*/
Sourceየቤኒሻንጉል ጉምዝ ምክር ቤት አባላት በዛሬው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ ያነሷቸው ነጥቦች
• በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በተጀመረው የህግ የበላይነትን ማስከበር ሥራ አጥፊዎችን አሳልፈን እንሰጣለን፣
• ለሰላም መስፈን አስፈላጊውን መስዋዕትነት እንከፍላለን፣
• የመተከልን ግጭት ለመፍታት ከተቋቋመው ኮማንድ ፖስት አባላት ውስጥ አንዳንዶቹ ሃላፊነታቸውን አልተወጡም፣
• የመተከል ጉዳይ ገና ብዙ አመራሮችን ይነካል፤ የህዝብ ጉዳት ሊያመን ይገባል፣
• ካማሽ እና አሶሳ ዞን የተፈጠረውን ችግር በመገምገም በቀላሉ መፍታት ችለናል ነገር ግን የመተከል ችግር ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከድምጸ ወያኔ ቴሌቪዥን ጋር ሲሰሩ ስለነበረ ሳይፈታ ቆይቷል፣
• በመተከል ጥቃት በአከባቢው የሚኖር ሁሉም ብሔር ተጎድቷል፣
• ችግሩን ለመፍታት በብሄራችን ተከልለን መከራከር ሳይሆን እንደአገር በማሰብ ልንሠራ ይገባል፣
• ዛሬ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳባቸው የምክር ቤቱ አባላት ጉዳይ ቀደም ሲል በተደጋሚ መፍትሔ እንዲሰጠው ጠይቀናል፤ ችግሩ ሰሚ በማጣት ጠይቋል፣
• የመተከልን ጥቃት በማስቆም ህዝብ እና አገርን ከአጥፊዎች ለማዳን የጋራ ርብርብ ያስፈልገናል፣
• በክልሉ ምክር ቤት የጁንታውን ሴራ የሚያራምዱ አባላት አሉ፣
• በዞኑ የጸጥታ ሀይሉን ሥራ ውጤታማ ለማድረግ ሌሎች ቀሪ የግጭቱ ተሳታፊ የምክር ቤት አባላትም ካሉ እየፈተሽን ለህግ ካላቀረብን የመተከልን ችግር መፍታት ያዳግተናል፣
• በአካባቢው በዋነኝነት እየሞቱ ያሉት ሴቶች እና ህጻናት ናቸው፣
• ህግ የማስከበር ስራን እንደምክር ቤት አባል ማስቀጠል የግድ ነው፣
• የህብረ-ብሄራዊነት ተምሳሌት በሆነው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ በጥቂቶች ጥፋት በመተከል ከማይካድራው ያልተናነሰ ግድያ ተፈጽሟል፣
• እንደህዝብ ተወካይ ከማህበራዊ ሚዲያ ከምናገኘው መረጃ ባሻገር ስለመረጠን ህዝብ በቂ እውቀት ሊኖረን ይገባል፣
• ችግሩ ለክልላችንም ሆነ አገራችንን የሚያሳፍር ጉዳይ በመሆኑ ከጁንታው ጋር አብሮ እንዲቀበር መስራት አለብን፣
• የጸጥታውን ዘርፍ በተደጋጋሚ ገምግመን ችግሩን ብንደርስበትም ተሸፋፍኖ አልፏል፣
• የችግሩ ምንጭ አመራሩ በጉዳዩ መሳተፉ ነው፣
• ህብረተሰቡ በየቦታው ግጭት ሳይከሰት አስቀድሞ ሲጮህ ነበር፣
• ህዝባችንን የምንታደገው በችግሩ የተሳተፉትን የምክር ቤት አባላትን ጭምር አሳልፈን በመስጠት ቆራጥ እርምጃ በመውሰድ ብቻ ነው፣
• በህግ ማስከበር ስራው አንደራደርም፣
• የተጀመረው የህግ የበላይነት ማስከበር ሥራ ተጠናክሮ አጥፊዎችን አሳልፈን እንሰጣለን እንዲሁምአስፈላጊውን መስዋዕትነት እንከፍላለን፣
• ምክር ቤቱ በመተከል ጉዳይ አስቸኳይ ጉባኤ መጥራት ከነበረበት ጊዜ ዘግይቷል፣
• በአስቸኳይ ጉባኤው ያልተገኙ በርካታ የምክር ቤት አባላት አሉ፣
• የመተከል ጉዳይ አሳፋሪ ነው፤ ተጨማሪ ሞት እና መፈናቀል እንዳይከሰት እና ከታሪክ ተወቃሽነት መውጣት አለብን” የሚሉ አንኳር ነጥቦች ተነስተዋል።
ENA