Aud ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት
Walia Tenderወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/ የተ/ የግል ማህበር
በውጪ ኦዲተሮች ሂሳብ ለ ማስመርመር በድጋሚ የወጣ የጨረታማስታወቂያ
ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግል ማህበር የ2012 በጀት ዓመትሂሳብ ለማስመርመር የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት የምታሟሉ ተጫራቾችበጨረታው እንድትሳተፉ እየገለጽን፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ለመሳተፍ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ እና የዘመኑንግብር የከፈለ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው እናበዘርፉ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይገባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከፈቃድ ሰጪው አካል ከዋናው ኦዲተር መ/ቤት አና ከኢትዮጵያ ሂሣብአያያዝና ኦዲት ቦርድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የIFRS ሰርቲፋይድ የሆነ እና በ “IFRS” ኦዲት ሰርቶ የሚያውቅና ማስረጃ ማቅረብየሚችል፡፡
- ተጫራቾች በኢትዮጵያ ምርት ገበያ (ECX) ባለስልጣን የኦዲት ምርመራእንዲያደርጉ የተመዘገቡ መሆን ይገባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ ቀደም ከሠሩባቸው መ/ቤቶች ለሠሩበት ምስክርነት የሚሠጡየመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃዎችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሙሉ ዋጋ 2% ( ሁለት መቶኛ ) በባንክበተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ስርዝ ድልዝ የሌለው ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምር) የጨረታማስከበሪያ ዋስትና በማያያዝ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል በኦርጅናል እና በኮፒ በፖስታበማሸግ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ዋናው መ/ቤት አ.አ 7ኛ ፎቅ ማስገባትይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች እንደታወቁ ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑተመላሽ ይደረጋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ መሆኑን እንደተገለፀለት በአምስት ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላዋጋ 10% (10 መቶኛ ) የውል ማስከበሪያ በማስያዝ የስምምነቱን ውል ይፈርማል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ውል ከተፈራረመ በኋላ በተያዘው የጊዜ ገደብ ስራቸውንአጠናቀው የመጨረሻ የኦዲት ሪፖርት እንዳቀረቡ የሰሩበት ክፍያ በውሉ መሰረትከጨረሰ እና የውሉ ጊዜ ሲያበቃ ያስያዘው ውል ማስከበሪያ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በድጋሚ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮዘወትር በሥራ ሰዓት በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት ብር ) በመክፈል ከወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዋና መ/ቤት 7ኛ ፎቅ ፋይ/ግ/ን/አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን አንገልፃለን፡፡
- ጨረታው በ 16 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 4 ፡ 00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ተጫራቶቹወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ከጠዋቱ 4 ፡ 30 ሰዓትበዋናው መ / ቤት አዲስ አበባ የሚከፈት ይሆናል፡፡ 16 ኛው ቀን የሥራ ቀንካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/ የተ/ የግ/ ማህበር፡- መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ፊንፊኔ ህንፃ 7 ኛፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-552-10-09/011-552-14-58
ፖሣቁ 9515 ፋክስ 011551-36-54 አዲስ አበባ
ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ/ የተ/ የግል ማህበር
Posted:አዲስ ዘመን ነሀሴ 5 ቀን 2012
Deadline: August 26, 2020
© walia tender