*/

*/

Source

“ሀገር ውስጥ ብንሆንም ሃገራችን ናፍቆናል”

- “በህይወት ኖሮ ይህን ማየት ቀላል አይደለም”

ለ30 አመታት በጣሊያን ኢምባሲ ተጠልለው የኖሩት ሁለቱ የቀድሞ የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሌ/ኮለኔል ብርሃኑና ባየህና እና ሌ/ጀነራል አዲስ ተድላ ከሰኞ ጀምሮ ባሉት ቀናት ከኤምባሲው ቅጥር ግቢ ወጥተው በነፃነት ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንደሚቀላቀሉ ተረጋግጧል።

የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ባለስልጣናቱ ከሚገኙበት የጣሊያን ኢምባሲ በስልክ አግኝቶ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ አነጋግሯቸዋል። እነሆ፡

ሌ/ጀነራል አዲስ ተድላ ስለ ራስዎ ጥቂት ይንገሩን? የቀድሞ የጦር ሃይሎች ኢታማዦር ሹም ነበርኩ፡፡ ከዚያ በፊት የኢሰፓ የፖሊት ቢሮ አባል በመሆን አገልግያለሁ። ለብዙ ዓመት በተለያየ ደረጃ ሰርተናል። እኔ የመከላከያ ኮሚቴ ውስጥ ነበር … ደርግ ሲቋቋም የምሰራው። ደርግ ከተቋቋመ በኋላ ደግሞ የኢኮኖሚ ዘመቻ መምሪያ ሲቋቋም በውስጡ ዘጠኝ ዓመት ሰርቻለሁ። በ1980 የኢፊድሪ መንግስት ሲቋቋም ተረጋግጧል። ም/ጠ/ሚኒስትር ሆኜ በማገልገል ላይ ሳለሁ በ1981 መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተከናወነ። ከዚያ ተነስቼ ወደ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሆኜ ሳገለግ ነበር። ተጨማሪ ያንብቡ

የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ =====

አዲስ አድማስ


ፌስቡክ↠
ትዊተር↠
ዩቲዩብ ↠
ቴሌግራም↠

Report Page