*/

*/

Source

[በሕይወት ዘመናችን አንዴ ልናየው የምንችለው አስደሳች ክስተት በታኅሣሥ 12 ይከናወናል]
🌅 በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
🌍 ከዕለት ወደ ዕለት በጣም እየተቀራረቡት የሚገኙት በሥርዓተ ፀሐያችን ካሉት ፕላኔቶች በጣም ግዙፋን የሆኑት የጁፒተርና የሳተርን ታላቁ ግጥጥሞሽ (Great Conjunction) ከ400 ዓመት በኋላ ታኅሣሥ 12 (December 21) ለማየት መላው ዓለም በዝግጅት ላይ ነው።

🌍 የሁለቱ ግጥምጥሞሽ የ20 ዓመት መደበኛ ዑደት ቢሆኑም የ2013 (2020) ልዩ የሚያደርገው፦ 1ኛ) የማያ የዘመን አቆጣጠር ማብቂያ በመሆኑ። 2ኛ) የዓመቷ ዐጭር ቀን የዊንተር ሶልስቲስ መግቢያ መሆኑ። 3ኛ) የሚቀራረቡት በ0.1 ዲግሪ መሆኑ። በዚህ መልኩ ከዚህ በፊት የተቀራረቡት፦

💥ከክርስቶስ ልደት በፊት 7 ዓመት ላይ


💥በአማካይ የዛሬ 800 ዓመት ማርች 5 በ1226 ዓ.ም.
💥በአማካይ የዛሬ 400 ዓመት ጁላይ 16 በ1623 ዓ.ም. ነው።

4ኛ) በዕለቱ ሁለቱም ስለሚጠጋጉ አንድ ብሩህና አንጸባራቂ መስለው በዐይን ስለሚታዩ Christmas Star, Star of Bethlehem (የገና ኮከብ፣ የቤተልሔም ኮከብ) የሚል ሥያሜ እየተሰጣቸው መሆኑ። 5ኛ) ከመቀራረባቸው የተነሣ በአንድ አነስተኛ ቴሌስኮፕ ጭምር በአንድ ላይ ጁፒተር ከ4 ጨረቃዎቹና የሳተርን ቀለበት መታየቱ።

6ኛ) ግማሿ ጨረቃና ማርስ በአጠገብ ሆነው ተጨማሪ ውበት ስለሚሆኑ።

7ኛ) ከዚህ በኋላ በጣም ተቀራርበው ሊታዩ የሚችሉት ከ60 ዓመት በኋላ በጎርጎሮሳዊኑ አቆጣጠር መጋቢት በ2080 ነውና በሕይወት ዘመናችን አንዴ ብቻ የሚያጋጥመን ክስተት በመሆኑ።
8ኛ) በዕለቱ 2017 XQ60 የሚባል ከ35-78 ሜትር ስፋት ያለው በጣሊያን የሚገኘውን የፒሳ ሰገነት የሚበልጥ አስትሮይድ (የሕዋ ዐለት) በሴኮንድ 15 ኪሎ ሜትር፤ በሰዓት 33,554 ማይሎችን እየተምዘገዘገ ምድራችንን ሳይነካ የሚያልፍበት መሆኑ።

🎆 በመሆኑም ይህንን አስደሳች ምሽት ቴሌስኮፕ ያላችሁ በቴሌስኮፓችሁ፤ የሌላችሁ ፀሐይ ከጠለቀች ከ1 ሰዓት በኋላ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በ0.1 ዲግሪ የሚቀራረቡትን ታላላቆቹን ፕላኔቶች እያያችሁ ፎቶ እያነሣችሁ በአድናቆትና በደስታ ሆናችሁ እንድታሳልፉት ሐሳብ አቀርባለሁ።

🌅 አስደሳቹ ነገር ባላገሩ ቴሌቭዥን በቀጥታ ሥርጭት ከ11 ሰዓት ጀምሮ የሚያስተላልፈው ይሆናል። በፎቶው ላይ እንደምታዩት 11 ኢንች የሆነውን ቴሌስኮፕ ለቀጥታ ሥርጭት ዝግጁ አድርገናል። በመሆኑም ይህንን ሰማያዊ ክስተት ለማየት በሰዓቱ ዐይኖች ሁሉ በባላገሩ ቲቪ ላይ ይሆናሉ።

🌅 በባሕር ማዶ ላላችሁ የቀጥታ ሥርጭት ስለሚተላለፍ ሰብስክራይብ አድርገው ይጠብቁን።

🌅 በተጨማሪም ተጠባቂው በአስገራሚ የሥነ ፈለክ፣ የሥነ ማዕድንና በሌሎች አስገራሚ የኢትዮጵያ ሳይንሳዊ ዕውቀት ትንታኔ የተሞላው አንድሮሜዳ ቁጥር 2 በ458 ገጾች ተዘጋጅቶ ለአንባብያን ዝግጁ ይሆናል።

🎆🎆 ብሩህ ቀንና አስደሳች ምሽት ይሁንላችሁ🎆🎆
[ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ያነሣችሁትን ፎቶ በዚህ ፔጅ ላይ እንደልብ መልቀቅ ትችላላችሁ።]

Report Page