Article

Article

Selam_et

[ማሳሰቢያ፡ ይህ ጹሑፍ እንዳንድ አንባቢያንን ምቾች ሊነሳ ይችላል]

አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር የለ ፍቃዷ ወሲብ ከፈጸመ፤ ይህ ያለአንዳች ጥርጥር በሕግ ፊት አስገድዶ መድፈር ነው። ተገላቢጦሹ ቢሆንስ? ሴት ልጅ ያለ ወንዱ ፍቃድ ወሲብ ብትፈጽምስ?

ይህ እንግሊዝን ጨምሮ በበርካታ ሃገራት ሕግ እንደ አስገድዶ መድፈር አይቆጠርም።

ጾታዊ ግንኙነትን መሰረት ያደረጉ ጥናቶችን የሚያካሂዱት ተመራማሪ፤ ይህ በሕግ ፊት አስገድዶ መድፈር ተደርጎ መታየት ይኖርበታል ይላሉ።

-------------------------------------------------------

ዶ/ር ሲኦብሃን ዊአር በላንካስተር ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት እአአ ከ2016-2017 ባሉ ጊዜያት በሴቶች ያለፍቃዳቸው ወሲብ እንዲፈጽሙ የተገደዱ ከ200 በላይ ወንዶችን አነጋግረው ጥናታዊ ምርምር አድርገዋል። በዚህ ሳምንት ይፍ የተደረገው ጥናት ከ30 በላይ ወንዶች ጋር ፊት ለፊት የተደረገ የቃለ መጠይቅ ውጤትም ተካቶበታል።

ጥናቱ ወንዶች በምን አይነት ሁኔታ ያለፍቃዳቸው ወሲብ እንዲፈጽሙ እንደሚገደዱ፣ ይህ በደል የሚያስከትለው ተጽእኖ እና በሕግ የሚሰጠው ትርጓሜ ምን እንደሚመስል ዳሰሳውን አድርጓል።

-------------------------------------------------------

በጥናቱ የተሳተፉት ወንዶች ማንነታቸው ይፋ አልተደረገም። ከተሳታፊዎቹ መካከል ግን አንዱን እንደምሳሌ እንውሰደው፤ ጆን ብለንም እንጥራው።

ጆን እንደሚለው ከህይወት አጋሩ ጋር ሳለ ''ትክክል ያልሆኑ'' ነገሮች የሚላቸውን ምልክቶች አስተዋለ መጥፎ ነገሮችም መከሰት ጀመሩ። እንደ ጆን ከሆነ የህይወት አጋሩ በቅድሚያ እራሷን መጉዳት ጀመረች። አንዳንዴም እራሷ ላይ በምትወስዳቸው አደገኛ እርምጃዎች በመደናገጥ ወደ ህክምና ይዟት የሚሄድበት አጋጣሚዎች እንዳሉም ይናገራል።

ጥንዶቹ ለሰዓታት የአዕምሮ ህክምና የምታገኝበትን ሁኔታ ተመካክረዋል። የሥነ ልቦና ባለሙያ ጋር ቀጠሮ ቢያዝላትም ፍቃደኛ ሳትሆን መቅረቷን ጆን ይናገራል። ይህ ነገር እያደር ሲመጣ እራሷ ላይ ጉዳት ማድረሱን አቁማ ፊቷን ወደ ጆን አዞረች።

''አንድ ቀን ሳሎን ቁጭ ብዬ ነበር። ምግብ ከምናበስልበት ስፍራ መጣችና አፍንጫዬን በኃይል በቡጢ መትታኝ ወደ መኝታ ቤት እየሳቀች ሮጣ ገባች" በማለት የህይወት አጋሩ ኃይለኝነት የጀመረበትን ሁኔታ ጆን ያስረዳል።

እያደር በሄደ ቁጥርም ዱላው እና ጉንተላው እየበዛ ሄደ።

"ከሥራ እንደተመለሰች ሁልጊዜም ወሲብ እንድናደርግ ትጠይቀኛለች" ይላል። "በጣም ኃይለኛ ትሆናለች። እንዳንዴም ከሥራ ቦታዋ ወደቤት ባትመለስ ብዬ የምመኝበት ጊዜያት አሉ።"

አንድ ጠዋት ላይ ጆን ከእቅልፉ ሲነሳ የህይወት አጋሩ ቀኝ እጁን ከአልጋው ራስጌ ጋር አስረዋለች። ከዚያም ከአልጋው ጎን በነበረ ስፒከር አናቱን ትመታው ጀመር። ከዚያም ግራ እጁን በጨርቅ ከአልጋው ጋር ካሰረች በኋላ ከእርሷ ጋር ወሲብ እንዲፈጽም በኃይል ማስገደድ ጀመረች።

በፍርሃት እና በድንጋጤ የተዋጠው ጆን ሰውነቱን ለእርሷ ጥያቄ ዝግጁ ማድረግ ተሳነው፤ በዚህ የተበሳጨቸው ሴት ደጋግማ ትመታው ያዘች። ከአልጋው ጋር የታሰሩ እጆቹን ከመፍታቷ በፊት ለሰዓታት ታስሮ ቆይቶ ነበር።

ከዚህ ሁነት በኋላ ስለ ጉዳዩ ለመወያየት ጥረት ቢያደርግም እርሷ ፍቃደኛ ስላልነበረች እንደልተሳካ ጆን ያስረዳል።

የጆን የህይወት አጋር ነብሰ ጡር መሆኗን ተከትሎ፤ ኃይለኝነቷ መቀነሱን ይናገራል። ልጃቸው ከተወለደች ጥቂት ወራት በኋላ ጆን አንድ ጠዋት ከእንቅልፉ ሲነቃ እጁ ከአልጋው ጋር ታስሮ ያገኛል።

ከዚያም በኃይል ቫያግራ (የወሲብ ፍላጎትን የሚያነሳሳ እንክብል) እንዲወስድ ካደረገች በኋላ አፉን በጨርቅ አፍና ወሲብ እንደፈጸመች ጆን ይናገራል።

''በወቅቱ ምንም ማድረግ አልቻልኩም" ይላል ጆን።

"ይህን ካደረገችኝ በኋላ ለምን ያክል ጊዜ እንደቆየሁ ባለውቅም ብቻ ለረዥም ሰዓት መታጠቢያ ክፍል ውስጥ ውሃ እላዬ ላይ እያፈሰስኩ ቆየሁ. . . በስተመጨረሻም ወደ ሳሎን ሄድኩ። ይህን አድርጋ ስታበቃ ለመጀመሪያ ጊዜ የተናገረችው 'እራት ምንድነው የምንበላው?' ነበር።"

ጆን ይህ ለሰዎች ለመናገር ጥረት ማድረጉን ይሁን እንጂ ሰዎች ስላማያምኑት እውነትነቱን በዝርዝር ማስረዳት ስለሚከብደው ብዙ ጊዜ እንደሚተወው ይናገራል።

"አንዳንድ ሰዎች 'ለምን ቤቱን ጥለህ አትወጣም' ይሉኛል። ይህ ግን ቤቴ ነው። ቤቱን የገዛሁት ለልጆቼ ነው። በገንዘብም ረገድ ከእርሷ ጋር እንድኖር ግድ ሆኖብኛል። ይህም ብቻ አይደለም፤ 'ስትመታህ ለምን መልሰህ አትመታትም' ይሉኛል። ግን እሱ እንደመናገሩ ቀላል አይደለም። እንደው ድሮ ነበር ማምለጥ የነበረብኝ" በማለት ጆን ይተርካል።

ይህን መሰል ታሪክ በርካታ በጥናቱ ተሳታፊ የሆኑ ወንዶች የሚጋሩት እውነታ ነው። የዶ/ር ሲኦብሃን ዊአር ጥናት ትኩረቱን ያደረገው በሴቶች ተገደው ወሲብ በሚፈጽሙ ወንዶች ላይ የሚከሰተው ተጽእኖ ስፋት እና መጠንን ለመለየት ሲሆን፤ ተገዶ ወሲብ መፈጸም ከሚደርሱ በደሎች አንዱ እንጂ ብቸኛው እንዳልሆነ ተመራማሪዋ ይናገራሉ።

በጥናቱ ተሳታፊ ከሆኑ አንዱ ለበርከታ ዓመታት የደረሰበትን በደል ለፖሊስ ባስታወቀበት ወቅት "ይህ ነገር ባያስደስትህ ኖሮ ቀደም ብለህ ለፖሊስ ሪፖርት ታደርግ ነበር" እንደተባለ በጥናቱ ላይ ቃሉን ሰጥቷል።

የጥናቱ ተሳታፊው ጆን እንዲህ ብሏል፡ "ስለጉዳዩ ማውራት ያስፈራል። ያሳፍራል። ደፍረን ስናወራ ደግሞ የሚያምነን የልም። ምክንያቱም ወንዶች ነና። 'እንዴት ወንድ ልጅ በሴት ልጅ ይበደላል? ወንድ ልጅ እኮ ነህ?' ይሉናል።"

ጥናቱ ምን ይፋ አደረገ?


√ ወንዶች አብዛኛውን ጊዜ በሴት የህይወት አጋሮቻቸው የሚደርስባቸውን ወሲባዊ በደሎች ሪፖርት አያደርጉም። የቤት ውስጥ በደልን ሪፖርት ካደረጉም ወሲባዊ በደሎችን ሳይጠቅሱ ነው ሪፖርት የሚያደርጉት።

√ በእዕምሮ ጤና ላይ ሊያስከትል የሚችለው ጫና እጅግ ከፍተኛ ነው። መሰል በደል የደረሰባቸው ወንዶች እራሳቸውን ለማጥፋት አስበዋል።

√ የጥቃቱ ሰለባዎች የወሲብ እርካታቸው በከፍተኛ ደረጃ ዝቅ ብሏል።

በዶ/ር ሲኦብሃን ዊአር ጥናት ግልጽ ከተደረጉ ትክክለኛ ያልሆኑ አመለካከቶች መካከል፤ ወንዶች ከሴቶች በላይ ጠንካራ ስለሆኑ ሴቶች ወንዶችን አስገድደው ወሲብ መፈጸም ቸይችሉም፣ ወንዶች ፍቃደኛ ካልሆኑ ብልታቸው ስለማይቆም የሴቷ ብልት ውስጥ ሊገባ አይችልም የሚሉ የሚገኑበት ሲሆን፤ በተጨማሪም ከሴት ጋር የወሲብ ግንኙነት ማድረጊያ አጋጣሚዎች በሙሉ አዎንታዊ ናቸው የሚሉት ይገኙባቸዋል።

ዶ/ር ሲኦብሃን እንደሚሉት ሌላው የተሳሳተው አመለካካት 'ወንዶች ብልታቸው ከቆመ ወሲብ ለማድረግ ፍላጎት አላቸው' የሚለው ነው ይላሉ። ተመራማሪዋ እንደሚሉት "ብልት የሚቆመው ለተነቃቃ የአዕምሮ ክፍል ምልሽ ሲሰጥ ነው።"

"ወንዶች በፍርሃት፣ በንዴት፣ በጭንቀትም ውስጥ ሳሉ እንኳን የብልት መቆም ሊያጋጥማቸው ይችላል።"

-------------------------------------------------------

በጥናቱ ከተሳተፉ መከካል ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው ወንዶች፤ በሴቶች ያለ ፍቃዳቸው ወሲብ እንዲፈጽሙ ከተገደዱባቸው ሁነቶች መካከል በአደንዛዥ እጽ እና አልኮል ጫና ስር ከወደቁ በኋላ መሆኑን ይጠቀሳሉ።

ከዶ/ር ሲኦብሃን ዊአር ጋር ፊት ለፊት ቃለ ጠይቅ ካደረጉት አንዱ፤ ከአንዲት ሴት ጋር በምሽት ክለብ ሲዝናና ከቆየ በኋላ አታላ የሰጠችው እጽ እራሱን እንዲስት እንዳደረገው እና ያለ ፍቃዱ ወሲብ እንዲፍጽም እንዳስገደደችው ተናግሯል።

ሌላ ወጣት ለዶ/ር ሲኦብሃን ሲናገር በአንድ ወቅት ለወንድ ጓደኛው የጻፈውን ደብዳቤ የተመለከተች የሥራ ባልደረባው ከእርሷ ጋር ወሲብ ካልፈጸመ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ነው ብላ እንደምታስወራበት በማስፈራራቷ ያለፍቃዱ ወሲብ መፈጸሙን አምኗል።

ዶ/ር ሲኦብሃን ዊአር በጥናቶቻቸው የተሳተፉ ወንዶች ያለ ፍቃዳቸው ወሲብ እንዲፈጽሙ መደረጋቸውን ''ተገዶ መደፈር'' ሲሉ ይጠሩታል ይላሉ። ብዙዎቹም እንግሊዝን ጨምሮ በሌሎች ሃገራት ሕጎች ይህ በደል ''ተገዶ መደፍር'' ተብሎ አለመጠራቱ ያበሳጫቸዋል።

በጥናቱ ላይ ከቀረቡ 8 የመፍትሄ ሃሳቦች መካከል አንዱ ወንዶች ያለ ፍቃዳቸው በሴቶች ወሲብ እንዲፈጽሙ ሲደረጉ በሕጎች ላይ ''አስገድዶ መደፈር'' ተበሎ እንዲፈረጅ አሳስቧል።

©BBC

#ሻሎም!

@selam_et

Report Page