Cn csl የጎዛምን ሁለ/የገ/ህ

Cn csl የጎዛምን ሁለ/የገ/ህ

Walia Tender

የግንባታ አማካሪ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምስራቅ ጐጃም ዞን በደ/ማርቆስ ከተማ የጎዛምን ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን .ኃ.የተ.ለሚያስገነባው የአግሮ ሜካናይዜሽን አገልግሎት ማዕከል ግንባታ የግንባታ አማካሪ ደረጃ 5 እና በላይ የሆኑ ተወዳዳሪዎች በጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ደረጃ 5 የታደሰ የግንባታ አማካሪ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፣
  5. በጨረታው የሚሣተፉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 በመክፈል ይህማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን ከጎዛምን ዩኒየን ዋና ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 01 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ማንኛውም ተወዳዳሪ ጨረታ ከፍቶ አሸናፊውን መለየት፣ የስራ ውል ማዘጋጀት፣ የግንባታ ክትትል ማድረግ፣ የክፍያ ሰርተፊኬት ማዘጋጀት እና በዩኒየኑ የሚገነቡ ትንንሽ የግንባታ ስራዎችን በሙያው ማገልገል የሚችልበትን መርሃዊ የአገልግሎትዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡
  7. አሸናፊው የሚለየው የቴክኒክ መስፈርቶችን ከ100% በመመዘን 80% እና በላይያመጡትን ተወዳዳሪዎች ለቀጣይ የዋጋ ውድድር እንዲያልፉ ይደረጋል፡፡ በዋጋ ውድድር ወቅት ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተወዳዳሪ የጨረታው አሸናፊ ይሆናል፡፡80% እና በላይ ያመጣ የቴክኒክ ማወዳዳሪያ በዋጋ ላይ ለመወዳደር የሚያስችል ነጥብ እንጅ የዋጋ ውድድር ላይ የሚደመር አይደለም፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱ የሚገባው በአንድ ኦርጅናል እና በሁለት ኮፒ ሲሆን ኦርጅናል የቴክኒክ መወዳደሪያው ለብቻ በአንድ ፖስታ፣ ሌሎች ሁለት ኮፒዎችም ለየብቻ በፖስታ በማድረግ ሶስቱን የቴክኒክ ፖስታዎችን እንደገና በአንድ ትልቅ ፖስታ ማድረግ፣ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ የዋጋ/ፋይናንሻያል/ መወዳደሪያዎችንም በተመሣሣይ መልኩ ለየብቻ በፖስታ ካደረጉ በኋላ ሶስቱንም በአንድ ትልቅፖስታ አድርጎ እንደገና የቴክኒካልና የፋይናንሽያል ፖስታዎችን በሌላ ትልቅ ፖስታውስጥ አድርጎ በድርጅቱ ማህተም በተዘጋጀ ፖስታ በማሸግ ዩኒዬኑ ባዘጋጀውየጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጎዛምን ዩኒዬንጽ/ቤት የጨረታ ማስታወቂያው በወጣ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  11. አሸናፊ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ድምር 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡ አሸናፊ ተጫራች በ5 ቀናት ውስጥ ውል ካልያዘ ግን ዩኒዬኑ የጨረታ ማስከበሪያን በቀጥታ ይወርሣል፡፡
  12. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በዚህ ያልተጠቀሱት ሃሣቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
  14. ተጫራቾች ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 7713179/0911908637 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡

የጎዛምን ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን .ኃ.የተ.


Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013

Deadline:15 ተከታታይ የስራ ቀናት


© walia tender

Report Page