*/

*/

Source

ኢትዮጵያዊው በእቃ መጫኛ አዉሮፕላን ( ካርጎ ) ውስጥ ተደብቆ ስቶክሆልም ገባ ።
--------------------

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የእቃ ማመላለሻ አዉሮፕላን ዉስጥ ተደብቆ ለስምንት ሰዓታት የተጓዘ አንድ ኢትዮጵያዊ ትናንት ስቶኮልም አየር ማረፍያ መያዙን ፖሊስ ገለፀ።

ግለሰቡ ስዊድን ዉስጥ ጥገኝነት መጠየቁም ተመልክቶአል። በስቶክሆልም አየር ማረፍያ ሰራተኛ ኦፊሰር ስቴፈን ፋርዲግስ ከድንበር ጠባቂ ፖሊስ ጋር በሰጡት መግለጫ የ24 ዓመቱ ግለሰብን ያገኙት አርብ ዕለት ማለዳ ከደረሰዉ የኢትዮጵያ አዉሮፕላን እቃ ሲያወርዱ የነበሩ ሻንጣ ተሸካሚዎች ናቸዉ።

ሻንጣ ተሸካሚዎቹ ግለሰቡን እንዳላዩ ለፖሊስ አሳዉቀዋል፤ ድንገተኛ ሕክምና መስጫ መኪናን ጠርተዋል።

ኢትዮጵያዊ እንደሆነ የተገለፀዉ ግለሰብ በጥሩ የጤና ላይ እንደሚገኝና ከአዲስ አበባ በቦሌ አየር ማረፍያ ተሸሽጎ መግባቱን በአስተርጓሚ መናገሩ ተዘግቦአል። የቦሌ አየር ማረፍያ ሰራተኛ መሆኑን የሚገልፅ መታወቅያውን የያዘው ግለሰብ በፈጠረለት አመቺ ሁኔታ ተጠቅሞ ፤ ወደ አዉሮፕላኑ በቀላሉ መግባት መቻሉን ገልፀዋል።

Report Page