Bu sl ag cmp tx vi fr ot የደባርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌ

Bu sl ag cmp tx vi fr ot የደባርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌ

Walia Tender

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የደባርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2012 ዓ.ም የተለያዩ የማሰልጠኛ እቃዎችን ማለትም

  • ሎት 1. የኮንስትራክሽን እቃዎች፣
  • ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያዎች፣
  • ሎት 3. የጽዳት እቃዎች፣
  • ሎት 4 የግብርና እቃዎች፣
  • ሎት 5. የኤሌክትሪክ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ሎት 6. ኮምፒውተርና የአይቲ ማቴርያሎች፣
  • ሎት 7. ጫማዎችና የተዘጋጁ ልብሶች፣
  • ሎት 8. ብትን ጨርቅ ፣
  • ሎት 9 የአውቶ እቃዎች ፣
  • ሎት 10 የፈርኒቸር እቃዎች ፣
  • ሎት 11. የሳኒተሪ ማቴርያሎች ሁሉም

ውድድሮች በሎት የሆኑ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው
  2. ከመንግስት የሚጠበቅበትን የዘመኑን ግብር የከፈለና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያለው ማስረጃውን አያይዛችሁ ማቅረብ የምትችሉ::
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ 200,000.00/ ሁለት መቶ ሺ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል እንዲሁም የቫት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  4. በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በደባርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ የጨረታ አይነት የማይመለስ ብር 30 በመክፈልና በመውሰድ መወዳደር ይችላሉ::
  5. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን በ16ኛው ቀን በ3፡00 ታሽጎ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ተጫራቾች ባይገኙም የመክፈቻ ጊዜው አይራዘምም በዚህ እለት ህዝባዊ በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል::
  6. በጨረታ ሰነዱ ላይ የተወዳዳሪው የድርጅቱ ማህተም ስምና ፊርማ እንዲሁም አድራሻ ማስቀመጥ ይኖርባችኃል::
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  8. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉትን እቃ ኮሌጁ ድረስ በማጓጓዝ ለንብረት ክፍል ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል::
  9. ተጫራቾች ማሸነፋቸው እንደተገለጽላቸው በ5 ቀን ውስጥ ውል ከኮሌጁ ጋር መያዝ ይጠበቅባቸዋል::
  10. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም::
  11. የጨረታውን አሸናፊ የምንለየው በጥቅል ድምር የሚታይ ስለሆነ ተጫራቾች ሁሉንም አይተሞች መሙላት የሚጠበቅባቸው ሲሆን ሁሉንም ማቴርያሎች ያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል::
  12. ኮሌጁ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  13. ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 117 08 06 ወይም 058 417 19 73 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

የደባርቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013

Deadline:በ16ኛው ቀን በ3፡00


© walia tender

Report Page