Grand Ethiopian Renaissance Dam

Grand Ethiopian Renaissance Dam


#የኔ_ግድብ

የግድባችን ሁለተኛው ዙር ውሃ ሙሌት እየተከናወነ ነው ፤ ነሃሴ መጨረሻ ላይ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ግብፅ እና ሱዳይ የግድባችንን ጉዳይ ወደፀጥታው ም/ቤት ይዘውት ቢሄዱም ይህን ነው የሚባል ለውጥ አላመጡም ይልቁንም አብዛኛው የምክር ቤቱ ሀገራት ከሁለቱ ሀገራት በተቃራኒ የግድቡ ጉዳይ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት መፍትሄ እንዲፈለግለት የሚል አቋም አንፀባርቀዋል።

ከምክር ቤቱ ስብሰባ በኃላ ግብፆቹም ሆኑ ሱዳኖቹ አላረፉም፤ ከተለያዩ ሀገራት ጋር በግድቡ ጉዳይ ሃሳባቸውን ለማስረፅ እና ለማሳመን እየተነጋገሩ ነው።

ለአብነት ዛሬ የግብፁ ፕሬዜዳንት ከቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ስለግድቡ መክረዋል።

የግብፅ እና ሱዳን ሚዲያዎችም ቢሆኑ በየቀኑ ስለግድባችን ሳያነሱ አያልፉም። አሁንም ስለግድባችን የተሳሳቱ መረጃዎች ከማሰራጨት አልተቆጠቡም።

Egyptian Independent በተባለው ሚዲያ ብቻ ባለፉት 4 ቀናት ውስጥ 7 የታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ ዘገባቸው ተሰርተዋል። በሌሎች ሚዲያዎች እንደነ Egypt Today , Al Ahram , Daily News Egypt ላይ በርካታ ዘገባዎች በላይ በላይ ሲሰሩ ነበር።

ከፍተኛ መነጋገሪያ የነበረው ግን በEgypt Today የወጣውና በሀገራችን ሚዲያዎች ተተርጉሞ የተሰራጨው ፕሬዜዳንት አል ሲ ሲ ሃያ ከሪማ ብሄራዊ ኮንፈረንስ ላይ ያደረጉት ንግግር ነው።

ንግግራቸው በሀገራችን ግዙፍ የሚዲያ ተቋማት ከአውድ ውጭ ተተርጉሞ/ሆን ተብሎ ብዙዎችን አሳስቷል። አንዳንዶች ግብፅ አቋም የቀየረች እንዲመስላቸው ሆኗል።

በእርግጥ አል ሲ ሲ ምንድነው ያሉት ?

- ኢትዮጵያውያንን በልማት ማገዝ እንሻለን ፣ ያ የሚሆነው ግን የውሃ ድርሻችንን የማይነካ ከሆነ ነው ብለዋል።

- በዓለም ዓቀፍ ህግ አግባብ ተስማምተን በሰላም እና ብልጽግና እንኑር ሲሉ ለኢትዮጵያና ለሱዳን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

- ብሄራዊ ጥቅማችን ማስከበር የማይታለፍ ቀይ መስመር ነው ብለዋል።

- ግብጽ ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ብዙ አማራጭ አላት ሲሉ የገለፁ ሲሆን አማራጮቹን እንደ ሁኔታዎችና አስፈላጊት መጠቀም ይገባል ብለዋል።

- ለታዳሚው ኢትዮጵያ እየገነባች ባለው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያላችሁ ስጋት ተገቢ ነው ያሉ ሲሆን ንግግር ስለዚህ ግድብ በዝርዝር እና በተረጋጋ መንፈስ መነጋገር ይገባል ብለዋል፡፡ “እኛ በጉዳዩ ላይ ያለንን ስጋት በምክንያት እና በተጠና እቅድ ነው የምናየው፡፡ እኛ የቅዠት ህይወት አልኖርንም፡፡ የናንተንም ስሜት ለመጠምዘዝ አንፈልግም” ሲሉ ተናግረዋል።

- “ከኢትዮጵያውንና ከሱዳናውያን ጋር የአባይ ወንዝ ለመልካም ትብብር በር እንደሚከፍት ተነጋግረናል፡፡ ለሁላችንም መልካም እንዲሆን እንሻለን፡፡ ኢትዮጵያውያን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለልማታቸው እንዲያውሉት እንሻለን፡፡ የኢትዮያውያንን የኑሮ ሁኔታ እንዲሁ እንዲሻሻል እሻለን፡፡ ግብጽ የኢትዮጵያውንና የሱዳናውያን ህይወት ብቻ ሳይሆን የመላ አፍሪካ ህይወት እንዲሻሸል ድጋፍ ማድረግ ትችላላች፡፡ ይህ የሚሆነው ግን በአንድ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ያም የግብጽ የውሃ ድርሻ የማይነካ ከሆነ ነው" ብለዋል

- እኛ ሞያተኛና የግብርና ምርቶችን ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችን እንልካለን፡፡ እነሱ ደግሞ የውሃ ድርሻችን እንዳይነካ ያደርጋሉ ብለዋል።

- የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይን ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የወሰዱት በጉዳዩ ዙሪያ የዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለማግኘት መሆኑን ጠቁመዋል። (Tikvah-Family & WALTA)

@tikvahethiopia

Report Page