*/

*/

Source

ላለፉት 30 አመታት አዲስ አበባ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ ተጠልለው የኖሩትና ዛሬ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በነጻ እንዲለቀቁ የወሰነላቸው ኮለኔል ብርሃኑ ባየህና ሌተናል ጄነራል አዲስ ተድላ ማን ናቸው?

👉 ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህ

በ1928 ዓ.ም በቀድሞው የጎጃም ክፍለ ሀገር ተወለዱ፤

እድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በትውልድ አካባቢያቸው ተከታትለዋል፤

እ.ኤ.አ. በ1959 ሀረር ወታደራዊ አካዳሚ እጩ መኮንንነት ትምህርት ቤት ገብተው እንደተመረቁ ናዝሬት ወደሚገኘው የአየር ወለድ ክፍል ተልከው አገራቸውን አገልገለዋል፤

ከሁለት ዓመት በኋላ በቀድሞው ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ተልከው የሕግ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፤

እአአ በ1967 በሐረር ወታደራዊ አካዳሚ በመምህርነት ያገለገሉ ሲሆን፤ በ1974 የጦር ኃይሎች ማስተባበሪያ ኮሚቴ አባል ሆኑ፡፡

ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህ የሕግ ኮሚቴ ሊቀመንበርና የወታደራዊ አካዳሚ ተወካይ ሆነው ደርግን የተቀላቀሉ ሲሆን፤ እ.ኤ.አ. በሚያዝያ 1976 ወደ ሜጀርነት ከፍ ብለዋል፤

በዚህ ሃላፊነታቸውም እ.ኤ.አ. በ1976 በርካታ የአረብ አገሮችን ተዘዋውረው በማግባባት ታላቅ ስራን አከናውነዋል፤

በኢትዮ ሶማሌ ጦርነት መጀመሪያ ላይ የሶቪዬት ህብረት በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የሰላም ድርድር ለማካሄድ በሞከረችበት ወቅት ኮሎኔል ብርሃኑ አገራቸውን ወክለው መገኘታቸው የህይወት ታሪካቸው ይናገራል፤

እ.ኤ.አ. የካቲት 1977 መጨረሻ ላይ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆነው ተሾመው አገራቸውን አገልግለዋል፤

በተጨማሪም እ.ኤ.አ. በ1988 የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ የጦር እስረኞች እንዲለዋወጡ ያመቻቸውን የኢትዮጵያ ልዑክ መሪም ነበሩ፤

እ.ኤ.አ. ሚያዚያ 19/1983 የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሹመውም አገራቸውን አገልግለዋል፤

እአአ መስከረም 12 ቀን 1984 የኢትዮጵያ ሰራተኞች ፓርቲ የፖሊት ቢሮ አባል ሆኑ፤ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 26 ቀን 1984 የተፈጥሮ አደጋ መከላከል መርጃ ኮሚቴ የእርዳታ ማስተባበሪያ መምሪያ ሊቀመንበር ሆነው ተሾመዋል፤

እ.ኤ.አ. በኖቬምበር 1986 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል፤

እ.ኤ.አ. በጥቅምት ወር 1988 በካቢኔ ሹመት ውስጥ አቶ አማኑኤል አንዲሚካኤል ወደ አሜሪካ ከተለወጡ በኋላ ኮሎኔል ብርሃኑ የክልል ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ፤

👉 ሌተናል ጀኔራል አዲስ ተድላ

በቀድሞው ሸዋ ክፍለ ሀገር በ1936 ዓ.ም እንደተወለዱ የህይወት ታሪካቸው ይናገራል፤

ሌተናል ጀኔራል አዲስ ተድላ በተለያዩ ቦታዎች በከፍተኛ ሲቪል ባለሙያነት አገራቸውን አገልግለዋል፤

እ.ኤ.አ ከ1989 እስከ 1991 ለሁለት ዓመት ያህል የአየር ሀይል አባል ሆነው መስራታቸውንም መረጃዎች ያሳያሉ፤

ኢህአዴግ አገሪቱን በተቆጣጠረበት ከግንቦት ወር 1983 ዓ.ም ጀምሮ ሁለቱም ግለሰቦች በጣሊያን ኤምባሲ ተጠልለው ላለፉት 30 ዓመታት በዚያው ቆይተዋል።

በፍርድ ቤት ተገኝተው ባልተሟገቱበት የፍርድ ሂደት የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለቱ የቀድሞ ባለስልጣናት የሞት ፍርዱ በእድሜ ልክ እስራት በአመክሮ የተቀየረላቸው ሲሆን፤ ዛሬ ደግሞ ፍርድቤት በአመክሮ እንዲለቀቁ ወስኖላቸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በዘመኑ የነበረውን የሁለቱን ባለስልጣናት የሥራ እንቅስቃሴ የሚያስታወሱ ፎቶዎችንም እንዲህ አቅርቦልዎታል።

በመሀመድ ሁሴን

Report Page