#1

#1

https://t.me/felegethiopia

የዓለምን አስተሳሰብ የለወጡ ሴቶች !

ዓለማችንን በመለወጥ በኩል እና ሴትነት በራሱ ይዞት የሚመጣውን ጫና ተቋቁመው ልዩነት መፍጠር የቻሉ ብዙ ሴቶች ያሉ ሲሆን ከዚህ በታች የምትመለከቷቸውም ይህንን የፈፀሙና ለመጪዎቹ ትውልዶች መንገድ የጠረጉ ናቸው፦

1.ቫላንታይን ትረሽኮቫ

በህዋ ጥናት እና ምርምር እ.አ.አ በ1963 የሩሲያ “ቮስቶክ” የተባለች መንኮራኩርን ይዛ ወደ ህዋ በመብረር ያረፈች የመጀመሪያዋ ሴት ስነህዋ ተመራማሪ ለመሆን የበቃች ሲሆን ለዚህም ተግባር የወሰደባት ጊዜ ሶስት ቀናቶች ብቻ ነበሩ።

የሷን ፈለግ በመከተል ከ20 አመት በሆላ ሴሊ ራይድ ወደ ህዋ በመጎዝ በአለም ሁለተኛዋ እና በአሜሪካ የመጀመሪያዎ ሴት የስነ-ህዋ ሳይንስ ተመራማሪ ለመሆን ችላለች።

2. ሜሪ ኩሪ

እ.አ.አ በ1903 “በራዴሽን” ዙሪያ ባደረገችው ጥናት እና ምርምር የመጀመሪያዋ ሴት የኖቭል ፕራይዝ ተሸላሚ ለመሆን ስትበቃ ፤ እ.አ.አ በ1911 በኬሚስትሪ ዘርፍ ባደረገችው ጥናት እና ምርምር “ራዲየም” እና “ፖሎኒየም” የተባሉ ሁለት ንጥረ-ነገሮችን በማግኘት የመጀመሪያዋ ሴት ባለሁለት ኖቭል ፕራይዝ ተሸላሚ ለመሆን በቅታለች። በሁለት የተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ሁለት የኖቭል ሽልማቶችን በማሸነፍ በአለማችን የመጀመሪያዋ ለመሆን ችላለች።

3. ኢኒጂነር ዳና አሊሪያ

እ.አ.አ 1961 የመጀመሪያዋ ሴት የናሳ ኢኒጂነር ዳና አሊሪያ ትምህርቷን የተከታተለችው በኮምፒውተር ሳይንስ ኢኒጂነሪንግ ነው። ስራዋን የጀመረችው በካርኒፎርኒያ “ጄት ፕሮፑሊሽን ላብራቶሪ” ቢሆንም በሆላላይ ግን የመጀመሪያዋ ሴት የናሳ ኢኒጂነር ለመሆን በቅታለች። 

ዳና አሊሪያ በናሳ ቆይታዋ የጠፈር ተመራማሪዎች ከጠፈር ወደ ምድር መረጃዎችን እና መልእክቶችን የሚያስተላልፉበት በየነ-መረብ ለመዘርጋት በቅታለች። በዚህም ስራዋ በአሜሪካን የወታደሮች ጥናት እና ምርምር ላብራቶሪ ውስጥ የመጀመሪያዋ ሴት ስራ አስኪያጅ ሆናለች።

4. አሚሊያ ኢርህርት

እንደ እ.አ.አ ከ1930 በፊት አንድ ሰው ለብቻው የአትላንቲክ ውቅያኖስን በኢሊኮፍተር ለማቋረጥ ብዙ ሙከራዎች ተደርገው ነበር። ነገር ግን ይህን ማሳካት የቻለው አንድ ሰው ብቻ ነው ። እንደ እ.አ.አ በ1932 አሚሊያ ኢርህርት የአትላንቲክ ውቅያኖስን በማቋረጥ በአለማችን ሁለተኛዋ እና የመጀመሪያዋ ሴት ለመሆን በቅታለች። 

ይሄንን ጉዞ ለማጠናቀቅ የፈጀባት 15 ሰዓት ብቻ ሲሆን ሰአቱም በወቅቱ ሪከርድ ሆኖ ተይዟል። እ.አ.አ በ1937 አለምን ለመዞር ባደረገችው በረራ ሙከራ እስካሁንም የደረሰችበት ሳይታወቅ ልትጠፋ ችላለች። እንደ እ.አ.አ በ1953 ጃኬሊን ኮችራን የሷን ፈለግ በመከተል የንፋስ እንቅፋችነትን በመቀነስ የጄት ፍጥነትን ከአስራአንድ አመት በኃላ በእጥፍ መጨመር ችላለች።

@felegethiopia

Report Page