Benishangul Gumuz

Benishangul Gumuz

Tikvah Family

* Update

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ካማሽ ከተማ ሙሉ ለሙሉ መግባቱን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ኢንስፔክተር ምስጋናው እንጂፈታ አሳውቀዋል።

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ካማሽ መግባቱን ተከትሎ በአካባቢው ይሰማ የነበረው የተኩስ ልውውጥ መቆሙንና በአካባቢው የነበረውን ታጣቂ ኃይልም ማፈግፈጉን ገልፀዋል።

ኢስፔክተር ምስጋናው እንጅፈታ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ በካማሺ ዞን የሚንቀሳቀሱ እራሳቸው የቤንሻንጉል ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ቤህነን) የሚባሉ ታጣቂዎች የዞኑን በርካታ ቦታዎች ተቆጣጥረው መቆየታቸውን አስረድተዋል።

"የቤህነን ታጣቂ ከኦነግ ሸኔ ጋር ቅንጅት አላቸው፣ ከእነሱ ጋር እየተጋገዙ ነው ይህን የሚያደርጉት፣ በዞኑ 5 ወረዳ ነው ያለው ከዞን እና የወረዳ ማዕከሎች ውጪ አንድም ቀበሌ በመንግስት እጅ ላይ የለም" ሲሉ አክለዋል።

ከመንግስት እጅ በወጡ ቦታዎች በፖለቲካው እንቅስቃሴ የለም፣ ሙሉ በሙሉ ግንኙነቶችም ተቋርጠዋል በዚህ ምክንያት በዞኑ ሰብዓዊ ቀውስ ተፈጥሯል ሲሉ ገልፀዋል።

ኢንስፔክተር ምስጋናው ፥ ባለው የፀጥታ ኃይል ውስንነት የተነሳ ችግር አለባቸው ተብሎ በጥናት የተለዩ ቦታዎች በመግባት ህግ ማስከበር እንዳልተቻለ አመልክተው ፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ ህብረተሰቡ በተጎሳቆለ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው ብለዋል።

ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ቦታዎች ያልተዘረፈ ከብት የለም፤ ያልተዘረፈ ንብረት የለም፣ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ነው ያለው ፤ ህብረተሰቡ በረሃብ እየተጎዳ ነው፣ መድሃኒት የለም ተዘርፏል፣ ጤና ኬላዎች ግብአት አይገባላቸውም ግንኙነት የለም ተቋርጧል በዚህም ህብረተሰቡ ከፍተኛ ስቃይ ላይ መሆኑን አመልክተዋል።

በክልሉ የፀጥታ ኃይል በለመጠናከሩ ምክንያት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰው ሰላም ለማስፈን ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች በታጣቂዎች መገደላቸውን ኢንስፔክተር ምስጋናው እንጅፈታ ተናግረዋል።

ሰላም አስከባሪዎቹ ከኦሮሚያ ጋር በሚዋሰነው የካማሺ ዞን ወረዳ ቦልጅጋንፎይ "ፏፏቴ" በተባለች ቀበሌ የነበረን ኃይል ለመቀየር ከሶሎ ከተማ ተነስተው ወደዛ ሲንቀሳቀሱ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የደፈጣ ጥቃት ተከፍቶባቸው ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የደረሰውን ጉዳት ፣ የፀጥታ ኃይሎችን ቁጥር ከመናገር የተቆጠቡት ኢስፔክተር እንጂፈታ በጥቃቱ ብዙ የፀጥታ ኃይሎች መጎዳታቸውን አስረድተዋል።

ኢንስፔክተር ምስጋናው በካማሺ ዞን የሚንቀሳቀሰውን ቤህኒን የተባለውን የታጣቂ ቡድን ለመመከት ከክልሉ አቅም በላይ ሆኖ እንደነበር ገልፀው ፤ ተጨማሪ የፀጥታ ኃይል ድጋፍ እንዲደረግ ለፌዴራል መንግስት ጥያቄ ሲያቀርቡ እንደነበር እና ትላንት ተጨማሪ ኃይል ወደዞኑ መግባቱን ተናግረዋል።

Credit : ጋዜጠኛ ኖኮር መልካ (VOA)

@tikvahethiopia

Report Page