Cn eng የሞጣ ከተማ አስ/ገ/አካ

Cn eng የሞጣ ከተማ አስ/ገ/አካ

Walia Tender

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 05/2013

በአብክመ በምስ/ጎ/ዞን የሞጣ ከተማ አስ/ገ/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የግ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን በUIIDP በጀት የሞጣ ከተማ አስ/ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ጽ/ቤት ለሚያሰራዉ የጠጠር መንገድ ግንባታ package no MOTTA-UIIDPCW-02/2020/2021 ሎት 1 ከልጃለም አበበ ቤት እስከ እስቴዉ መንገድ ድረስ ርዝመት 218 ሜትር ስፋት 7 ሜትር በGC እና RC ደረጃ 9 እና በላይ፣በUIIDP በጀት የዉሃ ተፋሰስ ግንባታ package no MOTTAUIIDP-CW-03/2020/2021 ሎት 11 ከሃይማኖት ማናየ ቤት እስከ 2012 ምራታ ድረስ ርዝመት 600 ሜትር፣ሎት 12 ከማናየ ይርጋ ቤት እስከ 16 ሜትር መንገድ ድረስ ርዝመት 250 ሜትር፣ሎት 13 ከአዲሱ ምራታ እስከአበበ ንጋቴ ቤት ድረስ ርዝመት 185 ሜትር ፣ ሎት 14 ከበላይ ፍቃዴ ቤት እስከ ጥሩስራ ሰዉነት ቤት ድረስ ርዝመት 173 ሜትር፣ ሎት 15 ከብሩ ካሴ እስከ አባ ሞፃ ዲች ድረስ ርዝመት 123 ሜትር፣ በCIP በጀት የዉሃተፋሰስ ግንባታ package no MOTTA-CIP-CW-03/2020/2021 ሎት16 ከድመት ገደል ዲች እስከ 2012 ምራታ ድረስ ርዝመት 620 ሜትር በGC እና RC ደረጃ 9 እና በላይ፣በUIIDP በጀት package no MOTTAUIIDP-CW-05/2020/2021 ሎት 1 አንድ ብሎክ ሸድ ግንባታ በGC እና BC ደረጃ 9 እና በላይ፣በCIP በጀት package no MOTTA-CIP-CW-06/2020/2021 ሎት 1 የፖሊስ ጽ/ቤት የቢሮ ግንባታ በቁጥር 1 በGCደረጃ 9 እና በላይ BC ደረጃ 8 እና በላይ፣በCIP በጀት package no MOTTA-CIP-CW-08/2020/2021 ሎት 1 GCP production and installation ስራ በቁጥር 20 በGC እና RC ደረጃ 9 እና በላይ፣ በሮድ ፈንድበጀት የዉሃ ተፋሰስ ጥገና package no MOTTA-CIP-MAT-03/2020/2021 ሎት 2 ከRTC እስከ አቆቤ ድረስ ርዝመት 360 ሜትር በGC እና RC ደረጃ 9 እና በላይ የግንባታ ፈቃድ ካላቸዉ ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጫራታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin number) ያላቸዉ፣
  2. የግዥዉ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች የግንባታ ብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-3 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. የጫራታዉን ዝርዝር መግለጫ ከጫራታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. በጥቃቅን የተደራጁ ተጫራቾች የልዩ አስተያየት ተጠቃሚ የሚያደርጋቸዉን ወቅታዊ የሆነና ለጽ/ቤት በአድራሻ የተፃፈ ማስረጃ ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 100 ብር (አንድ መቶ ብር) ከፍለዉ ከሞጣ ከተማ አስ/ገን/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 የጫራታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡የጫራታ ሰነድ ለመግዛት ወይም ለመዉሰድ ሲመጡ ተራ ቁጥር 1፣2 እና 3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ኮፒ አድርጋችሁ መምጣት አለባችሁ፡፡
  8. ተጫራቾች ሰነድ ወስደዉ ወይም ገዝተዉ መወዳደር የሚችሉት 1 (አንድ) ሎት ወይም ሳይት ላይ ብቻ ሲሆን በተጨማሪ GCP production and installation መወዳደር ይቻላል፡፡ከGCP production and installation ግንባታ ዉጭ አንድ ተጫራች ሁለትና ከዚያ በላይ ሰነድ ገዝቶ (ወስዶ) ቢወዳደር ሙሉ ለሙሉ ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
  9. ተጫራቾች የጫራታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለጠጠር መንገድ ግንባታ ለሎት 1 ብር 7,000.00 (ሰባት ሽህ ብር)፣ለዉሃ ተፋሰስ ግንባታ ለሎት 11 እና 16 ለእያንዳንዱ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሽህብር)፣ለሎት 12 እና 13 ለእያንዳንዱ ብር 8,000.00 (ስምንት ሽህ ብር)፣ለሎት 14 እና 15 ለእያንዳንዱ ብር 5,000.00 (አምስት ሽህ ብር)፣ሎት 1 አንድ ብሎክ ሸድ ግንባታ ብር 5,000.00 (አምስት ሽህ ብር)፣ሎት1 የፖሊስ ጽ/ቤት የቢሮ ግንባታ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሽህ ብር)፣ሎት 1 GCP production and installation ብር 500,00 (አምስት መቶ ብር)፣የዉሃ ተፋሰስ ጥገና ሎት 2 ብር 2,000.00 (ሁለት ሽህ ብር) ባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ተጫራቾች በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  10. ተጫራቾች የጫራታ ሀሳባቸዉን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስምና አድራሻ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታዉ ላይ የሚወዳደሩበትን የግንባታ አይነትና ሎት በመፃፍ ከሞጣ ከተማ አስ/ገን/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18 ለጫራታ ከተዘጋጀዉ የጫራታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  11. ተጫራቾች ጫራታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት ሁኖ በ31ኛዉ ቀን እስከ ጧቱ 4፡00 ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸዉን ከተዘጋጀዉ የጫራታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡ ጫራታዉ በ31ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡20 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በሞጣ ከተማ አስ/ገን/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 16 ይከፈታል፡፡
  12. የጫራታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  13. ስለጫራታዉ ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0586611890/0221 ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 18 በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  14. በተጨማሪ በአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጫራታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

የሞጣ ከተማ አስ/ገ/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን


Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013

Deadline:በ31ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡00


© walia tender

Report Page