Ctr ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ

Ctr ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ

Walia Tender

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በስሩ ለሚገኙት ቢሾፍቱ ዶሮ ልማትእና ኮምቦልቻ ቄራ የሚያገለግሉ ከዚህ በታች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 የተጠቀሱትንግብዓቶችን በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችሉ ልምድና ብቃትያላቸውን አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ቁጥር አንድ፡ የካርካስ ውጤታቸው (Carcass yield) 28% የሆኑና ሙሉየስጋ ይዘት ያላቸው፣ ያልከሱና በቆዳቸው ላይ ጉዳት (ጠባሳ) የሌለባቸው ሆነውየቁመና ክብደታቸውም ከ201> ኪሎግራምበላይ የሚመዝኑ፤ በሳምንት አቅርቦትበቁጥር እስከ 138 የሚደርሱ የዳልጋ ከብቶችን ጠቅላላ ብዛት በቁጥር 1,650 ኮምቦልቻ ቄራፋብሪካ ድረስ ማቅረብ የሚችሉትን ተወዳዳሪዎች በመጋበዝ መግዛትይፈልጋል፡፡

ቁጥር ሁለት ፡የካርካስ ውጤታቸው (Carcass yield) 25% የሆኑና ሙሉየስጋ ይዘት ያላቸው፣ያልከሱና በቆዳቸው ላይ ጉዳት(ጠባሳ) የሌለባቸው ሆነውየቁመና ክብደታቸውም ከ151-200 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ፤ በሳምንት አቅርቦትበቁጥር እስከ 22 የሚደርሱ የዳልጋ ከብቶችን ጠቅላላ ብዛት በቁጥር 1,467 ኮምቦልቻቄራ ፋብሪካ ድረስ ማቅረብ የሚችሉትን ተወዳዳሪዎች በመጋበዝ መግዛትይፈልጋል፡፡

ቁጥር ሶስት፡

ጥሬ ዕቃው ዓይነት ብዛት በኩንታል

1. በቆሎ --------7,783

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢ ድርጅቶችመወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  • ተጫራቾች የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢመሆን አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናየሚመለስ ብር ለእያንዳንዳቸው ብር 100,000 ( አንድ መቶ ሺህ) በሲፒኦወይም በካሽ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ለመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ጠቅላላ ካሸነፈውአቅርቦት ክፍያ ብር ላይ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  • ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ በተዘረዘረው እና በተያያዘው የአቅርቦትናየጥራት መሥፈርት መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን አዲስ አበባ ላም በረት አካባቢከሚገኘው የድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል በስራ ሰዓት ከነሐሴ 04 ቀን 2012 ዓ.ምጀምሮ እስከ ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የሚጫረቱበትን የመጫረቻ ሰነድለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100.00 ( አንድ መቶ ብር) በመግዛት ላምበረትበሚገኘው አዲሱ የኤልፎራ ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ በመቅረብ ቅጹ በሚፈቅደው መሠረትዋጋ ሞልተው በማቅረብ እስነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ. ከረፋዱ 4:00 ሰዓትበሚዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሰነዳቸውን ያስገባሉ፡፡
  • የጨረታው ሰነድ የተቀመጠበት ሳጥን ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ. ከጠዋቱ 4 ፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4 ፡30 ሰዓት ላምበረት በሚገኘው አዲሱየኤልፎራ ህንጻ ሶስተኛ ፎቅ በሚገኘው ይከፈትና ተጫራቾች ወይም ህጋዊወኪሎቻቸውበተገኙበት ጨረታው ይካሄዳል፡፡
  • አቅርቦት መጠንን በተመለከተ እንደሁኔታው መጠኑ ሊጨምር ወይም ሊቀንስይችላል፡፡
  • የክፍያው ሁኔታ አቅርቦቱ ከቀረበ ከ45 ቀን በኋላ፡፡
  • ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝመብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 115159688 +251 115159684 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/ የተ/ የግ/ ማኅበር


Posted:አዲስ ዘመን ነሀሴ 3 ቀን 2012
Deadline: August 17, 2020


© walia tender


Report Page