*/

*/

Source

አገልግሎታቸውን የጨረሱ የኤሌክትሮኒክስ ቁሶችና የብክለት ስጋት
*************************************************
የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በምርቶቻቸው ምክንያት የሚመጣን ብክለት ለመቀነስ የሚያስችል ተግባር ተገቢውን ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ እንዳልሆነ ተጠቆመ፡፡ አሁን ወቅቱ እያንዳንዱ የቴክኖሎጂ ተቋም ምርቱን ለአካባቢ ብክለት ምክንያት በማይሆንበት መንገድ ማቅረብ ያለበት ጊዜ እንደሆነ ይታመናል፡፡

አብዛኛዎቹ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በየአመቱ አዳዲስ ምርቶችን ወይም የነበሩትን ምርቶች በማሻሻል ለማቅረብ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ይህ ደግሞ ሰዎች በእጃቸው ያለውን ቁስ በአዲሱ ለመተካት እንዲጓጉ ስለሚያደርጋቸው የአብዛኞቹ ምርቶች አገልግሎት ከሁለት አመት ያለፈ አይደለም፡፡

ለምሳሌ በ2019 ጋርትነር የተባለ ተቋም ባወጣው መረጃ 153 ሚሊዮን ስማርት ስልኮች በሁሉም የአለማችን ክፍሎች ተሽጠዋል፡፡ በየቴክኖሎጂ ቁሶቹ የሚጨመሩ አዳዲስ ማሻሻያዎች ደግሞ ሰዎች ያያዙትን ስልክም ሆነ ሌላ የኤሌክትሮኒክስ ምርት በቶሎ እንዲቀይሩ ያደርጋቸዋል፡፡ በሚገርም ሁኔታ በ2019 ተሸጡ የተባሉት ስማርት ስልኮች የበይነመረብ አገልግሎት ከ4ኛ ትውልድ ወደ 5ኛ ትውልድ እያደገ በመምጣቱ አሁንም በአዳዲስ ምርቶች የመተካት እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡

በአሜሪካ በተሰራ አንድ ጥናት በ2019 ብቻ የተሰበሰበው የኤሌክትሮኒክስ ውጋጅ 6.9 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የሚበልጥ ነው፡፡ ጥናቱን እንደሰራው አለምአቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ውጋጅ ተቆጣጣሪ ድርጅት መረጃ ከሆነ ከተጠቀሰው ቁጥር ውጋጅ ውስጥ 15 በመቶው ብቻ ለድጋሚ አገልግሎት መዋል ችሏል፡፡ ቀሪው በየቦታው የተጣለው ከፍተኛ ብክለት የሚስከትል ነው፡፡

የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የአንድን የኤሌክትሮኒክስ ምርት የአገልግሎት ጊዜ ማራዘም የብክለት መጠኑን ለመቀነስ ሁነኛ መፍትሄ ነው፡፡ ለዚህም ከአምራቾች ባሻገር ተጠቃሚዎችም የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው ይታመናል፡፡
ምንጭ CNBC Technology

Report Page