Bu የግንደወይን ከተማ ውሃ አገ/ጽ
Walia Tenderግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ጎጃም ዞን በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የግንደወይን ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት የቧንቧ መገጣጠሚያ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉን መሆኑን ይገልፃል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፣
- የግዥ መጠን ብር 50 ሺህ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200 ብቻ በመክፈል ሰነዱን ከገ/ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ ግ/ወይን ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት የገቢ ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማለትም ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ወይን ከተማ ውሃ ፍሣሽ አገ/ጽ/ቤት የገቢ ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ታሽጐ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ካልተገኙ ግን በሌሉበት በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ጨረታው የሚከፈት መሆኑን
- ጨረታው ውድቅ ቢሆን ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎች/ ያወጡትን ወጭ ጽ/ቤቱ የጠያቂ አይሆንም፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፋቸውን እቃዎች ግ/ወይን ከተማ ውሃ ፍሣሻ አገ/ጽ/ቤት ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ወጭ ማቅረብ የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- መ/ቤቱ አሸናፊውን የሚለየው በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋ ሞልቶ ያቀረበውን ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ አሸናፊው ድርጅት ከውል በፊት ያሸነፋቸውን እቃዎች 25 በመቶ የመጨመር/የመቀነስ/ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በመ/ቤቱ በእቃ ጥራት ባለሙያ እየተረጋገጡ ከመ/ቤቱ እቃ ግምጃ ቤት ንብረት ክፍል ጋር ርክክብ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በዓል/ቅዳሜና እሁድ/ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት መሆኑን ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡
- ካሸናፊ ድርጅቱ 2 በመቶ የቅድመ ግብር የሚቆረጥ መሆኑን፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ከ6 ቀን ጀምሮ ቀርቦ ውል መያዝ አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉ ተገልፆለት ውል ከተፈፀመ በኋላ እስከ 10 ቀናት ውስጥ እቃውን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ በጽ/ቤቱ ውስጥ ካለው እቃ ግምጃ ቤት ማስረከብ ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን ድርጅቱ ያሸነፋቸውን እቃዎች ካላቀረበ መ/ቤቱ የውል ማስከበሪያውን ይወርሣል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት እቃውን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ በጽ/ቤቱ ውስጥ ካለው እቃ ግምጃ ቤት ካስረከበ በኋላ በሚቀርበው ህጋዊ የንብረት ገቢ ደረሰኝ መሰረት ክፍያው የሚፈፀምለት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የዕቃ ናሙና ከጽ/ቤቱ ማየት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በጨረታው በሚያወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን የማይመስድ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት /አንድ ተጫራች/ ከአንድ በላይ ጨረታ ሞልቶ ቢገኝ ከተጫራች ውጭ ያደርጋል/ይሆናል/
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ገቢ ግዥና ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0586640373/0586640675 በመደወል ዝርዝር መረጃውን ማግኘት ይቻላል፡፡
ማሣሰቢያ መ/ቤቱ ተጫራቾች የሞሉትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
የግንደወይን ከተማ ውሃ እና ፍሣሽ አገ/ጽ/ቤት
Posted:በኩር መስከረም 25፣ 2013
Deadline:በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30
© walia tender