EOTC

EOTC


#Update


የደብረ ኃይል ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን መልሶ ለማቋቋም የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

በሀድያና ስልጤ ዞን በቃጠሎና ምዝበራ የወደመውን የደብረ ኃይል ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን መልሶ ለማቋቋም የመሠረት ድንጋይ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ተቀምጧል።

በዚሁ ወቅት ፤ የስልጤ ዞን የሃይማኖት ተቋማት ሰብሳቢ ሀጂ መሐመድ ከሊል መልዕክት አስተላልፈዋል።

የክርስትና እምነት ተከታዮችንም ማፅናናተቸው ተነግሯል።

ሀጂ መሐመድ በዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክት "ችግሩን የፈጠርነው እኛው ነን ችግሩን የምንፈታውም እኛው እንሆናለን" ሲሉ ተናግረዋል። " ቤተ ክርስቲያንና መስጂድ ግጭት ፈጥረው አያውቁም " ያሉት ሀጂ መሐመድ " እንዲህ አይነቱ ችግር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመጣ ነው " ብለዋል። 

የፖለቲካና የራሳቸውን ፍላጎት ለማስፈፀም በየፌስ ቡክ የሚወራው እና የሚተላለፈው መልዕክት ለዚህ አብቅቶናልም ብለዋል። መስጂድንም ሆነ ቤተ ክርስቲያንን ከሚያፈርሱ ሰዎች ፈጣሪ ይጠብቃችሁ ሲሉ ተናግረዋል።

እንዲህ አይነት ክፋት ሲፈፀምም ፈጣሪ ዘብ ያድርን ያሉት ሀጂ መስጂድ ፈርሶ ቤተ ክርስቲያን ይኖራል ቤተክርስቲያን ፈርሶ መስጂድ ይኖራል የሚል እምነት ፈፅሞ የለንም ያሉ ሲሆን የራሱን የሚወድ የሌላውንም ይወዳል ብለዋል።

ሀጂ መሐመድ እነዚህ ቤተ ክርስቲያንን ላጥፋ የሚሉ እኛ የማናውቃቸው ከእምነት አስተምሮ ውጪ የሆኑ አጥፊዎች ናቸውም ብለዋል። አክለውም ፌስቡኩ በወሬ ቢሰራም እኛ በወሬ ሳይሆን በተግባር ለመፍታት እየታገልን ነው ብለዋል። 

ሀጂ መሐመድ ጥፋት በጥፋት አይስተካከልም ያሉ ሲሆን የሆነ ቦታ የሆነ ጥፋት ሲከሰት ያንኑ ጥፋት በመድገም የሚስተካከል ነገር የለምም ብለዋል። " እውነት ለመናገር ተኝተን አናውቅምም እኛው አፍርሰነዋል እኛውም እንሰራዋለን " ሲሉ ቋጭተዋል።

በተመሳሳይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጋራ የማምለኪያ ስፍራቸው የወደመባቸው የፕሮቴስታንት ወንጌላውያን አማኞች ህብረት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ተክለ ሰንበት ተክለ ሥላሴም በዕለቱ የተገኙ ሲሆን፤ በደብረ ኃይል ቅዱስ ሩፋኤል ቅጥረ ቤተ ክርስታያን ለተገኙት የእምነቱ ተከታዮች ለዚህ ቀን ስለደረሳችሁ እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን ብለዋል።

ሚያዚያ ፳ የደረሰውንም የአብያተ ክርስቲያናት ጥቃት አንስተው የወንጌላውያን አማኞቾ ህብረትም ጥቃቱ እንደደረሰበት ገልጸዋል።

ሁሉም ሃይማኖት ተዋዶ ይኖርባት የነበረችውን ወራቤ ከቅርብ ጊዜ ወዲ እንዲህ ያለ ጥቃት ሲደርስባት በማየቴ ባዝንም አብረን እንድንሰባሰብ አድርጎናልና እግዚአብሔር ይመስገን ብለዋል። 

የተቃጠለውን የእናንተን አብያተ ክርስቲያናትም የኛንም የወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት አብረን እንገነባለን ሲሉም አጠቃለዋል።

#EOCTV

Report Page