CN INS ENG MECOD 17

CN INS ENG MECOD 17

Walia Tender

የጨረታ ማስታወቂያ 

በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የአርሚ ፋውንዴሽን አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት /16-01B ምዕራፍ ሁለት በሰሚት አካባቢ ለሚሰራቸው የህንፃ ግንባታ የሚከተሉትን ሥራዎች እና አቅርቦት በሚቀርበው ዝርዝር መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል:: 

  1. Cementious type of Water Proofing work for septic tank 
  2. Membran type of Water Proofing Work for pump house

ስለሆነም ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ብቻ ከፍለው ከፕሮጀክቱ ፋይናንስ ክፍል በመውሰድ በተያያዘው የሥራ ዝርዝር መሰረት የሚሰሩበትን/የሚያቀርቡበትን ዋጋ በመሙላት በፖስታ አሽገው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ በፕሮጀክቱ ግቢ የግብአት አቅርቦት እና አስተዳደር ኬዝ ቲም ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:: ጨረታው ሰኞ 02/2/2013ዓ/ም ከረፋዱ 4.00 ሰዓት ይዘጋል:: ቴክኒካል ዶክመንት በዕለቱ 4.30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የፋይናንሻል ሰነድ የሚከፈትበት ቀን በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል:: 

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈረት:- 

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና TIN No ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው:: 
  2. ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸውን የሚገልፅ ታክስ ክሊራንስ (tax clearance) ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው:: 
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በተጫራቾች መመሪያ ላይ በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት:: 
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም፣ ፊርማ እና መራ ስም እንዲሁም አድራሻቸውን በመግለፅ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: 
  5. ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበቸው:: 
  6. በውሃ ስርገት ሥራ (Water Proofing Work) ላይ ልምድ ያለው መሆን አለበት 
  7. ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዱ ለየብቻ ታሽጐ መቅረብ አለበት:: 
  8. የሥራው መጠን ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል:: 
  9. ቴክኒካል ሰነድ በእለቱ የሚከፈት ሲሆን ፋይናሻል የሚከፈትበት ቀን ለተጫራቾን በውስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል:: 
  10. ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ሲገኙ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና (Unconditnal Bank Guarantee ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው 
  11. ፕሮጀክቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: 

አድራሻ፡- ሰሚት ኮንዶሚኒየም 2ኛ በር ከጊዮርጊስ ቤተክርስትያን ወረድ ብሉ 

ስ/ቁ 0118-34-92-41 

__________________

Posted:ሪፖርተር  መስከረም 24፣ 2013

Deadline:02/2/2013


__________________
© walia tender


Report Page