ENDF

ENDF


#FDREDefenseForce

የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በህወሓት ተይዘው የነበሩ ቦታዎች ማስለቀቁን አስታወቀ።

መከላከያ ሰራዊት ከአማራ ልዩ ኃይል እና የአማራ ሚሊሻ ጋር በመሆን በወሰደው እርምጃ ፦ ጋሳይ፣ ክምር ድንጋይ፣ ጎብጎብ፣ ሳሊና ንፋስ መውጫ ነፃ ማውጣቱን ገልጿል።

የንፋስ መውጫ ከተማ ነዋሪዎች ህወሓት በንፋስ መውጫ ከተማ ንፁሃንን መግደሉንና በርካታ ውድመት ማድረሱን የተናገሩ ሲሆን ሀገር መከላከያ ሰራዊት ወደከተማቸው ሲገባ አቀባበል አድርገዋል።

በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አንደኛ ኮር አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ብርሃኑ ጥላሁን ፤ ከሰሞኑን ህወሓት ህዝቡን በጣም እንደጎዳው ፤ የቀረ ነገር ሳይኖር ዘርፊያ እንደፈፀመ ገልፀው ፥ "ህዝባችን እንዲህ ያለ ወራዳ ተግባር ማየቱ የሚያሳዝን ነው፤ ነገር ግን አሁን ላይ ቡድኑ ዋጋውን እያገኘ ነው" ብለዋል።

ብርጋዴር ጄነራል ብርሃኑ ጥላሁን ፥ ህወሓት በወረራ የያዛቸውን ቦታዎች በሙሉ የማስለቀቅ እና የማፅዳት ስራ እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን አሁን ላይ ከመኪና ወርዶ እየተበታተነ ነው እሱን የመልቀም ስራ እየተሰራ ነው፤ የሚሸሽበትም መንገድ ተዘግቷል፤ ትግራይ ውስጥ ያየውን ጉድ እዚህም ያየዋል፤ እዚህ ገብቶ መውጣት የሚባል ነገር እንደሌለ ያየዋል" ብለዋል።

አዛዡ ፤ ህወሃት ስርዓት መቀየር ነው ፍላጎቴ ይላል እንጂ ተግባሩ ሀገር ማፍረስ እና ሀገር ማውደም ነው ፣ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው የማፍረስ ምልክቱም ህዝቡን ምን እያረገው እንዳለ ማየት በቂ ነው ፤ የከተማውን ህዝብ ጠይቁ ምን አድርጓቸው እንደሄደ ፤ እነሱ የስርዓት አራማጅ አይደሉም ፤ ድሆች ናቸው ፤ ከድሆቹ አፍ ነጥቆ ሽሮ ሳይቀር እየጫነ እየወሰደ ያለው" ሲሉ አስረድተዋል።

"በአጠቃላይ ቡድኑ ስርዓት መቀየር ብቻ ሳይሆን ሀገር ማጥፋት ስለሆነ በዚህ ሀገር አጥፊ ኃይል ላይ ማንም ትዕግስት ሊኖረው አይገባም ኢትዮጵያን ወዳታለሁ የሚል ሁሉ መሰለፍ አለበት" ብለዋል። ይህ ደግሞ ለማንም ሳይሆን እራስን እና ሀገርን ለመከላከል እና ሀገርን ለማዳን ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia

Report Page