*/

*/

Source

የኢትዮ-ሱዳን የባቡር ፕሮጀክት የመጀመሪያው የአዋጭነት ጥናት ቀረበ።

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 08/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢትዮ ሱዳን የባቡር ፕሮጀክት የመጀመሪያው የአዋጭነት ጥናት በካናዳው የአማካሪ ተቋም ሲ ፒ ሲ ኤስ ትራንስኮም (CPCS TRANSCOM limited) በተባለው ድርጅት ቀርቧል።

1 ሺህ 522 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውና አዲስ አበባን ከካርቱም የሚያገናኘው ይህ የባቡር ፕሮጀክት እንዲገነባ በሁለቱ ሀገራት መንግስታት ይሁኝታ ማግኘቱ ይታወሳል።

አዲሱ የባቡር መስመር ፕሮጀክት ከኢትዮጵያ እስከ ፖርት ሱዳን ድንበር ክልል ውስጥ እንዲሁም ቀሪው በሱዳን ድንበር ክልል ውስጥ እንደሚገነባ ታዉቋል።

በመሰረተ ልማት አዋጭነት ጥናት ልምድ ያለዉ ይህ ካናዳዊ አማካሪ ድርጅት የተቀጠረው በአፍሪካ የልማት ባንክ ሲሆን የመጀመሪያውን መሠረታዊ የአዋጭነት ጥናት ዉጤት ሪፖርት በኢትዮ-ሱዳን የባቡር መስመር ላይ ለሁለቱም ሀገራት ማስረከቡ ታውቋል።

የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ ኢኮሚኖያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ጠቀሜታው የጎላ የባቡር መስመር ለመዘርጋት መሆኑን የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ገልፀዋል።

የባቡር ፕሮጀክቱ የሎጅስቲክ ፖሊሊ፣ የብሄራዊ የባቡር ኔትወርክ የኮንስትራክሽን ፍላጎት፣ ዓለም አቀፍ የባህር ትራንስፖርት መስመር እና ቀጣይነት ያለው ማህበራዊ እና ኢኮሚያዊ እድገትን መሰረት ያደረገ ነው። ምንጭ-የትራንስፖርት ሚኒስቴር

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ
በዌብሳይት
በቴሌግራም
ትዊተር

Report Page