*/

*/

Source

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣሕለወርቅ ዘውዴ በ15ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ክብረ በዓል የማጠቃለያ መርኃ ግብር ላይ ያስተላለፉት መልእክት
*******************

-የሀገራችንን ደህንነት፣ ሉዓላዊነት እና የሕዝባችንን አንድነት አደጋ ላይ ለመጣል የኢትዮጵያ የሁል ጊዜ መከታ በሆነው የመከላከያ ሠራዊታችን የሰሜን እዝ ላይ የተከፈተውን ጥቃት ለመቀልበስ እና ሀገርን ለማዳን በተሰጠው በሳል የጦር አመራር፣ ጥበብ እና ጥንቃቄ እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊታችን ላሳየው ወደር የለሽ ጀግንነት የላቀ ምስጋና እና ክብር ለማቅረብ እወዳለሁ።

-በተለይም በንፁሃን ዜጎቻን ላይ ጉዳት እንዳይደርስ በመጠንቀቅ አስደናቂ ገድል ለፈፀሙት ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ አለን ብለዋል

-መንግሥት የሀገሪቱን ክብር እና የፌዴራል ሥርዓቱን ለማስጠበቅ የወሰደው እርምጃ በስኬት እንዲጠናቀቅ ማንኛውም ልዩነት ሳያግደው በኢትዮጵያዊነት ስሜት እና በአባቶቻችን ወኔ በአንድነት በመቆም በሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ሁለንትናዊ ድጋፍ ላበረከተው ለኩሩው ሕዝባችን ታላቅ ክብር እና ምስጋና አቀርባለሁ።

-በጥፋት እና ከሃዲ ኃይሉ ሀገር የማፍረስ እና ማንነት ተኮር ጥቃት ምክንያት በተለያዩ ጊዜያት በሀገራችን በልዩ ልዩ አካባቢዎች ክቡር የሆነውን ሕወታቸውን ላጡ ንፁሃን ዜጎች፣ በሰሜን እዝ የጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ላይ ጨለማን ተገን በማድረግ በተፈፀመው ክህደት እና ጭፍጨፋ፣ በማይካድራ በርካታ ንፁሃን ዜጎች ላይ በተፈፀመው ዘግናኝ እና ኢ-ሰብአዊ የጅምላ ጭፍጨፋ ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶኛል። ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመለያው የሀገራችን ሕዝቦች መፅናናትን እመኛለሁ።

-በራሳቸው ሕይወት ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ሳያስፈራቸው ወገኖቻቸውን ለማዳን በመደበቅ እና በመደገፍ ጀብዱ ለሠሩ ዜጎቻችን ከፍተኛ ምስጋና እና ክብር በያላችሁበት ይድረሳችሁ!

-እነዚህ ወገኖች ያልተዘመረላቸው፣ ብርሃን ያልበራላቸው በርካታ አኩሪ ዜጎቻችን መካከል ናቸው! የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው፣ በሕክምና ላሉ ምሕረቱን እመኛለሁ።

-በተከፈተብን ጥቃት መሠረታዊ ፍላጎታቸው ለተጓደለባቸው ችግር ላይ ለወደቁ ወገኖች አስባለሁ፤ የሰብአዊ ድጋፍ መሰጠት በመጀመሩ ሁኔታቸው በአስቸኳይ እንደሚሻሻል እርግጠኛ ነኝ።

-ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን የሀገርም ሆነ የመንግሥት ታሪክ ያላት፣ ከራሷ አልፎ ለተቀረው ዓለም የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ያበረከተች፣ በልጆቿ የተገነቡ አስደናቂ ቅርሶች ያሏት ታላቅ ሀገር ናት።

-በዓለም አቀፍ እና አሁጉራዊ ደረጃ የተቋቋሙት ተቋሞች በልጆቿ ትጋት እና በመሪዎቿ አርቆ አሳቢነት መሥራች ሀገር ናት።

-የዚያኑ ያህል እንደ ሀገር የቆምንባቸውን ምሶሶዎችን ሳይቀር ገዝግዘው የሚጥሉ ክፉ አጋጣሚዎችን እኛው በራሳችን ፈጥረናል።

-አንዳችን በአንዳችን ላይ ግፍ ፈፅመናል፣ ንብረትን አውድመናል፣ ዜጎቻችን በገዛ ሀገራቸው እንዲፈናቀሉ አድርገናል፤ እንዲፈሩ፣ እንዲሸማቀቁ፣ እንዲሰጉ ሆነዋል።

-እኛ ኢትዮጵያውያን መጥፎ የሚባሉ የታሪክ አጋጣሚዎች አልፈናል፣ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፈናል። ይህ ሊሆን የቻለው ከብዙ ኪሳራ፣ እልቂት፣ ደም መፋሰስ በኋላ መሆኑን አንዘንጋ።

-ባለፉት ሳምንታት ከሃዲዎች በፈፀሙት ጥቃት የፈሰሰው ደም የኢትዮጵያውያን ደም ነው።

-መሠረታዊው ጥያቄ ችግር በገጠመን ጊዜ "እንዴት ለዚህ ደረስን?" ብለን ቆም ብለን አለመገንዘባችን እና ከሁኔታው አለመማራችን ነው። ይህ ደግሞ እያደር ዋጋ እያስከፈለን ይገኛል።

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

በምስል የሚገኙ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የኢንስታግራም ገፃችንን ይከተሉ

Report Page