*/

*/

Source

ኢንተርፕራይዙ በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ
----------------------------------------------
የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ዘመናዊ እና በቴክኖሎጂ የታገዙ መንገዶችን ለማስፋፈት ከባለድርሻ አካላት ጋር ከሚሰራቸው ስራዎች በተጨማሪ በመንገድ ደህንነት ዙሪያ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ለመንገድ ደህንነት ስኬታማነት የአሽከርካሪዎች ሚና የላቀ በመሆኑ የአመቱ የደህንነት አምባሳደሮች ብሎ ለለያቸውን ደንበኞች እውቅና እና ሽልማት አበርክቷል፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶችን ኢንተርፕራይዝ ስራአስኪያጅ ሙስጠፋ አባሲመን የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ አሽከርካሪዎችን ከመውቀስ ባለፈ የመንገዶችን ጥራት ማረጋገጥ እና የአሰራር ስርዓቱን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ገልጸው፣ ኢንተርፕራይዙ በዚህ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የትራፊክ ደህንነት ባለሙያ የሆኑት ኢንስፔክትር አሰፋ መዝገቡ በኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች በአመት እስከ 40 ሚሊየን ተሽከርካሪዎች እንደሚመላለሱ እና በመንገዶቹ ላይ የተከሰቱ የትራፊክ አደጋዎች ቁጥራቸው አናሳ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሰል የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ቢስፋፉ ፋይዳቸው የላቀ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ለአሽከርካራዎች ክብር በመስጠት እንዲህ አይነት የአውቅና መድረከክ መዘጋጀቱ አሽከርካሪዎቹ በቀጣይ የመንገድ ላይ ስነምግባር ጠብቀው እዲያሽከረክሩ ሞራላቸውን ከፍ ከማድረጉ ባለፈም ለሌሎች ትምህርት የሚሰጥ ነው ሲሉ ዋልታ ያነጋገራቸው ተሸላሚ አሽከርካሪዎች ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል አሽከርካሪዎቹ በፍጥነት መንገዶቹ ላይ የሚስተዋሉትን የመብራት መቆራረጥ እና የእንስሶች ወደ መንገዱ መግባት ለአደጋ ተጋላጭ ስለሚያደርጉ በኢንተርፕራይዙ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶችን ኢንተርፕራይዝ ስራ አስኪያጅ ሙስጠፋ አባሲመን የመብራት ሀይል መቆራረጡ እንደሀገር ካለው የሀይል አቅርቦት እጥረት መሆኑን በማንሳት ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰሩ መሆናቸውን እና የእንስሳቱን እንቅስቃሴ ለመግታትም 21 ጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበራትን በማደራጀት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
(በብዙአየሁ ወንድሙ)

Report Page