*/

*/

Source

የማንም ዘር፥ ብሄር፥ ቀለም ከማንም አይበልጥም።
🌏🇩🇪️🇩🇲️🇪🇹️🇬🇲️🇬🇧️🇪🇺️🇺🇲️🇾🇪️🇹🇱️🇹🇹️🇷🇴️🇲🇷️🇲🇻️🌏 ለስራ ቻይና አገር ሄጄ አውቃለሁ። ታዲያ አንድ ቀን ከቻይናዊ ጓደኛዬ ጋር በስራ መውጫ ሰአት ከተማ ጎዳና ላይ ስንጓዝ ድንገት መንገዱ በሰዎች ተሞላ። ከጓደኛዬ ከ ዮንግ ጋር እያወራን ነበር የምንጓዘውና ድንገት ድምፁ ጠፋብኝ። ዞር ዞር ብዬ ብፈልገው ዙሪያዬ አጣሁት። እየተዟዟርኩኝ መፈለግ ጀመርኩኝ እንደት ላግኘው?! ሁሉም የከበቡኝ ወጣት መንገደኞች በመልክም ሆነ ቁመት ዮንግ ይመስላሉ። እርሱም ነቅቶብኝ ስለነበረ በአንዱ መንገደኛ ተከልሎ ጎኔው ይሄዳል። አፈለለጌ የምር መሆኑን ሲረዳ ብቅ ብሎ ታየኝ። እግዚኣብሄርን ሁሌ ከምጠይቀው ጥያቄዎች አንዱ የሰው ልጅን ስትፈጥር ለምን በቀለም፥ በዘር፥ በብሄር፥ በጎሳ ፥በባህል ፈጠርክ የሚል ነበር እና ለግሌ በዚህ ክስተት መልስ አገኘሁበት። እግዚኣብሄር ቻይና ብቻ ( ፈረንጅ ብቻ) (ህንድ ብቻ) ( ጥቁር አፍሪካዊ ብች) ፈጥሮ ምድርን ሞልቷት ቢሆን ኖሮ ምድር የቱን ያህል እንደምታስጠላ አሰብኩኝ። እንግዲህ ልዩነት (Diversity) የእግዚኣብሄር ሃሳብ ነበር። ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩትም ብዙ አይነት የእፅዋት እና እንስ ሳት ዝርያዎች እንዳሉ ያመለክታሉ። ከሁሉ የሚገረኝ የክ ዋክብቶች ዝርያ፣ የፕላነቶች ዝርያ እና የጋላክሲዎች ዝርያዎች ናቸው። ህዋ በ (Diversity) የተሞላ ነው። እግዚኣብሄር ሲፈጥረን ተመሳሳይ ሮቦቶች አድርጎ አይደለም። ሴት እና ወንድ ሆነን መፈጠራችንም ልዩነታችንን ያሳያል። ልዩነት የሰው ልጆች አንዱ አካል ነው። መፅሃፍ ቅዱሳችን በየዮሐንስ ራእይ 7:9 ላይ “ከዚህ በኋላ አየሁ፥ እነሆም፥ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ” ተብሎ ተፅፎልናል። በየዮሐንስ ራእይ 5:9 ላይ “ መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ” ተብሎ ተፅፎልናል። እንግዲህ እግዚኣብሄር በልዩነቶቻችን (Diversity) ደስ ይለዋል። እኛም የተፈጠርነው በእርሱ አምሳል ለክብሩ ነውና (ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል። ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:16)። እያንዳንዳችንን ውብ አድርጎ ፈጥሮናል። (መዝሙረ ዳዊት 139: 13-16):: የማንም ዘር፥ ብሄር፥ ቀለም ከማንም አይበልጥም። ነገር ግን አሁን ባለንበት ዘመን ልዩነቶቻችን ጣኦት እየሆኑብን መጥተዋል። ልዩነቶቻችን ፈጣሪ የሆነውን እግዚኣብሄርን ትተን ልዩነቶቻችን ካጎላን ያኔ ችግር ይፈጠራል። እግዚኣብሄር ስለ ህብረታችን የሚገደው አምላክ ነው። ወደ ገላትያ ሰዎች 3:28 “አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።” በማለት ህብረታችን ይገልፃል። ልዩነቶቻችን ውበት ነውና ተከባብረን፥ተፋቅረን ፥ አድንቀን አምላካችንን እግዚኣብሄርን እያመሰገንን አብረን እንኑር። እግዚኣብሄር ለሁላችን ማስተዋልን ይስጠን።

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖


ጥላዬ ታደሰ( የህዋ አየር ንብረት ተመራማሪ)

Report Page