*/

*/

Source

ትግራይን መልሶ የመገንባት ሥራ በድኅረ ዘመቻው የመንግሥት ዋና ተግባር ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

*****************

ትግራይን መልሶ የመገንባት ሥራ በድኅረ ዘመቻው የመንግሥት ዋና ተግባር መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ፡፡ "ትግራይን መልሶ የመገንባቱ ሥራ የድኅረ ዘመቻ ዋናው ተግባራችን ነው። ይህ ተግባር ሦስት መልኮች አሉት። ሰብአዊና ማኅበራዊ ድጋፍ፣ የተጎዳውን መሠረተ ልማት መልሶ መገንባት እና መሠረታዊ አገልግሎቶችን መልሶ ማስጀመር። እነዚህ ሥራዎች በስፍራው በተገኙ ቡድኖች አማካኝነት ተጀምረዋል" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት አስተያየት። "የሰብአዊ ድጋፍ አገልግሎትም እጅግ ተጋላጭ የሆኑትን የማኅበረሰብ ክፍሎች በመደገፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል። አንድ ሆነን የተቋረጠውን እናስቀጥላለን፣ የፈረሰውን እንገነባለን፣ የነገውንም እናለማለን" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

በፎቶ የሚቀርቡ መረጀዎችን ለማግኘት ኢንስታግራም ገጻችንን ይጎብኙ

2 hours ago · Public · in

Report Page