*/

*/

Source

ባለፉት ሁለት ዓመታት በተለያዩ የህግ ማዕቀፎች ላይ ማሻሻያዎች መደረጋቸው ተገለፀ
************************ (ኢ ፕ ድ)

ባለፉት ሁለት አመታት በተካሄደዉ የህግ ሪፎርም በተለያዩ የህግ ማዕቀፎች ላይ ማሻሻያዎች መደረጋቸው ተገለፀ፡፡

ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የህግና ፍትህ አማካሪ ጉባኤ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣የፍሬድሪክ ኢበርት በጋራ ያዘጋጁት መድረክ የህግና ፍትህ ማሻሻያ ጉባኤ አባላት እና ምሁራን እንዲሁም የህግ ተማሪዎች በተገኙበት እየተካሄደ ነው፡፡

በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ባሉ የህግ ማሻሻያዎች ዉስጥ ከነፃነቶችና መብቶች አጠባበቆች ጋር የተያያዙ ተሞክሮዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገው መድረኩ፤ እ.ኤ.አ ከ2016 ጀምሮ እየታተመ ለሚገኘው የህግ ጆርናል የተፃፉ የጥናት ጽሁፎች ደረጃቸውን የጠበቁ ጽሁፎች ለአንባቢያን እንዲቀርቡ ያለመ ነው፡፡

በተካሄደዉ የህግ ሪፎርም ላይ የንግድ ህግ፣ የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ህግና እና የማስረጃ ህግን ጨምሮ ሌሎች በርካታ አዋጆች መሻሻላቸውም ተገልጻዋል፡፡
በመድረኩ ባለፉት ሁለት አመታት ዉስጥ የተሻሻሉ ህጎችን አስመልክቶ የተፃፉ ፅሁፎች ቀርበዋል፡፡ ከእነዚህም የጥላቻ ንግግር ምንነት፣ የሚዲያ ህግ፣ መረጃ የማግኘት መብት እና ሌሎች ከሰብዓዊ መብት ጋር የተያያዙ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ፅሁፎች ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የጉባኤዉ ተሳታፊዎች በበኩላቸዉ አማካሪ ጉባኤዉ በሚሻሻሉና በሚረቁ ህጎች ዙሪያ እያካሄደ ያለዉ ስራ የሚበረታታ መሆን ገልጸው በቀጣይ ግን ህጎችና አዋጆች ከረቀቁ በኋላ አተገባበራቸዉ ላይ ዳሰሳ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ በሚወጡ ደንብና መመሪያዎች ዙሪያ ጉባኤዉ ያለዉ ሚና በግለፅ መታወቅ ይገባዋል ሲሉ ሀሳብ አስተያየታቸዉን መግለጻቸውን ከጠቅላ አቃቤ ህግ የተገኘው መረጃ ያሣያል፡፡

Report Page