01

01

YWC

በተለያዩ ምክንያቶች ባለንበት ቦታ ሆነን ስራን መስራት ተመራጭ ሆኗል፡፡ ኢንተርኔትን በመጠቀም እንዴት ነው ገንዘብ መስራት የምንችለው? ከተቻለስ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት አማራጮች ምንድናቸው? በትክክል እናንተም መጠቀም እምትችሉትን 7 መንገዶች አሳያችኋለሁ፡፡ ከነዚህም 7 መንገዶች ውስጥ አኔ ባለፉት ቅርብ ወራት እንዴት ከ3ዐ‚ዐዐዐ ብር በላይ መስራት እንደቻልኩ አሳያችኋለሁ፡፡

 


ሰላም ኃይለአብ ያገርሰው እባላለሁ የኔ ፕላትፎርም ባለቤት እና መስራች ነኝ በ2ዐ12 ዓ.ም መጀመሪያዎች ላይ የተለያዩ የኦንላይን ቢዝነስ በማቋቋም አሁን ላይ ስኬታማ የሆኑ ድርጅቶችን መመስረት ችያለሁ፡፡ ኢንተርኔት ላይ ውጤታማ ከመሆኔ በፊት 2 ዓመት ወደ ኋላ ልውሰዳችሁ እና online business ከመጀመሬ በፊት ሙዚቀኛ ነበርኩ፣ ይሁን እና የሰራሁት ትልቅ ስራ ስላልነበር እውቀናም ሆነ ትርፍ አላገኘሁበትም፡፡ ግን እንደ ሙዚቃ የሚያስደስተኝ ነገር ስላልነበር ከመስራት ወደ ኋላ አልልም በወቅቱም IMT records የሚባል ሌብል ውስጥ ከተለያዩ ሙዚቀኞች ጋር እሰራ ነበር፡፡ በሰይፉ ኢቢኤስ ስራችንንም አቅርበን ነበር እናም በመጨረሻ ሀይማኖታዊ በሆነ ምክንያት ሙሉ በሙሉ ሙዚቃውን አቆምኩ

 

እንግዲህ በዚህ 2 ዓመት ውስጥ የተለያዩ የኦንላይን ቢዝነሶችን በማጥናት እና በመሞከር ቆየሁ አብዛኞቹ ሐሰተኞች እና phishing ወይም አካውንታችንን Hack ለማድረግ የተዘጋጁ ሲሆኑ በእውነት ግን ኦንላይን ላይ ገንዘብ መስራት የሚያስችሉ መንገዶችን አግኝቻለሁ፡፡ ከ7 በላይም ናቸው አማራጮቹ ነገር ግን እኔ ስለማላውቀው ነገር ያልተጨበጠ መረጃን ልሰጣችሁ ስለማልፈግ እኔ እራሴ ገንዘብ መስራት የቻልኩበትን እና ጓደኞቼ እና ሌሎች ሰዎች ሲሰሩበት ያየሁትን አማራጮች ለእናንተ አቀርባለሁ፡፡

 

ይህ ኮርስ 2 ክፍሎች ይኖሩታል የመጀመሪያው 7 ትክክለኝ ኢትዮጵያ ውስጥ ገንዘብ ልንሰራባቸው የሚያስችሉትን መንገዶች ሲሆን 2ኛው ክፍል ላይ እኔ የተጠቀምኩትን አማራጭ ሙሉ በሙሉ ደረጃ በደረጃ አሳያችኋላሁ፡፡ ይህ ኮርስ ከተለመደው የት/ት ሂደት ወጣ ባለ ይዘት ሳትሰላቹ አስደሳች በሆነ መንገድ ለማስተማር በጥንቃቄ የተዘጋጀ ነው፡፡ በቀጥታ ወደ ቪዲዮው፡፡

 

7ኛው ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን ገንዘብ መስራት የምንችልበት አማራጭ

Crypto currency:- ለዚህኛው አማራጭ አዲስ ለሆናችሁ ወይም በትክክል ኢትዮጵያ ውስጥ መስራቱን ማወቅ ለምትፈልጉ ይህ መረጃ በመጠኑም ይረዳችኋል፡፡

 

Crypto currency:- ማለት የኢንተርኔት ገንዘብ፣ ብር ማለት ሲሆን ምርት እና አገልግሎቶችን ለመገበያየት የሚያስችል ገንዘብ ነው፡፡ ልክ እንደ ዶላር፣ ፓውንድ ገንዘብ ሲሆን ልዩ የሚያደርገው ኖት ወይም ወረቀት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ዲጅታል ሲስተም ላይ የተመሰረተ መሆኑ ነው፡፡ privacy, security ወደ ሚለው ከገባን አሁን ላይ ካሉት የገንዘብ ዓይነቶች ልዩነት እየሰፋ ይሄዳል ነገር ግን አጠር ያለ መረጃን ለመስጠት ያክል ነው፡፡ youtube ላይ የኔ space በሚል ቻናል ሙሉ በሙሉ ሰለ Crypto currency እና እንዴት ገንዘብ መስራት እንደምትችሉ ሙሉ ኮርስ አቀርብላችኋለሁ፡፡ ስለዚህ subscribe አድርጋችሁ ጠብቁኝ ፍቅሩ ካላችሁ፡፡

 

ገንዘብ ከምንለው ይልቅ ማዕድን ብንለው የተሻለ ይገልፀዋል ምክንያቱም ይህን ማዕድን ልዩ የሆነ ስራን በመስራት የምናገኘው ሳይሆን Mining ወይም ቁፋሮ በማድረግ የምናገኘው ስለሆነ ነው፡፡ ካሉት አማራጮች መሀል cryptotab ድረገፅ ላይ በመግባት ቁፋሮ ወይም Mining መጀመር እንችላለን፡፡ ሙሉ በሙሉ ጊዜየን ሰጥቼ ይሄን ስራ የማልሰራበት ምክንያት በቁፋሮ የምናገኘውን ገንዘብ እጅግ በጣም ትንሽ እና

አብዛኞቻችን በወር የሚከፈለውን የካርድ ክፍያ እና የወርሃዊ የኢንተርኔት ክፍያ መክፈል ስለማያስችል ነው 1ዐዐ% ይህን አማራጭ በመጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ገንዘብ የሚሰሩ ልጆች አሉ ነገር ግን በነሱ ስር የተመዘገቡ ብዙ ሰወች ስላላቸው ነው



6ኛው ገንዘብ መስራት የምንችልበት አማራጭ

you tube እጅግ በጣም ብዙ ኢትዮጵያውያን you tubers ይህን አማራጭ እየተጠቀሙበት ነው፡፡ you tube ላይ ቪዲዮ በመልቀቅ ከአስተዋዋቂዎች ወይም Google Aosense ተካፋይ መሆን ይቻላል፡፡

 

ይሁን እና ብዙ ሰዎች በጣም የተሳሳተ መረጃ ነዉ ያላቸው


  1. የመጀመሪያዉ ስህተት youtube ላይ ትርፋማ ለመሆን ብዙ view ያስፈልገኛል

ማለትም ብዙ view እና ብዙ subscriber ያለው ሰው ክፍ ያለ ገንዘብን ያገኛል የሚል በፍፁም የተሳሳተ መረጃ ነው

ለዚህም ነው በጣም ብዙ የprank videos እናም ምንጫቸው የማይታወቅ የዜና ቻናሎች የተስፋፉት


ምን ልላቹ ፈልጌ ነው ትንሽ subscriber እና ትንሽ view እያላቸው 1million ከዛም በላይ subscriber እያላቸው ነገር ግን በ20 እና በ15ሺ subscriber ብዙ ገንዘብ ማግኘት ይቻላል

በሌላ በኩል ደሞ youtube መጀመር ፈልጋቹ ትርፋማ የሚያደርግ ሃሳብ ላጣቹ የተለያዩ ሃሳቦችን የምታገኙበትን ቀመር እና በአጠቃላይ ስለ Youtube ያለተዳሰሱ እና እናንተም ዉጤታማ መሆን የምትችሉበትን መንገድ


እንደናንተ ፍላጎት መሰረት ስለyoutube ትክክለኛ እና ብዙ ሰወች ያላገናዘቡትን ሚስጥሮች የያዘ video youtube channel ላይ እንለቅላቹሃለን

No እኔ ከካሜራ ፊት መቅረብ አልፈልግም የሚል ምክ. ላላችሁም ፊታችንን ሆነ እኛ መናገር ሳይጠበቅብን በቀላሉ ልንሰራቸው የምንችላቸዉን videos እናቀርባለን


5ኛው ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን ገንዘብ መስራት የምንችልበት አማራጭ

ሶሻል ሚዲያ ማኔጅመንት፡- ይህኛው አማራጭ በሚገርም ሁኔታ ሀገራችን ላይ ያለ ነገር ግን ትንሽ ሰዎሽ ብቻ ጠቀም ያለ ገንዘብ የሚያገኙበት ነው፡፡ በአብዛኞቻችንም እንደ ትንሽ ነገር የሚታይ ነው፡፡

 

በአጭሩ ይህ የስራ አማራጭ የተለያዩ ቢዝነስ ያላቸው ሰዎች ሶሻል ሚዲያ ላይ ያላቸውን እንቅስቃሴ ለባለሙያዎች በመስጠት እነሱ ስራቸው ላይ ትኩረትን መስጠት ይፈልጋሉ፡፡ ይህም ማለት ስለድርጅቱ ፎቶ እና ቪዲዮ በስዓቱ ፖስት ማድረግ ክፍያው ከፍ ሲልም እነዚህን ፎቶ እና ቪዲዮ እኛው በማዘጋጀት ተከፋይ መሆን ነው፡፡ በተጨማሪም ከደንበኛ የሚመጡ ጥያቄዎችን መመለስ እና የዛን ድርጅት ስም ማህበራዊ ገፆች ላይ ተደራሽ ማድረግ ነው፡፡

 

ለምሳሌ ያህል ሀገራችን ላይ ምርጥ ፋሽን Designer’s መሀል ቁንጅና አንዷ ስትሆን በስሟ የልብስ Brand ፈጥራ ያለች ጐበዝ ሴት ነች፡፡ Instagram ላይ ስራዎችዋን የምታስተዋውቅበት Kunjina በሚለው አካውንት እሷ ሳይሆን ሶሻል ሚዲያ ማናጀር ስላላት ተያያዥ ስራዎችን በማኔጀሩ በኩል ያልቃል ማለት ነው፡፡

 

ከዚሁ ሶሻል ሚዲያ ላይ ሳንወጣ በጣም ብዙ ገንዘብ መስራት የሚያስችለው አካውንት መሸጥ ነው፡፡ አንድ አንድ ሰዎች በቀላሉ ብዙ Follower መሰብሰብ ይችላሉ፡፡ ለነሱም በጣም ቆንጆ አማራጭ የሆነው አካውንት መሸጥ ለብዙዎች በቀላሉ ምርታቸውን ማሳወቅ የሚችሉበት መንገድ በመሆኑ እጅግ በጣም ብዙ ፈላጊ ነገር ግን በጣም ትንሽ አቅራቢ አለው፡፡

 

እኔ ብዙ የምመክረው አይደለም Follower ለማግኘት እረዥም ጊዜ ይወስዳል፡፡ ነገር ግን ብዙ ሳይደክሙ የተለያዩ ነገሮችን በመልቀቅ በቀላሉ Follower ማግኘት የምትችሉ ሰዎች ጥሩ አማራጭ ነው፡፡

 

4ኛው ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን ገንዘብ መስራት የምንችልበት አማራጭ፡-

Affiliate marketing:- ብዙዎቻችሁ የምታውቁት የስራ አማራጭ ቢሆንም ሀገራችን ውስጥ በጣም ትንሽ ሰዎች ትርፍ እየሆነበት ያለ የስራ ዓይነት ነው፡፡

Affiliate marketing በቀላሉ ሀገራችን ላይ ያለውን የድለላ ስራ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ በሙሉ ትኩረት እና ጉልበት ይህን ስራ በመስራት ውጤታማ መሆን ይቻላል፡፡ አንድ ሻጭ የሚሰጠንን የ Affiliate ሊንክ በመጠቀም ምርቱን በመሸጥ ከእያንዳንዱ ሽያጭ ትርፍ ወይም ኮሚሽን ይታሰብልናል ማለት ነው፡፡ ብዙ ሰው ይህን ተመራጭ የሚያደርገው ስራውን ለመስራት መነሻ አያስፈልገንም ያማለት ኢንተርኔት እስካለን ድረስ ምንም አይነት የ$ ክፍያ ማድረግ ሳይኖርብን ያመንበት ምርት አስተዋውቀን በመሸጥ በኛ ምክንያት የተሸጡ ምርቶች ትርፍ ላይ ኮሚሽን ይታሰብልናል ማለት ነው፡፡

 

እጅግ በጣም ምርጥ ምሳሌ ለመስጠት ያህል በየኔ ፕላትፎርም ውስጥ የAffiliate marketing ፕሮግራም አዘጋጅተናል፡፡ አንደኛው

1/ የኔ ዌቭሳይት ኮም በማለት Affiliate marketing ላይ በመመዝገብ አባል መሆን ትችላላችሁ፡፡

2/ የተለያዩ የሶሻል ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ዌቭሳይት ያስፈልጋቸዋል ብላችሁ የምታምንቱን ግለሰብ ወይም ድርጅት መልዕክት በመላክ እናንተ ዌቭሳይት በ16 ቀናት ውስጥ አሰርታችሁ እንደምታቀርቡ ማሳወቅ፡፡

3/ የሚመጣላችሁን የተለመዱ ጥያቄዎች ለምሳሌ ዋጋ፣ ከዚህ በፊት የሰራችሁት ድረገፅ ምሳሌ ስትጠየቁ በመመለስ እና የየኔ ዌቭሳይት ማርኬቲንግ አባላት እንደሆናችሁ በማስረዳት እነሱ ክፍያ እያደረጉ የ15% ኮሚሽን እናንተ ተከፋይ ትሆናላችሁ ማለት ነው፡፡



3ኛ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን ገንዘብ መስራት የምንችልበት አማራጭ

Drop shipping፡- ይሄኛው አማራጭ እጅግ በጣም አስደሳች እና ትርፋማ የሚያደርግ አማራጭ ነው፡፡ ከ2ዐ13 – 2015 ዓ.ም ሀገራችን ላይ በጣም ትርፋማ የሚሆን ድርጅትን አቀርባለሁ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ አሁን ላይ ግን ይህን አተረፍኩ የምላችሁ ውጤት የለም፡፡

Drop shipping፡- ማለት አንድን ምርት ከድርጅቱ ወይም ከአከፋፋዮች በስማማት Amazon እና የመሳሰሉት ድረገፆች ላይ ከፍ ባለ ዋጋ መሸጥ ማለት ነው፡፡

 

ለምሳሌ ያህል፡- ከቻይና Alibaba.com ላይ አንድ ጫማ መርጠን USA ወይም የመረጥነው ቦታ ላይ በጥሩ ሁኔታ እንደሚሸጥ ያመንበትን ጫማ ከአቅራቢው Drop shipping ስምምነት ከወሰድን በኋላ Amazon ላይ ገብተን ከፍ ባለ ዋጋ መሸጥ እንችላለን፡፡

 

ይሄን ሁሉ ስናደርግ ቻይናም ሆነ ሌላ የዓለማችን ክፍል ላይ በቦታው መገኘት አያስፈልግም፡፡ ሁሉንም ቤታችን ውስጥ ኢንተርኔትን በመጠቀም የምንሰራው ነው፡፡

 

Amazon ላይ አብዛኞችን የምንሳሳተው Amazon ምርቶችን የሚሸጥ ይመስለናል፡፡ ወይም ምርቶችን በመግዛት ለኛ የሚያቀርብ ይመስለናል፡፡ ነገር ግን Amazon ላይ የሚሸጡት ምርቶች ከ6ዐ% በላይ የሚሆኑት በግለሰቦች ልክ እንደ እኔና እንደኛነት ባሉት ሰዎች ነው፡፡

 

ይሄ ሲባል Amazon በራሱ አምርቶም ሆነ ገዝቶ የሚሻጣቸው ምርቶች የሉም ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን Amazon ላይ የሚካሄዱት ግብይይቶች አብዛኞች በግለሰቦች ነው፡፡ በቀላሉ አካውንት በመፍጠር አሁኑኑ ምንም ምርት ሳይኖረን የአምራቾችን ምርት በመሸጥ ትርፋማ መሆን እንችላለን፡፡ ይህን ስራ የሚሰሩ Amazon ላይ ብቻ ከ5,ዐዐዐ,ዐዐዐ በላይ ሰዎች አሉ፡፡

1ኛ. በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ምርቶች ውስጥ እኛ በቀላሉ አግባብተን መሸጥ የምንችለውን ምርት መምረጥ፡፡

2ኛ. የራሳችንን ዌብሳይት ለምርቱ በመፍጠር ተጠቃሚዎች እኛ ባስቀመጥነው ዋጋ መሰረት እንዲገዙ ማመቻቸት ወይም የኢንተርኔት ሱቅ መቅርት፡፡

3ኛ. ሱቃችንን በተለያዩ ማህበራዊ ገፆች በማስተዋወቅ ተጠቃሚዎች ከኛ ድርገፅ እንዲገዙ ማድረግ፡፡

4ኛ. ክፍያውን እንደፈፀሙ የኛ ተጠቃሚዎች እኛ ምሩትን ማየት ሳይኖርብን እነሱ እጅ ከአቅራቢዎች ወይም አከፋፋዮች ይደርሳቸዋል ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ይህን ስራ ለመስራት እንዲሁ ፍቅሩ ላላችሁ ኃይለአብ ያገርሰው በሚል ቻናል ደረጃ በደረጃ በዋነኝነት የሚያሳይ ቪዲዮ ዩ ቲዩብ ላይ አቀርብላችኋለሁ ስለዚህ መከታተል ትችላላችሁ፡፡ ው ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን ኢንተርኔት በመጠቀም ልንሰራው የምንችለው ስራ፡-

Free lancing:- ይህም ማለት ያለንን ችሎታዎች በመጠቀም ወይም በቀላሉ ልንማራቸው የምንችላቸውን ችሎታዎችን በመማር መስራት የምንችለው ነው፡፡

ለምሳሌ፡-


  • Graphics design 
  • Branding
  • Video photo editing
  • Photography & video graphy
  • Software development
  • Marketing
  • Advertising
  • Copy writing
  • ስማችንን ሶሻል ሚዲያ ላይ ተደራሽ ማድረግ፣
  • ኮንቴንት ወይም ተመልካችን ወደ ደንበኛ የሚቀይሩ ይዘቶችን ፖስት ማድረግ፣
  • ማስተዋወቅ እና ትኩረት ማግኘት ብለን እንክፈላቸው፡፡

እና የመሳሰሉትን ት/ት በመማር በሌሎች ሰዎት ማቅረብ ነው፡፡ ቀላል ምሳሌ ለመስጠት ያህል የሀገራችን አዘጋጆች ከቴሌቪዥን ይልቅ ዩ ቲዮቨርን ተመራጭ ስላደረጉ ለነሱ የግራፊክስ ዲዛይን በመስራት እናም እነዚህ ዩ ቲዮቨርስ እራሳቸው ስለሆኑ ቪዲዮችን የሚሰሩት ማለትም ከቀረፃ ጀምሮ ኢዲት እና መልቀቅን ጨምሮ እራሳቸው ስለሆኑ ለነሱ ኢዲት በማድረግ ባለንበት መስራት እንችላለን፡፡

 

ይህኛውን አማራጭ ዓለም አቀፍ በሆነ ደረጃ መስራት ለምትፈልጉ Freelancer እና Fiverን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ ሀገራዊ የሆኑ መፍትሔዎችን ብንከተል ምርጫየ ነው ምክንያቱም ተከፋይ የምንሆነውም ከፍለው ተጠቃሚ የሚሆኑትም ኢትዮጵያዊያን ስለሆን አብሮ መስራትን ይጨምትልናል፡፡ በነዚህ ዓለም አቀፍ አማራጮች ተጠቅመን ሎጐ በመስራት ቪዲዮ ኢዲት በማድረግ እና በርካታ ስራዎችን በመስራት ተከፋይ መሆን እንችላለን፡፡፡

 

ከፍተኛ ውድድር ስላለው የሚገባንን ያህል የሚከፍለን ሰው ላናገኝ እንችላለን፡፡ ነገር ግን የግላችንን የስራ ዌቭሳይት ወይም ድረገፅ Build ወይም በመገንባት ካሉት ተወዳዳሪዎች የበላይ መሆን እንችላለን፡፡ ኢንተርኔት ላይ ስራዎችን በቋሚነት ለመስራት የሚፈልግ ሰው ድረገፆችን እንዴት መገንባት እንዳለበት ማወቅ አለበት ስለሱም በዛኛው ቪዲዮ እናመራለን፡፡

 

2ኛው ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን ብዙ ገንዘብ መስራት የምንችልበት መንገድ፡-

Selling ወይም መሸጥ ነው ይህንንም በ2 ከፍለን እንየው፡-

አንደኛው 1.አዘጋጅቶ መሸጥ ሲሆን ሁለተኛውን ደሞ መግዛት ከዛ አትርፎ መሸጥ በሚል እንየው

 አሁን ላይ ያለው የኢንተርኔት ግብይይት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ሰው ጣሊያን የሚገኝን ምርት ገዝቶ ብራዚል ላይ ላለ ሰው መሸጥ አስችሎታል፡፡ ይህም ሲባል ከጣሊያን ወደ ኢትዮጵያ፣ ከኢትዮጵያ ወደ ብራዚል ሳይሆን በቀጥታ ከጣሊያን ወደ ብራዚል መሸጥ ማስቻሉ ይበልጥ የንግዱን ዓለም አዘምቶታል፡፡ ለዚህም ነው መረጃ ከምንም በላይ ገንዘብ የሆነበት ጊዜ ላይ የደረስነው፡፡ ምክንያቱም ብራዚል የሚገኘው ሰው እሱ የሚፈልገው ምርት ጣሊያን እንደሚመረት ወይም እዛ እንደሚከፋፈል መረጃው ካለው በቀጥታ ከዛ በመግዛት እና የተሻለ ዋጋን ማግኘት ይችላል፡፡ ነገር ግን እኛ ኢትዮጵያዊያን ይህን መረጃ ከሱ በፊት ካወቅን በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ ድረገፅን በመፍጠር ብራዚልም ሆነ ካናደ ላለ ሰው መሸጥ እንችላለን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ በዘመናችን ከምርቱ ይልቅ መረጃው ገንዘብ ነው ማለት ነው፡፡


አሁን መግዛት ከዛ አትርፎ መሸጥ የሚለውን እንይ፡-


ይህ ቅድም ካነሳነው Drop shipping አማራጭ ጋር ተመሳሳይ ቢመስልም እጅግ በጣም ብዙ ልዩነት አለው፡፡

በዋነኝነት የሚለየውም በዚህኛው አማራጭ የትርፍ መጠናችን እጅግ በጣም ከፍ ያለ ሲሆን የኪሳራችንም መጠን ከፍ ያለ ነው፡፡ ስራውን ለመጀመረም ከፍተኛ የሚባል ገንዘብ ማለትም ከ5ዐዐ$ ጀምሮ እስከ 1ዐዐ,ዐዐዐ$ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አምራቾች ሊያስገርመን በሚችል ሁኔታ ዝቅተኛ ዋጋን ይሰጡናል በግልባጩ ደግሞ ባንዴ ብዙ ምርትን እንድንገዛ ይፈልጋሉ፡፡ ለምሳሌ አንድ የፀጉር ቅባት በጣም ተወዳጅ እና ጠቃሚ በመሆኑ ምክንያት 45ዐ$ የሚሸጥ ቢሆን የዚህ አከፋፋዮች ለኛ ምን አልባት በ127$ ሊሸጠሉን ይችላሉ ያን የሚያደርጉበት ምክንያት ግን በስቶክ ደረጃ ማለትም ለምሳሌ 5,ዐዐዐ ቅባቶችን ባንዴ ስንገዛ ነው፡፡ ይህም ማለት፡- 5,ዐዐዐ ቅx127= 635,000$

 

ስለዚህ የ127 ብር ዋጋ ለማግኘት 635,000$ 5ዐዐዐ ቅባቶችን መግዛት ይኖርብናል ማለት ነው፡፡ ቅድም እንዳልነው ይህ ቅባት 45ዐ$ የሚሸጥ ከሆነ የራሳችንን ድረገፅ በቀላሉ በመገንባት ያሉንን 5ዐዐዐ ቅባቶች ሱቆች ላይ ከሚሸጥበት የ45ዐ$ ዋጋ ዝቅ በማድረግ በ4ዐዐ$ ብንሸጥ በፍጥነት እነዚህን ቅባቶች 4ዐዐ$x5,ዐዐዐ = 2 ሚሊዮን$ ግሮስ ረቬኑ ወይም አጠቃላይ ሽያጭ ማድረግ እንችላለን፡፡ ትርፋችንም 2m - 635,000$ 1,365,ዐዐዐ$ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ለተለያዩ ወጭዎች ማለትም ድረገፆችን ለማስተዋወቅ እና ሌሎች ወጭዎች 2ዐዐ,ዐዐዐ ወይም 1ዐዐ,ዐዐዐ ልናወጣ እንችላለን ያ ማለት በአማካይ ከ1m$ በላይ ማትረፍ እንችላለን፡፡

 

ይህ ሲባል የዚህ የቅባት ዋጋ በተለያዩ ምክንያቶች ከፍም ዝቅም ሊል ስለሚችል ነው፡፡ በጣም ሠፊ ትርፍ ወይም ሠፊ ኪሣራ የምናይበት ለዚህም ሲባል ገዝተን ልንሸጥ ስለምንችለው ነገር ዕውቀት ሊኖረን ይገባል፡፡ ልብሶች ከሆነ ለመሸጥ ያሰብነው ስለ ፋሽን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ኤሌክትሮኒክ ከሆነ ዕውቀት ያስፈልገናል፡፡ ፊልሞችን ከሆነ ገዝተን የምንሸጠው በተመሳሳይ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ተመራጭ እና ብዙ ተመልካች ይኖረዋል ወይስ አይኖረውም የሚለውን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

 

አንድ አንድ ሰዎች በተፈጥሮ ነገሮችን በርካሽ ገዝተው አትርፈው መሸጥ ይችላሉ ለምሳሌ ት/ትቤት ላይ አንድ አንድ ልጆች እነሱ ሰፈር ብቻ ያለ ነገርን ወይም ለየት ያለ ነገርን በማምጣት ሱቁ ላይ ከገዙበት ዋጋ ጨምረው መሸጥ ይችላሉ ለተማሪዎች፡፡ እናም ተመሳሳይ ዝንባሌ ወይም የማሳመን ችሎታዎች ላላቸው ሰዎች ከ1,ዐዐዐ$ አለፎ አልፎ ከ5ዐዐ$ መነሻ በመጀመር ስራውን መስራት ትችላላችሁ እንዴት የሚለውን ለማወቅ ዮቲዩቭ ላይ ቪዲዎችን እንደናንተ ጥያቄ መሰረት አቀርብላችሁአለሁ፡፡ ስለዚህ በዛው እንገናኝ፡፡

 

ነገረ ግን እኔ ይሄን ስራ ለመስራት ችሎታው የለኝም ሞክሪያለሁ ነገር ግን ገዝቶ መሸጥ ላይ በጣም ደካማ ነኝ በተለይ ከዋጋ ጋር በተያያዘ ምክኒያቱም እኔ የገዛሁበትን ዋጋ ውስጤ ላይ ደጋግሜ ስለማስብ በመሸጥ ሂደት ላይ የማሳመን ችሎታው የለኝም፡፡

 

ሁለተኛውን የመሸጥ ዓይነት እንይ፡-

መስራት መሸጥ በግልባጩ እዚህ ላይ ባለ ሙሉ እምነት ነኝ፣ የተለያዩ የእጅ ስራዎችን እና ማንኛውም ፈጠራ የሚያስፈልጋቸው ስራዎች ላይ ዋጋ ለመናገርም ሆነ ለማሳመን አልቸገረም ምክንያቱም ስራው ሙሉ በሙሉ እራሴ ስለሰራሁት ያስፈለገውን ወጭ ጊዜ እና ጉልበት ግምት ውስጥ በማስገባት ተመጣጣኝ ዋጋን እና አሳማኝ የሆነ አቀራረብን ማቅረብ እችላለሁ እንደእኔ ከሆነ ይህኛው በጣም ጥሩ አማራጭ ነው፡፡

 

ምሳሌዎችን ለመስጠት ያህል ማፃህፍት ማሳተም ሳይኖብን ኢንተርኔት ላይ በመሸጥ ትርፍ መሆን እንችላለን፣ ድረገፅን በመስራት የስጦታ ዕቃዎችን፣ ፕሮዳክት ወይም የድምፅ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት እና መሸጥ ሀገራዊ ግራፊክስ ዲዛይን የሚሸጥበት ድረገፅን በመስራት ለማስታወቂያ እና ለሌሎች ጥቅሞች የሚውሉ ዲዛይንስ መስራት እና መሸጥ፣

 

በተመሳሳይ ድረገፆችን በመክፈት ፎቶግራፊክ ለሆዎች ፎቶ እና ቪዲዮችን ለተለያዩ ዓላማዎች መሸጥ፣ የተለያዩ የሀገራችን መጽሐፍት ፀሐፊዎችን በማናገር Avdiobooks ወይም የድምፅ መፃሕፍትን ማዘጋጀት፣ እነዚህ መፃህፍት ለአይነስውራን ብቻ ሳይሆኑ ለማንኛውም ሰው በመኪናዎች ስልካችን ላይ በመጫን ልናደምጣቸው የምንችላቸው መጽሐፍት ስለሆኑ ዋጋቸውም ከፍ ያለ ነው፡፡ ስለዚህ እነሱን በማዘጋጀት እና በመሸጥ ውጤታማ መሆን ይቻላል፡፡

 

===

ወደ ርዕሱ እንመለስ እና መስራት ከዛ መሸጥ የምንለው የስራ አይነት በጣመ በግሌ የምወድበት ምክንያት በዝግጅት ወቅት ምንም አይነት ገቢ ባይኖረውም በጥንቃቄ እና ሰዎችን ለመጥቀም ካዘጋጀነው አንዴ ሰርተነው ለዘመናት ልንከፍልበት እንችላለን ይህም ማለት ቀላል የሆነውን የመፃሕፍትን ምሳሌ ስንሰጥ ስናዘጋጀው ማንም የሚከፍለን አይኖርም፡፡ ነገር ግን ከዝግጅት በኋላ የባለቤትነት መብታችንን እስካልሸጥን ድረስ በታተመ ቁጥር ገቢ የሚያስገኘን ይሆናል ማለት ነው፡፡




1ኛው ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን ገንዘብ መስራት የምንችልበት አማራጭ

Drop shipping፡- ይሄኛው አማራጭ እጅግ በጣም አስደሳች እና ትርፋማ የሚያደርግ አማራጭ ነው፡፡ ከ2ዐ13 – 2015 ዓ.ም ሀገራችን ላይ በጣም ትርፋማ የሚሆን ድርጅትን አቀርባለሁ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ አሁን ላይ ግን ይህን አተረፍኩ የምላችሁ ውጤት የለም፡፡

Drop shipping፡- ማለት አንድን ምርት ከድርጅቱ ወይም ከአከፋፋዮች በስማማት Amazon እና የመሳሰሉት ድረገፆች ላይ ከፍ ባለ ዋጋ መሸጥ ማለት ነው፡፡

 

ለምሳሌ ያህል፡- ከቻይና Alibaba.com ላይ አንድ ጫማ መርጠን USA ወይም የመረጥነው ቦታ ላይ በጥሩ ሁኔታ እንደሚሸጥ ያመንበትን ጫማ ከአቅራቢው Drop shipping ስምምነት ከወሰድን በኋላ Amazon ላይ ገብተን ከፍ ባለ ዋጋ መሸጥ እንችላለን፡፡

 

ይሄን ሁሉ ስናደርግ ቻይናም ሆነ ሌላ የዓለማችን ክፍል ላይ በቦታው መገኘት አያስፈልግም፡፡ ሁሉንም ቤታችን ውስጥ ኢንተርኔትን በመጠቀም የምንሰራው ነው፡፡

 

Amazon ላይ አብዛኞችን የምንሳሳተው Amazon ምርቶችን የሚሸጥ ይመስለናል፡፡ ወይም ምርቶችን በመግዛት ለኛ የሚያቀርብ ይመስለናል፡፡ ነገር ግን Amazon ላይ የሚሸጡት ምርቶች ከ6ዐ% በላይ የሚሆኑት በግለሰቦች ልክ እንደ እኔና እንደኛነት ባሉት ሰዎች ነው፡፡

 

ይሄ ሲባል Amazon በራሱ አምርቶም ሆነ ገዝቶ የሚሻጣቸው ምርቶች የሉም ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን Amazon ላይ የሚካሄዱት ግብይይቶች አብዛኞች በግለሰቦች ነው፡፡ በቀላሉ አካውንት በመፍጠር አሁኑኑ ምንም ምርት ሳይኖረን የአምራቾችን ምርት በመሸጥ ትርፋማ መሆን እንችላለን፡፡ ይህን ስራ የሚሰሩ Amazon ላይ ብቻ ከ5,ዐዐዐ,ዐዐዐ በላይ ሰዎች አሉ፡፡

1ኛ. በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ምርቶች ውስጥ እኛ በቀላሉ አግባብተን መሸጥ የምንችለውን ምርት መምረጥ፡፡

2ኛ. የራሳችንን ዌብሳይት ለምርቱ በመፍጠር ተጠቃሚዎች እኛ ባስቀመጥነው ዋጋ መሰረት እንዲገዙ ማመቻቸት ወይም የኢንተርኔት ሱቅ መቅርት፡፡

3ኛ. ሱቃችንን በተለያዩ ማህበራዊ ገፆች በማስተዋወቅ ተጠቃሚዎች ከኛ ድርገፅ እንዲገዙ ማድረግ፡፡

4ኛ. ክፍያውን እንደፈፀሙ የኛ ተጠቃሚዎች እኛ ምሩትን ማየት ሳይኖርብን እነሱ እጅ ከአቅራቢዎች ወይም አከፋፋዮች ይደርሳቸዋል ማለት ነው፡፡

ስለዚህ ይህን ስራ ለመስራት እንዲሁ ፍቅሩ ላላችሁ ኃይለአብ ያገርሰው በሚል ቻናል ደረጃ በደረጃ በዋነኝነት የሚያሳይ ቪዲዮ ዩ ቲዩብ ላይ አቀርብላችኋለሁ ስለዚህ መከታተል ትችላላችሁ፡፡



አሁን ደሞ እኔ ስለመረጥኩት እና ሙሉ ጊዜየን ሰጥቼ የምሰራዉን አማራጭ ልንገራችሁ


እኔ የተጠቀምኩበት አማራጭም ////// ዌቭሳይት ወይም ድረገፅ መስራት ነው፡፡ ቆይ ታዲያ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ካልተማርን እንዴት እኛ ድረገፆችን መስራት እንችላለን፡፡ ብዙ የኮምፒዩተር ብቃት ከሌለንስ እንዴት ድረገፆችን በመስራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንዘብን መስራት እንችላለን? ለነዚህ ጥያቄዎች መፍትሔ የሚሆን ለእናንተ ምርጥ አማራጭን ይዤላችሁ መጥቻለሁ፡፡ የኔ ዌቭሳይት ኮርስ

 

መጀመሪያ እንደነገርኳችሁ በነዚህ ሁለት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን ኢንተርኔት ተጠቅመን ስራ መስራት የምንችልበትን ሳፈላልግ ስሞክር ነበር፣ ያለምንም ማቋረጥ ያሉትን አማራጮች ተመልክታችሁ እናም ድረገፆችን መስራት ሀገራችን ላይ ለመስራት እስከተነሳን ድረስ ብዙ የስራ ዕድል ያለበት ሀገር ናት፡፡

 

ትልቁ ፈተና ግን ድረገፆችን ለመስራት በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ፕሮግራሚኒግ languages ወይም የተለያዩ frameworks ማጥናት ይኖርብናል፡፡ በውስጡም ብዙ librarips መሸምደድ እና ወደ ማቲማቲክስ ያጋደለ በመሆኑ ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስድ መሆኑ ነው፡፡ ከጊዜ ፍለጋ በኋላ እጅግ በጣም በቀላሉ ምንአልባት 15 ደቂቃ ብቻ የሚወስዱ ድረገፆችን የመስሪያ አማራጮችን አገኘሁ እነዚያ ደግሞ የራሳቸው ድክመት አለባቸው፡፡

 

አንደኛው፡- ችግር የሚቀርፍ ድረገፅን መስራት አያስችሉንም ምክንያቱም እጅግ በጣም ውስንነት ስላለባቸው እጅግ በጣም የተለመዱ እና ልዩ ጥቅም የማይሰጡ ድረገፆችን ብቻ ነው መስራት የሚያስችሉን፡፡

 

ሁለተኛው፡- በአመት ወይም በወር የምንከፍለው ክፍያ እጅግ በጣም የተጋነነ እና ውድ መሆኑ ከምንም በላይ ደግሞ ክፍያውን መፈፀም አንችልም ምክንያቱም ሀገራችን ላይ ክሬዲት ካርድ ወይም ሌሎች ዓለም አቀፋዊ ክፍያን ማድረግ የሚያስችል ባንክ ባለመኖሩ ቢወደድም መክፈል አለመቻላችን እነዚህን አማራጮች ውድቅ ያደርጋቸዋል፡፡

 

ከጊዜ በኋላ በቀላሉ ድረገፆችን መስራት የሚያስችል አማራጭን አገኘሁ ይህም አማራጭ ዓለም አቀፋዊ ተወዳጅነት ያገኘ ሲሆን ኢንተርኔት ላይ ያሉት ድረገፆች ከ37% በላይ የሚሆኑት የሚሰሩበት አማራጭ ነው፡፡ ለመማር እጅግ በጣም እና አስደሳች በሆነ መንገድ ሁሉንም ሂደት ኢትዮጵያዊ አማራጮችን 1ዐዐ% ታሳቢ በማድረግ አንድ ኮርስ ይዤላችሁ መጥቻለሁ፡፡ በዚህ ኮርስ ማንኛውንም ዓይነት ድረገፅ በቀልጣፋ መንገድ የምትሰሩበት ት/ት ሲሆን ከምንም በላይ ግን ከተለመደው የመማር ማስተማር ሂደት ወጣ ባለ መልኩ ዘና ብላችሁ የምትማሩበትን ኮርስ ነው ያዘጋጀሁላችሁ፡፡ ገንዘብ ለመስራት ብቻ ሳይሆን በትክክል ሀገራችን ላይ ያሉትን ችግሮች መቅረፍ በሚያስችል ሁኔታ የምትማሩበት ይሆናል፡፡

 

ማስታወስ ያለብን ይህ ኮርስ በአቋራጭ ብዙ ገንዘብ የምናገኝበት መንገድ አይደለም ይልቁንም መስራት የሚያስፈልገው እና ት/ቱንም መማር የሚያስፈልግ ነው፡፡ ያላችሁን ጥያቄዎች የምናይበት ክፍልና ሙሉ በሙሉ ሊኖራችሁ ስለሚችሉ ጥያቄዎች በክፍል 2 እናያለን ፡፡ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድባችሁ ከተማራችሁስ በኋላ በቀላሉ ምን ምን መስራት እንደምትችሉ በክፍል 2 እናያለን። 


Report Page