*/
Sourceከእለታት አንድ ቀን አንድ ሙሥሊም ያልሆነ ሰው ሙሥሊም የሆነን ሰው እቤቱ ተቀብሎ አስተናገደ።
ከዚያም ሰውዬው ለሙሥሊሙ ወይን አቀረበለትና ሙሥሊሙም ወይኑን በላ። በመቀጠልም የወይን ጠጅ አቀረበለት፤ ከዚያም ሙሥሊሙ እንዲህ አለው፡- ሙሥሊሙ፡- “ይህ እኛ ላይ እርም (ሀራም) ነው” አለው። ሰውዬውም፡- “እናንተ ሙሥሊሞች ትገርማላችሁ፤ ይህን ሀላል ታደርጋላችሁ ይህን ደግሞ ሀራም ታደርጋላችሁ። ሆኖም ግን ይህ ወይን ጠጅ የተሰራው ከዚሁ ከበላኸው ወይን ነው” አለው። ሙሥሊሙ፡- “ሚስት አለህ?” አለው ሰውዬው፡- “አዎን” አለው ሙሥሊሙ፡- “አምጣልኝ” አለውና አመጣለት፤ በመቀጠልም “ሴት ልጅ አለህ?” አለው ሰውዬው፡- “አዎን” አለው ሙሥሊሙ፡- “እሷንም አምጣልኝ” አለውና አመጣለት። ከዚያም ሙስሊሙ እንዲህ አለው:- “አየህ ይህችን ሚስትህን አላህ ልታገባት ሀላል አደረገልህ፤ ይህችን ልጅህን ግን ልታገባት ሀራም አደረገብህ። ሆኖም ግን ይህቺ ልጅህ ከዚህች ሚስትህ ነው የተፈጠረችው” አለው። ሰውዬው፡- “አሽሃዱ አንላኢላሃ ኢለላህ ወአነ ሙሐመደን ረሱሉላህ” በማለት ኢሥላምን ተቀበለ።
ከዚህ ቂሳ ምን ተማራችሁ?