*/

*/

Source

“የህወሓት ቡድን የፈጸመውን ክህደት ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ያሳዩት ድጋፍ በሉዓላዊነታቸው ላይ መቼም እንደማይደራደሩ ያስመሰከሩበት ነው”

- የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም
*******************
(ኢ.ፕ.ድ)

ከሀዲው የህወሓት ቡድን በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ክህደት ተከትሎ የፌዴራል መንግስት የወሰደው ህግ የማስከበር እርምጃና ኢትዮጵያውያን ከጫፍ ጫፍ በመነቃነቅ ያሳዩት ድጋፍ በሉዓላዊነታቸው ላይ ለሚመጣ ማንኛውም ጉዳይ መቼም እንደማይደራደሩ ያስመሰከሩበት ነው ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም አስታወቁ።

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከህዳር 25 እስከ 26 ቀን 2013 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የተወያየባቸው አጀንዳዎች እና ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች ዙሪያ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ብናልፍ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ ከሀዲው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ የጠነሰሰውን ሴራ ተግባራዊ ለማድረግ በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመሰንዘር የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የማፍረስ ተልዕኮ ለመፈጸም ተንቀሳቅሷል፡፡

ከሀዲው የህወሓት ቡድን በአገር መከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ክህደት ተከትሎ የፌዴራል መንግስት የወሰደው
ህግ የማስከበር ዘመቻ እና ህዝቡ ከጫፍ እስከ ጫፍ በመውጣት ያሳየው መነቃነቅ የሀገሪቷ ሉዓላዊነት እንዲጠበቅ፤ የአገር መከላከያ ሰራዊት አገር ከመፈራረስ እንዲድን፤ ኢትዮጵያዊነትም ጎልቶ እንዲወጣ ማድረግ አስችሏል።

ይህ ህግ የማስከበር ዘመቻም ኢትዮጵያዊነት አሸንፎ የወጣበት ዘመቻ ነው ብለዋል፡፡

ስራ አስፈጻሚው ከህዳር 25 እስከ 26 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው፤ በወቅታዊው የሀገሪቱ ሁኔታና የቀጣይ አቅጣጫዎች፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ ቅራኔዎችና የዓለም አቀፍ የሀይሎች አሰላለፍ እንዲሁም የብልጽግና ፓርቲ ለ2013 ዓ.ም ምርጫ የሚጠቀምበት ማንፌስቶ ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ ማስተላለፉን አቶ ብናልፍ ገልጸዋል፡፡

በመላኩ ኤሮሴ

Report Page