*/

*/

Source

“አስክሬን ማየት በጣም ቀላል ሊሆን ይችላል፤ እኔም አይቸዋለው፡፡ ከዚህ በፊት የአንድ አመት ልጄን ቀብሬያለሁ፤ አልከበደኝም ፡፡ ማይካድራ ላይ ግን መቆም አይቻልም፤ ያዩትን ሁሉ መመስከርም አይቻልም፤ ስሜቱ በጣም ከባድ ነው፡፡ ያንን ተቋቁመን ባንዘግበው፤ ቦታው ላይም ባንቆም ኖሮ ወንጀሉ ተዳፍኖ ይቀር ነበር” - ጋዜጠኛ ወንድአጥር መኮንን
*************************
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 80ኛ አመት የምስረታ በአሉን አመቱን ሙሉ በተለያቱ መድረኮች እያከበረ ይገኛል። የበአሉ አካል በማድረግም በህግ ማስከበር ዘመቻው ላይ ለተሳተፉ የመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች የምስጋና እና የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በዚሁ መርሀ ግብር ላይም ወደ ግንባር ከተላኩ ጋዜጠኞች መካከል የማይካድራውን ጭፍጨፋ በስፍራው ተገኝቶ የዘገበው የአማራ መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኛ ወንድአጥር መኮንን የተመለከተውን ለእለቱ ታዳሚያን አጋርቷል።

አስክሬን ማየት በጣም ቀላል ሊሆን ይችላል፤ እኔም አይቸዋለው፡፡ ከዚህ በፊት የአንድ አመት ልጄን ቀብሬያለሁ፤ አልከበደኝም ፡፡ ማይካድራ ላይ ግን መቆም አይቻልም፤ ያዩትን ሁሉ መመስከርም አይቻልም፤ ስሜቱ በጣም ከባድ ነው፡፡ ያንን ተቋቁመን ባንዘግበው ቦታውም ላይ ባንቆም ኖሮ ወንጀሉ ተዳፍኖ ይቀር ነበር” ሲል ነው ጋዜጠኛ ወንድአጥር ምልከታውን ያጋራው።

የተመለከትኳቸው ነገሮች የሚያሙ ናቸው፤ እነዚህ ህመሞች እኛን አመው ባይቆሙ ኖሮ ኢትዮጵያም ኢትዮጵያ ሆና አትቀጥልም ነበር፤ እውነት ለመናገር የማይካድራ ህዝብ ህመሙን ባይችለው ኖሮ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሆና አትቀጥልም ነበር፡፡

ጋዜጠኛ ወንድአጥር በእለቱ በሰጠው የአይን ምስክርነት ላይም ያነሳቸው ዋና ዋና ጉዳዮች እንደሚከተለው ቀርበዋል፤

👉በማይካድራ ላይ የሞተው በዋናነት አማራ ይሁን እንጂ ኦሮሞም ሞቷል፤
ወላይታም ሞቷል፤ ሶማሌም ሞቷል፤

👉ትህነግ ለማንኛውም ነገር እንደማይመለስ የስለት ጫፍ ድረስ ከመጨከን
ወደኋላ እንደማይል ያሳየበት ቦታ ማይካድራ ነው፤

👉የትህነግ ጥላቻ ከ1968 ማኔፌስቶውም በፊት ነው፤ ማንፌስቶው እኮ
የአስተሳሰቡ ውጤት ነው፤

👉የትህነግ የማይካድራ ጭካኔና ጭፍጨፋ በፊት ከመጋረጃ ጀርባ እንደሚፈጸም በሀሜት ደረጃ ይሰማ የነበረው አሁን መጋረጃው የተገለጠበት ሰይጣንም

ያፈረበት ስራው ነው፤

👉የጁንታው ውሸት አስገራሚ ነበር፤ እኔ ሁመራ ሆኜ ዘገባ እየሰራሁ፤ በሬዲዮ የሰማሁት የእነሱ ዜና ሁመራን ተቆጣጥረናል የሚል ነው፤ ደነገጥኩ የት ነው ያለሁት እኔ ነኝ ወይንስ ሁመራ ነው ወደሌላ ቦታ የሄደው እስክል ድረስ

ተገረምኩ፤

👉እነሱ ቢዋሹም አይናቸውና እጃቸው አይዋሽም ነበር፤ በሚዲያዎቻቸው
እየቀረቡ ሲዋሹ ሁሉም ነገር ያስታውቅባቸው ነበር፤

👉የትህነግ ሀይል ገኖ ነበር የመጣው፤ በተለይ እኔ በነበርኩበት አብድራፊ በኩል አብድራፊን ተቆጣጥሮ ወደ ጎንደር፤ ሶሮቃን በዳንሻ በኩል ተቆጣጥሮ ወደ ጎንደር፤ በራያ በኩል ወደ ወልዲያ የመሄድ እቅድ ነበረው፤ 23ኛው ክፍለ ጦር

ተበትኖ ስለነበረ ምንም አያስቀረውም ነበር።

👉ነገር ግን የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ዝግጁ ስለነበረና የኮንትሮባንድ ስራን ሲቆጣጠሩ በነበሩ ከተፈጸመባቸው ጥቃት ያመለጡ የፌዴራል ፖሊስ አባላትም

ባደረጉት ተጋድሎና ጀግንነት ትህነግ ሊቆም ችሏል፤

👉ከፊት ለፊት በመሳሪያ ከጎናቸው በጓደኞቻቸው አስከሬን ሽታ ተፈትነው ድል
ነስተዋል፤ ይሄንን ድል ያደረጉት በኢትዮጵያ ፍቅር ነው፤ በኢትዮጵጽያዊነት ነው፤

👉የአማራ ልዩ ሀይል ወደማይካድረ ከመሄዱ በፊት ሁለት የግዴታ አማራጮች ነበሩት፤ አንደኛው ያለውን ስንቅና ጥይት ለተበተኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት እያጋራ መዝለቅ፤ የተማረከውን ሀይል ደግሞ ለመከላከያ እየሰጠ መሄድ

ነበረበት፤ ይሄንን አደረገ፤

👉ሁለተኛው አማራ ልዩ ኃይል ሌላኛው ጫና እነማይካድራን ማስለቀቅ፣ የሉግዲ መሿለኪያን ማስለቀቅ ወደ ሱዳን የሚሄደውን የትህነግ ኃይል የሚሾልከበትን በር መዝጋትና የሁመራን ቦታ መቆጣጠር ብቻ ሳይሆን የተከበቡ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ከጓደኞቻቸው የአስክሬን ሽታ፣ ከተከበቡበትም ሕይወታቸውን

ማትረፍ ግዴታው ነበረ፤ ሀላዊና በረከት ላይ ይህንን አደረገ፤

👉ወደ ማይካድራ ስንደርስ ደም ፈሷል፤ ሁሉም አዝኗል፤ ሁሉም ይተኩሳል፤ ከመኪና ስንወርድ ሁሉም በእኛ ተቆጥቷል፤ ምክንያቱም እኛ ድሉን ስናበስር

ነው የቆየነው፤

👉እዛ ቦታ ላይ ደም ፈሷል፤ የራሳችንን ወገን ደም ረግጠናል፤ እዛ ቦታ ላይ በወደቀ የአስክሬን ብዛት መካከል መቆም ምናልባትም ትንፋሽን መቁጠር እስከሚያክል

ድረስ የምንተነፍሰው አየር ያስጨንቀን ነበር፤

👉በእንደዚህ አይነት አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ትንፋሽ ቅንጦት ነው፣ የልብ ምት ቅንጦት፤ ሁሉም ጭንቅላታቸው ተከፍቷል፤ ሁሉም ሆዳቸው ተከፍቷል፤ ሁሉም ደምተዋል፤ ሁሉም ወድቀዋል፤ አልጋ ያገኙት በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ በእነዚህ

መሃል መቆም በጣም ከባድ ነበር፤

👉በጋራ ሆነን ይህንን ነገር ለዓለም ማሳወቅ ነበረብን፤ ይህንን ዘግተነው ካለፍን አደገኛ ነበረ፤ መበርታት ነበረብን፣ ደም ረግጠን ነው የቆምነው፤ ሁላችንም

ደም ረግጠናል፡፡

👉ይህንን ለቅሶ እዛ አላለቀስኩትም፣ ሰላም ስለሆነ ነው፤ ማልቀስም ሰላም
በሆነበት ቦታ ነው የሚቻለው፣

👉ህዝብን አነጋገርን ወስደው እንደ ቀበሯቸው ነገሩን፤ ነገር ግን የተገደሉት እነዚህ
ብቻ አይደሉም አሉን፤

👉ከቢሮ መቀሌ ትገባላችሁ የሚል ትዕዛዝ ተሰጥቶናል፤ መቀሌ መግባት ለእኛ መዝናናት ነበር፤ ስለሆነም በየቦታው የተደፉ ሰዎችን ማሳየት ነበረብን፤ አሞራና

ዝንብ እየተከተለን በየቦታው የወደቁ አስከሬኖችን አሳየን፤

👉 ዓለም የትህነግን መጥፎነት ያየው ያን ቀን ነበር፤ ምክንያቱም በፕሮፓጋንዳ
ተሸፍኖ ነበረ፤ እኛ ገለጥነው፤

👉 ከአከባቢው ሰው ጋር ተባብረን በመጀመሪያው ቀን የ74 ሰዎችን አስከሬ አገኘን፤ 74ቱም ስዎች በጋራ ነው የተቀበሩት፤ የህጻናት ጫማ ነበረ፣ የሴቶች

ነጠላ ነበረ፤

👉 አቡነ አረጋዊ በሚባለው ቦታ ላይ የተቀበሩት ሰዎች ቁጥራቸው አይታወቅም፤ በጣም የሚገርመው አስክሬኖቹን መቅበር የማይቻልበት ጊዜ ነው የተደረሰው፤

የአካባቢው ሰው የአስከሬኑን ሽታ ለመቋቋም ሲል ሽቶ ተጠቅመዋል፤

👉 ከሁለት ቀናት በኋላ ተመሳሳይ ጥቆማ ደረሰን፤ አሞራ አከባቢውን ይዞራል፤ ዝንቦች ወረውታል፤ 18 የደረቀ አስክሬን አንድ ላይ ሳይቀበሩ አገኘን፤ እንዲሁ

ነው የተደፉት፤

👉 እስከ መቼ ነው በዚህ ሁኔታ የምንቀጥለው አሁን ያለን አማራጭ ኢትዮጵያ
የሁላችንም ድምቀት መሆን አለባት፤ የሁላችንም ጌጥ ነው መሆን ያለባት፤

👉 ኢትዮጵያን ተጭኖ የተለያዩ ብሔሮችን ዘር እየለየ የሚያጭድ የተንኮል ገበሬ
ካለና እሱ ካልፀዳ ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያ መሆን አይችልም፤

👉 እያንዳንዱ ወታደር የተዋጋው በሸተተ ጓደኛው አስክሬ ጎን ሆኖ ነው፤ እዚህ ቦታ ላይ መቆም አስክሬን ማየት በጣም ቀላል ሊሆን ይችላል፤ እኔም አይቻለሁ ከዚህ በፊት ልጄን ቀብሬያለው፤ አልከበደኝም፤ ማይካድራ ላይ ግን

መቆም አይቻልም፤ ይሀንን መመስከር አይቻልም፤

👉 ሰው ካልሆንን ኢትዮጵያዊ መሆን አይቻልም፤ እነዛ ሰዎች ሰውነታቸው
ስለካዳቸው ነው ኢትዮጵያዊ መሆን ያልቻሉት፤

👉 ከዚህ በኋላ በዚህ ሁኔታ ውስጥ የመጨረሻውን የተንኮል ስለት የያዘው አካል በመከላከያ ሰራዊት፣ በልዩ ኃይል አባላት፣ በአፋር ልዩ ኃይል አባላት፣ በሁሉም

ኢትዮጵያዊ ደጀንነት ተሰናብቷል፤

ለትክክለኛና ወቅታዊ መረጃ ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ!

Report Page