#BALDERAS

#BALDERAS


ከታሰሩት የባልደራስ ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች መካከል ሁለቱ በዋስ ሲለቀቁ 40ዎቹ ለሰኞ ተቀጥረዋል።

የእነ እስክንድር ነጋን የችሎት ውሎ ለመታደም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በጥቅምት 11/2014 ዓ/ም የሄዱ 42 የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በትላንትናው ዕለት በፓሊስ መታሰራቸው መግለፁ ይታወሳል።

ባልደራስ ፓርቲ አባላቱ እና ደጋፊዎቹ የታሰሩት ፥ አቶ እስክንድር በእስር ቤት የደረሰባቸውን ድብደባ በችሎት ከሰሙ በኃላ እያለቀሱ ችሎቱን አቋርጠው ከችሎት ወጥተው በመንገድ ላይ እያኑ ነው ፖሊስ የታሰሩት ብሏል።

ታሳሪዎቹ ዛሬ ጠዋት 4 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ " ችሎት ውስጥ ረብሸዋል፣ ሲወጡ ደግሞ ፍትህ የለም ፣ መንግስት የለም በማለት ሁከት እና ብጥብጥ በመቀስቀስ " ሲንቀሳቀሱ መያዙን ገልጿል።

ከድርጊቱ ጋር በተያያዘ የምስክሮችን ቃለ ለመቀበል እና ማስረጃቸውን ለማሰባሰብ የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ቆጠሮ ጠይቋል።

የ42ቱ ተጠርጣሪዎች ጠበቆች ፖሊስ ያቀረበው የጊዜ ቀጠሮ አቤቱታ ውድቅ እንዲሆን ጠይቀዋል። 

"በችሎት ውስጥ ተፈጸመ ለተባለው ድርጊት ፖሊስ የሚመለከተው ሳይሆን በወቅቱ ችሎቱ በራሱ ትዕዛዝ የሚሰጥበት ነው። ሆኖም ግን ችሎቱ ምንም አይነት ትዕዛዝ ባልሰጠበት ፖሊስ ያቀረበው አቤቱታ ተገቢ አይደለም" ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ " ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀበት ምክንያት በሕግ ምንም አይነት ድጋፍ " የለውም በማለት የጊዜ ቀጠሮው ውድቅ እንዲሆን በመጠየቅ ከእስር እንዲለቀቁ ለፍ/ቤት ጥያቄ አቅርበዋል ።

ግራና ቀኙን ያከራከረው ፍርድ ቤት ሁለት ህፃናት ልጆች ያላቸውን ተጠርጣሪዎች በዋስትና እንዲወጡ፣ የተቀሩትን ደግሞ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ወደ 3 ቀን በመቀየር ለፊታችን ሰኞ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲቀርቡ፣ እንዲሁም የተጠርጣሪዎቹን ተሳትፎ ለይቶ በቀጣይ ቀጠሮ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል ።

እስረኞች በተያዙበት ወቅት ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ችሎቱም ለደረሰባቸው ጥሰት ክስ ማቅረብ እንደሚችሉ ገልጿል።

(ባልደራስ)

Report Page