*/

*/

Source

"የኮሪያ አርቲፍሻል ፀሐይ" አዲስ ክብረ-ወሰን
*********************************** የኮሪያ ሰው ሰራሽ ፀሐይ ለ20 ሴኮንዶች ያክል መቆየት የቻለ የ100 ሚሊዮን ዲግሪ ሙቀት በመያዝ የአለማችን አዲስ ክብረ-ወሰን አስመዝግቧል፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ በሚገኝ አንድ የዘርፉ የምርምር ተቋም (KSTAR) የተሰራው ይህ ሰው ሰራሽ ፀሐይ መቶ ሚሊዮን ዲግሪ ሴልሺየስ የደረሰ ከፍተኛ ሙቀት በመያዝ ለተመራማሪዎቹ ትልቅ ስኬትን አስገኝቷል፡፡ የምርምር ተቋሙ ከሴኡል ብሔራዊ ዩኒቨርሲቲና ከአሜሪካው ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሰራው ይህ ምርምር ለተከታታይ 20 ሴኮንዶች ያክል የቆየ ሲሆን በኒውክሌር ፊውዥን ዙሪያ ለሚሰሩት ጥናት ምቹ ሁኔታ እንደሆነ ተነግሮለታል፡፡ በ2019 በተደረገ ሙከራ የቆይታ ጊዜው ለ8 ሴኮንዶች ያክል ብቻ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን የአሁኑ ሁለት እጥፍ ስኬትን ያስገኘ ነው፡፡ ተመራማሪዎቹ አርቲፍሻል ፀሐይ ሲሉ የሰየሙት ከፍተኛ አስተላላፊ ቁስ የሀይድሮጅን አይሶቶፖችን የያዘ ሲሆን ይህ አዮኖችና ኤሌክትሮኖች የሚለያዩበትን የፕላዝማ ኩነት (state) እንዲፈጠር የሚያደርግ ነው፡፡ አዮኖቹ ከፍተኛ መጠን ባለው ሙቀት እንዲግሉ ይደረጋል፡፡ ምንም እንኳን ከ100 ሚሊዮን በላይ ከፍ ያለ ሙቀትን መያዝ የሚችሉ ሌሎች የፊውዥን ቁሶች ቢኖሩም እስካሁን ከ10 ሴኮንዶች በላይ ሙቀቱን ተቋቁመው መቆየት የቻሉ ግን አልነበሩም፡፡ ይህኛው ሙካራ ሊሳካ የቻለውም የምርምር ተቋሙ የውስጣዊ ግድግዳውን አቅም በማሻሻሉ ሲሆን ለዚህ ያበቃውም ባለፈው አመት የተሰራው ከፍተኛ ሙቀትን መቋቋም የሚችል ቁስ (plasma operation mode) መጠቀሙ ነው፡፡

እንደ ተመራማሪዎች ገለጻ ከሆነ የዚህ ምርምር ዋና አላማ እንከ 2025 ድረስ ከመቶ ሚሊዮን ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ ሙቀትን ለ300 ሴኮንዶች ያክል ማቆየት መቻል ነው፡፡ ፈጠራው ከፍተኛ ሙቀት መቋቋም የሚችል ቁስ በማግኘት የወደፊቱን የኒዩክሌር ማበልጸጊያ መሳሪያ ለማግኘት ያለመ ነው፡፡ መረጃውን ከPHYS.ORG አግኝተነዋል፡፡

36 minutes ago · Public · in

Report Page