*/

*/

Source

በአካባቢ ላይ የድምፅ ብክለት ያደረሱ 11 መጠጥ ቤቶች እና ሬስቶራንቶች ታሽጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በአካባቢ ላይ የድምፅ ብክለት እያደረሱ ያሉ 11 መጠጥ ቤቶች እና ሬስቶራንቶች መታሸጋቸው ተገለጸ፡፡

ከ100 በላይ መጠጥ ቤቶች ላይ የአካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን የአካባቢ ብክለት ቁጥጥር ባለሙያዎች ባደረጉት የድምፅ ልኬት አካባቢ እና ህብረተሰቡን የሚያውክ ድምጽ ማውጣታቸው በመረጋገጡ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው እንደቆዩ ተገልጿል፡፡

ሆኖም አብዛኛዎቹ መጠጥ ቤቶች ቢያስተካክሉም 11 የሚሆኑት መጠጥ ቤቶች የሚለቁትን የድምጽ መጠን ባለማስተካከላቸው እንዲታሸጉ የአካባቢ ብክለት ኢንስፔክሽን ቡድን መሪ አቶ ሙላቱ ወሰኑ ተናግረዋል፡፡

መጠጥ ቤቶቹ ከተፈቀደው 45 ዴሲቤል የድምፅ መጠን በላይ አልፍው እስከ 85 ዴሲቤል መጠን ሲጠቀሙ መገኝታቸው ተረጋጧል፡፡

በዚህም ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ሊያስተካክሉ ባለመቻላቸው የድምፅ ብክለቱ በህብረተሰቡ ላይ ትልቅ ችግር እየፈጠረ በመሆኑ እና ህግ መከበር ስላለበት እርምጃው እንደተወሰደባቸው ነው አቶ ሙላቱ የተናገሩት፡፡

ከዚራ ባርና ሬስቶራንት፣ ሰለሞን ጀርመን ሀውስ፣ ፋልከን ላውንጂ፣ ሴራኒ ባርና ሬስቶራንት፣ አዲናስ ባርና ሬስቶራንት፣ ዊንክ ላውንጂ፣ ፉድ ዞን፣ ኤልቢስ ትሮ ባርና ሬስቶራንት፣ ሚሚስ አዲስ ባርና ሬስቶራንት፣ ሮያል ባርና ሬስቶራንት እንዲሁም ተክለሃይማኖት ግሮሰሪ ታሽገዋል፡፡

በቀጣይም በአካባቢ ላይ ብክለት የሚያደርሱ ኢንዱስትሪዎች፣ ፋብሪካዎች፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት መጠጥ ቤቶች እና ሬስቶራንቶች ላይ ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት እርምጃ የሚወሰድ ሲሆን ህብረተሰቡም አካባቢ ላይ ብክለት የሚያደርሱ ተቋማትን በ6317 የስልክ መስመር ላይ ጥቆማ ማድረስ እንደሚችሉ አቶ ሙላቱ መናገራቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Report Page