Bu ሐበሻ ሲሚንቶ

Bu ሐበሻ ሲሚንቶ

Walia Tender

ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ

የጅብሰም ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

Purchase bid No.02/ጅፕሰም/2012

ፋብሪካችን ለሲሚንቶ ምርት በግብአትነት የሚጠቀምበትን (መጠኑ ከ1540ሚ.ሜ) ያልበለጠ 75,000 ቶን ጂፕሰም ለአንድ አመት በሚቆይ ኮንትራት በዘርፉ ከተሰማሩ እና የስራ ፍቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ማንኛውም ተጫራች ስለጨረታው እና ስለ ፑሚሱ ዝርዝር እና ተያያዥ መመሪያዎችን የያዘውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅታችን ዋናው መስሪያ ቤት ጎተራ ወሎ ሰፈር ወንጌላዊት ህንጻ ፊት ለፊት ከሚገኘው ካስማ ህንጻ 8ተኛ ፎቅ ግዢና አቅርቦት መምሪያ ቀርቦ ሰነዱን በመውስድ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢድ ቦንድ፡ ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በድርጅቱ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ ገቢ የተደረገበትን የደረሰኙን ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራች ድርጅቶች የምታቀርቡትን የጅብሰም አይነት እና ጥራት እንዲሁም የመጫረቻ ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው ዝርዝር መሰረት በማቅረብ ሆለታ ፋብሪካችን ድረስ ማንኛውንም ወጪ አካቶ የምታቀርቡበትን የአንድ ዋጋ እና ተያያዥ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ እስከ ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም ከላይ በተመለከተው የድርጅታችን ዋና መ/ቤት አድራሻ “እንድታስገቡ እንጠይቃለን፡ጨረታው ጥቅምት 12 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ከላይ በተገለጸው አድራሻ በዋናው መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ

ስልክ ቁጥር 011-4163273/0904033975


Posted:ሪፖርተር መስከረም 24፣2013

Deadline:ጥቅምት 12 ቀን 2013


© walia tender

Report Page