Cn የነፋስ መውጫ ከተማ አስ/ገ/አ

Cn የነፋስ መውጫ ከተማ አስ/ገ/አ

Walia Tender

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ጎንደር ዞን የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ አካባቢ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን በUIIDP በጀት እና በCIP በጀት የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት ለሚያሰራዉ መሰረተ ልማት1. የጠጠር መንገድ ግንባታ package no NEFAS MEWOCHA-UIIDP-CW-04/20/21

ሎት 1 ከዋናው አስፓልት እስከ ማረሚያ ቤት ድረስ ርዝመት 260 ሜትር ስፋት 10 ሜትር ይህንን ለመስራት የተጫራቾች ደረጃ በGC እና RC ደረጃ 9 እና በላይ ተሳታፊ ይሆናሉ 2. የጠጠር መንገድ ግንባታ package no NEFAS MEWOCHA-UIIDP-CW-04/20/21

ሎት 2 ከዋናው አስፓልት እስከ ጤና ጣቢያ ቤት ድረስ ርዝመት 400 ሜትር ስፋት 10 ሜትር ይህንን ለመስራት የተጫራቾች ደረጃ በGC እና RC ደረጃ 8 እና በላይ ተሳታፊ ይሆናሉ 3. የኮብል መንገድ package no NEFAS MEWOCHA-UIIDP-CW-02/20/21 ሎት 1 ከዶ/ር አብይ ህንጻ እስከ ላይ ጋይንት ወረዳ አስተዳደር ድረስ ርዝመት 209 ሜትር ስፋት 10 ሜትር ይህንን ለመስራት የተጫራቾች ደረጃ በGC እና RC ደረጃ 9 እና በላይ ተሳታፊ ይሆናሉ 4. የኮብል መንገድ package no NEFAS MEWOCHA-UIIDP-CW-02/20/21 ሎት 2 ከውብነህ አዳነ እስከ ስላሴ ቤተክርስቲያን ድረስ ርዝመት 280 ሜትር ስፋት 10 ሜትር ይህንን ለመስራት የተጫራቾች ደረጃ በGC እና RC ደረጃ 9 እና በላይ ተሳታፊ ይሆናሉ 5. የኮብል መንገድ package no NEFAS MEWOCHA-UIIDP-CW-02/20/21

ሎት 3 ከተስፌ ሙሉጌታ እስከ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክርስቲያን ድረስ ርዝመት 280 ሜትር ስፋት 10 ሜትር ይህንን ለመስራት የተጫራቾች ደረጃ በGC እና RC ደረጃ 9 እና በላይ ተሳታፊ ይሆናሉ 6. የወሃ ማፋሰሻ ዲች package no NEFAS MEWOCHA-UIIDP-CW-01/20/21 ሎት 2 ከሳሊ ገበያ እስከ ዛንጢ ችግኝ ጣቢያ ድረስ ርዝመት 1175 ሜትር ስፋት 80 ሴ/ሜ ይህንን ለመስራት የተጫራቾች ደረጃ በGC፤BC እና RC ደረጃ 8 እና በላይ ተሳታፊ ይሆናሉ 7. የወሃ ማፋሰሻ ዲች package no NEFAS MEWOCHA-UIIDPCW- 01/20/21

ሎት 4 ከወዳጀ ዘውዴ ቤት እስከ እንዳለ ፍቃዱ ቤት ድረስ ርዝመት 247 ሜትር ስፋት 70 ሴ/ሜ ይህንን ለመስራት የተጫራቾች ደረጃ በGC፤BC እና RC ደረጃ 9 እና በላይ ተሳታፊ ይሆናሉ 8. የወሃ ማፋሰሻ ዲች package no NEFAS MEWOCHA-CIP-CW-01/20/21

ሎት 6 ከአስቻ ሚካኤል እስከ አስቴር ንጋቴ ቤትና ዋናው አስፓልት ድረስ ርዝመት 294 ሜትር ስፋት 70 ሴ/ሜ ይህንን ለመስራት የተጫራቾች ደረጃ በGC፤BC እና RC ደረጃ 9 እና በላይ የግንባታ ፈቃድ ካላቸዉ ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin number) ያላቸዉ፣
  2. የግዥዉ መጠን ከብር 50,000 (ሃምሳ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች የግንባታ ብቃት ማረጋገጫ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1-3 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. የጨረታዉን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. በጥቃቅን የተደራጁ ተጫራቾች የልዩ አስተያየት ተጠቃሚ የሚያደርጋቸዉን ወቅታዊ የሆነና ለጽ/ቤት በአድራሻ የተፃፈ ማስረጃ ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 100 ብር (አንድ መቶ ብር) ከፍለዉ ከነፋስ መውጫ ከተማ አስ/ገን/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ወይም ለመዉሰድ ሲመጡ ተራ ቁጥር 1 ፣ 2 እና 3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ኮፒ አድርጋችሁ መምጣት አለባችሁ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለጠጠር መንገድ ግንባታ ለሎት 1 ብር 28,000.00 (ሃያ ስምንት ሽህ ብር) ለሎት2 ብር 55,000.00/ሃምሳ አምስት ሽህ ብር/፣ ለኮብል መንገድ ለሎት 1 ፣ 2 እና 3 ለእያንዳንዱ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሽህ ብር)፣ ለውሃ ማፋሰሻ ዲች ለሎት 2 ብር 55,000.00/ሃምሳ አምስት ሽህ ብር/፣ ለሎት 4 ብር 11,000.00 (አስራ አንድ ሽህ ብር)፣ ለሎት 6 ብር 14,000.00(አስራ አራት ሽህ ብር/በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ተጫራቾች በመስሪያ ቤቱ የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨሬታ ሰነዳቸውንና የጨሬታ ማስከበሪያቸውን በሁለት ፖስታ በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስገባት አለባቸው ስምና አድራሻ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ እንዲሁም ፖስታዉ ላይ የሚወዳደሩበትን የግንባታ አይነትና ሎት በመፃፍ ከነፋስ መውጫ ከተማ አስ/ገን/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ለጨረታ ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  10. ተጫራቾች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ሁኖ በ22ኛዉ ቀን እስከ ጧቱ 4፡00 ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸዉን ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡ ጨረታዉ በ22ኛዉ ቀን ከጧቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በነፋስ መውጫ ከተማ አስ/ገን/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል፡፡
  11. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  12. ስለጨረታዉ ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0584451374/0258 ወይም በአካል ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  13. በተጨማሪ በአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

የነፋስ መውጫ ከተማ አስ/ገ/አካ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ቡድን


Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013

Deadline:በ22ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00


© walia tender

Report Page