Ctr የወረታ ግብርና ቴ/ሙ/ት/

Ctr የወረታ ግብርና ቴ/ሙ/ት/

Walia Tender

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የወረታ ግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ለ2013 በጀት በበጋ የትምህርት መርሃ ግብር ለሚያስተምራቸው ተማሪዎች ለምግብ አገልግሎት የሚውል ግብዓቶች ማለትም፡-

  • ሎት 1 ንጹህ የተበጠረ ሰርገኛ ጤና፣
  • ሎት 2 የባልትና ውጤቶች፣
  • ሎት 3 የኢንዱስትሪ ውጤቶች፣
  • ሎት 4 የማገዶ እንጨት፣
  • ሎት 5 ቀይ ሽንኩርት፣
  • ሎት 6 ሩዝ፣
  • ሎት 7 ዳቦ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስቀረብ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-
  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
  3. የግዥ መጠኑ በሎት ድምር ሲታይ ከ50 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ /ቫት ለሚጠይቁ አቅርቦቶች ብቻ/
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ፣ በትክክል የሚነበብ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በጥንቃቄ በታሸግ ፖስታ በማድረግ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ አቅርቦቶች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫና መጠን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ቢሮ ቁጥር 44 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ጨረታው በአየር ላይ በሚውልበት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በመንግስት የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ተወዳዳሪዎች ናሙና እንዲያቀርቡ ለሚጠየቁት አቅርቦት የማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን መ/ ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና ደግሞ በናሙናው መሠረት ሞልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. አሸናፊው ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርቦ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውል ወስዶ አቅርቦቱን በራሱ ወጭ መ/ቤታችን ድረስ ማቅረብ ይኖበታል፡፡
  10. ረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመንግስት በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  11. አሸናፊው የሚለየው በሎት ጥቅል ድምር ዋጋ ወይም በተናጠል ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቾች በሚሞሉት የመወዳደሪያ ሰነድ እና ፖስታው ላይ የሎት ስም ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና የድርጅቱን ክብ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  13. ኮሌጁ ከሚያስቀርባቸው አቅርቦቶች ላይ 20 በመቶ የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ተጫራቾች ከላይ ከተጠቀሱት ነጥቦች በተጨማሪ በክልሉ የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  15. ተጫራቾች አንዱ በሞላው ዋጋ ላይ ተንተርሶ መሙላት አይቻልም፡፡
  16. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 4460102/815/101 ወይም በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የወረታ ግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ


Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013

Deadline:ለ 15 ተከታታይ ቀናት


© walia tender

Report Page