013
__________________
© walia tender