*/

*/

Source

4. ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ ቅዱስ እንድርያስ የቅዱስ ጴጥሮስ ወንድም ሲሆን በዓሣ ማጥመድ ተግባር ላይ ሳለ በጌታ ቃል በመጀመሪያ የተጠራ ሐዋርያ ነው ። ዮሐ 1 : 35 - 45 ጌታን ከመከተሉ በፊት የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀመዝሙር ነበር ።

ቅዱስ እንድርያስ መጀመሪያ የሰብከት ሥራውን በፍልስጥኤም ጀመረ ፤ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ የነበረው አውሳብዮስ እንደገለጸው እንድርያስ በሩሲያ ወንጌልን ሰብኳል ፤ ቀጥሎም በቢታንያ ፣ በገላትያ ፣ በሩማንያ ፣ በመቄዶንያ ፣ በታናሽ እስያ ፣ በግሪክ ወንጌልን አስተምሯል ። የቁስጥንጥንያን ቤተ ክርስቲያን የመሠረተውና የቁስጥንጥንያ የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳስ መሆኑ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይነገራል ፤ በመጨረሻም ግሪክ ውስጥ ምትራ በምትባል ሀገር ሲያስተምር ጣኦት አምላኪዎች የ " X " ቅርጽ ባለው መስቀል ላይ ሰቅለውና በድንጋይ ወግረው ታኀሣሥ 4 ቀን በ60 ዓ.ም በሰማዕትነት አርፏል ፣ ጸሎትና በረከቱ በሁላችን ላይ ይደር አሜን ።

Feb 17, 2016 · Public · in

Report Page