*/

*/

Source

ለዶክተር አህማድሬዛ ጃላሊ ከሌላው ጊዜ የተለየ አልነበረም፤ ያው የተለመደው የሥራ ጉዞ። በታቀደውም መሰረት ሁለት ሳምንት በኢራኗ መዲና ቴህራን ቆይቶ ወደ መኖሪያው ስዊድን መመለስ ነበር። ነገር ግን ሳይመለስ አሁን አራት ዓመት ተቆጠረ። እንደወጣም ቀረ፤ በኢራን ለእስር መዳረግ ብቻ ሳይሆን የሞት ፍርድም ተፈርዶበታል። የመጨረሻ ስንብት ባለማድረጓ ባለቤቱ ቪዳ ሜህራን ኒያ፤ ፀፀቱ የእግር እሳት ሆኖባታል። የተፈጥሮ አደጋና፣ ድንገተኛ ህመሞች መድኃኒት ባለሙያና ተመራማሪ የሆነው ዶክተር አህማድሬዛ ጃላሊ በየጊዜው ኢራን እየተመላለሰ ጉባኤዎችንና ትምህርቶችንም ይሰጥ ነበር። ከአራት አመት በፊት ባለቤቱን ከሁለት ሳምንት በኋላ እንገናኛለን ብሎ ነበር ለተለመደ ሙያዊ ተግባሩ ወደ ኢራን ያቀናው። እዚያ እንደደረሰም በስልክ አውርተዋል። "ሁለት ሳምንትም ቢሆን መለያየት ቀላል አይደለም" ትላለች ባለቤቱ ቪዳ ከቢቢሲ ጋር ባደረገችው ቆይታ። ልጇ አባቱ በኢራን እስረኛ እንደሆነ ስለማያውቅ በተቻለ መጠን ያንን ጉዳይ የሚመለከት ነገር እሱ ፊት አታነሳም። አባቱ አሁንም ለሥራ እንደሄደ ነው የሚያስበው።

የስዊድና የኢራን ጥምር ዜግነት ያለው ዶክተር አህማድሬዛ ጃላሊ በኢራ

Sunday at 8:59 PM · Public · in

Report Page