*/

*/

Source

አትላስ የተሰኘ ፕሮጀክት 12 አዳዲስ የውሃ ውስጥ ፍጥረታትን ማግኘቱን አሳወቀ
************************************************** በፕሮጀክቱ ውስጥ የሚሰሩ ተመራማሪዎች ለሳይንሱ ዓለም አዲስ የሆኑ 12 የውሃ ውስጥ ፍጥረታትን ማግኘታቸውን አሳውቀዋል፡፡ ይህ በአውሮፓ ህብረት የሚደገፍ የውሃ ውስጥ ፕሮጀክት ላለፉት አምስት አመታት ከ45 በላይ ፍለጋዎችን ወደ 80 በሚደርሱ ተመራማሪዎችና ፈቃደኛ ተማሪዎች አማካኝነት ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት በአለማችን ካሉት የውቅያኖስ ላይ ተቋማት መካከል እጅግ ግዙፉ ለመሆን የበቃው ይህ ፕሮጀክት የሰሜን አትላንቲክን ውሃ፣ ጥልቅ የመሬት ክፍል፣ ፍሰት እና በዋናነት በውስጡ የያዛቸውን ፍጡራን ለማጥናት የተቋቋመ ነው፡፡ ከ13 ሀገራት የተውጣጡት ተመራማሪዎች ፕሮጀክቱን ሲጀምሩ ውቅያኖሱ በአለም ሙቀት መጨመር ምክንያት ያመጣውን ለውጥ አጥንተዋል፡፡ የምርምሩ አብዛኛው ስራ የተከናወነው የውሃ ውስጥ ሮቦቶችን በመጠቀም ሲሆን 12ቱ አዳዲስ የውሃ ውስጥ ፍጡራን የሚገኙበትን ጥልቁን የውቅያኖሱን ክፍል ማጥናት ከፍተኛውን ጊዜ ወስዶበታል፡፡ ተመራማሪዎቹ በምርምራቸው ማብቂያ ላይ በሰጡት መግለጫ ስለ ጥልቁ የውቅያኖስ ክፍል ከታወቀው ይልቅ ስለጨረቃና ስለ ማርስ የታወቀው ይበልጣል በሚል ንጽጽር የውቅያኖስ ክፍሎች ትኩረት እንደተነፈጋቸው ተናግረዋል፡፡ ተመራማሪዎቹ በተጨማሪም የግሪን ሀውስ ጋዞች በውቅያኖሶች ላይ እያመጡት ያለውን ተጽዕኖ የተመለከቱ ሲሆን የዚህ አይነቱ ተጽእኖ የውሃ ውስጥ ፍጥረታትን ህልውና ስጋት ላይ እንደጣለው ተናግረዋል፡፡ ይባስ ብሎም የውቅያኖሱ ፍሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ እንደመጣም በምርምራቸው ማረጋገጣቸውን ተመራማሪዎቹ አሳውቀዋል፡፡

ምንጭ

1 hour ago · Public · in

Report Page