Bu sl tx vi የቡሬ ፖሊቴክኒክ

Bu sl tx vi የቡሬ ፖሊቴክኒክ

Walia Tender

በድጋሜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የቡሬ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለማስተማሪያ ጥሬ ዕቃዎችን እና አላቂ የቢሮ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው የምትሳተፉ ድርጅቶች በቀረበው የጨረታ ዝርዝር በንግድ ፍቃዱ መሰረት በሎት መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  • ሎት 1. የኮንስትራክሽን እቃዎች መሸጫ መደብር
  • ሎት 2. የጽህፈት መሳሪዎች /ስቴሽነሪ/ መደብር
  • ሎት 3. ኤሌክትሪክ እቃዎች መሸጫ መደብር
  • ሎት 4. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች መሸጫ መደብር
  • ሎት 5. የመኪና እቃዎች መለዋወጫ መደብር
  • ሎት 6. ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት መሸጫ መደብር

የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የም ትችሉ መሆኑን እየገለፅን፣ ተወዳዳሪዎች

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን /ያላቸው እና ጨረታው ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1 እስከ 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸውጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ግዥውን ግምታዊ ዋጋ መሰረት በማድረግ ከ0.5 በመቶ ያላነሰና ከ2 በመቶ ያልበለጠ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ /ሲ.ፒ.ኦ / ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው ፡፡
  6. የጨረታ መቆያ ጊዜ ከ26/01/2013 ዓ.ም እስከ 16/02/2013 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ ይሆናል ፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት የጨረታ መወዳደሪያውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጫራታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16/02/2013 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
  8. ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን በ15ኛው ቀን ማለትም 16/02/2013 ዓ.ም ሲሆን ከቀኑ 11፡30 የጨረታ ሳጥን ታሽጎ ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በ17/02/2013 ዓ.ም በ4፡00 ጨረታው የሚከፈት ሁኖ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. በቀረበው የመጫረቻ ሰነድ መሰረት ሙሉ በሙሉ ዋጋ ካልሞሉ በጨረታው አይወዳደሩም፣
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 0587740771 ደውሎ ወይም በአካል ቀርቦ መረዳት ይቻላል፡፡
  11. አሸናፊው ድርጅት ውል ከያዘ በኋላ እቃውን ከኮሌጁ ንብረት ክፍል ማስረከብ /ገቢ ማድረግ / ይኖርበታል፡፡
  12. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጫራታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው ፡፡
  13. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት /ግለሰብ /ማሸነፉን በተገለፀ በአምስት ቀን ውስጥ ውል መያዝ አለበት፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለፀ በ5 ቀን ውስጥ ውል ካልያዘ የጨረታ ማስከበሪያው ውርስ ይሆናል፡፡
  15. የጨረታ ሰነዱን ኮሌጁ ግ/ፋ/ን /አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በ50.00 ብር ገዝቶ መውሰድ ይቻላል፡፡

የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013

Deadline:16/02/2013


© walia tender

Report Page