Fnf የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ2

Fnf የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ2

Walia Tender

ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የመኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ለየብዝሃ ህይወት ጥበቃና የደን ልማት ፕሮጀክት ለ2013 በጀት አመት በክልሉ ዉስጥ ባሉ 6 የደቡብ ወሎ ወረዳዎች እና ቀበሌ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክት ሳይቶች ላይ እንዲሁም 1 ለክልል አስተባባሪዎች የተለያዩ ለመስክ አገልግሎት የሚውሉ መለስተኛ ተሸከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደርእንዲችሉ ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ወይም የተርን ኦቨር ታክስ(TOT) ወይም በደረጃ ሐ ግብር ከፋይነት ተመዝጋቢ ከሆኑ መመዝገባቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ሊብሬና ሶስተኛ ወገን ኢንሹራስ ማቅረብ የሚችል፤
  5. በስሙ የታተመ ደረሰኝ ያለው፤
  6. ተሽከርካሪው አገልግሎት የሚሰጠው በተወካይ ከሆነ ደግሞ በበጀት ዓመቱ የታደሰ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-6 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. የተሸከርካሪውን ዓይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ በመክፈል አማራ ደን ኢንትርፕራይዝ ዋናው መ/ ቤት ባህር ዳር እና ኮምበልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ለኩባንያው ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ከሠነዱ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ፋይናንሻል /የዋጋ መሙያ/ እና /ሲ.ፒ.ኦ/ አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ አማራ ደን ኢንትርፕራይዝ ዋናው መ/ቤት እና ኮምበልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 8፡00 ድረስ መቅረብ አለበት፡፡ በዚሁ ቀን 8፡30 ላይ የጨረታሰነዱ ይከፈታል፡፡
  12. ረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት አማራ ደን ኢንትርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 09 እና ኮምበልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ይታሸግና በዚሁ ቀን 8፡30 በሁለቱም ቦታ ላይ በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ ከሆነ 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ወደሚቀጥለዉ የሥራ መጀመሪያ ቀን በማዛወር ከላይ በተገለጸዉ ተመሳሳይ ሥዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  13. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አማራ ደን ኢንትርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 09 እና ኮምበልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582205235፣ 0582200374 ፣0335511094 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • የድርጅቱ አድራሻ፡- አማራ ደን ኢንትርፕራይዝ ባህር ዳር ቀበሌ-14 አረጋዊያን ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ ቤንማስ ሆቴል ጎን እና ኮምበልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ


Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013

Deadline:በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00


© walia tender

Report Page