*/

*/

Source

‹‹ጁንታው የህወሓት ቡድን የፈጸመው ተግባር የውጭ ወራሪዎች እንኳን ያልፈጸሙት ነው›› - አርቲስት ደበበ እሸቱ
******************** (ኢ ፕ ድ)

ጁንታው የህወሓት ቡድን በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት የክህደት ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም የሀገሪቱን ህዝቦች ለማንበርከክ የሞከሩ ወራሪዎች እንኳን ያልፈጸሙት ተግባር መሆኑን አርቲስት ደበበ እሸቱ አስታወቀ።

አርቲስት ደበበ እሸቱ ጁንታው የህወሓት ቡድን በመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመውን ትቃት አስመልክቶ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቀው ፤ ከሃዲው ቡድን ለ21 ዓመታት ክልሉንና ህዝቡን ሲጠብቅ በነበረው የመከላከያ ሰራዊት ላይ የፈጸመው ጥቃት የከሃዲነት ተግባር ከመሆኑም ባሻገር ትውልድም ይቅር የማይለው ነው።

‹‹ተስፋ የቆረጠ ሰው ብዙ ነገር ያደርጋል። ተስፋ ባይቆርጥ ኖሮ፣ አብሮት ሲሰራና አብሮት ሲበላ የቆየ ወንድሙን አይገድልም ነበር። መከላከያ ሠራዊቱ ከኋላዬም ከፊቴም ያለው የራሴው ወገን ነው ብሎ ወገኑን ተማምኖ በተኛበት በሌሊት ክህደት መፈጸሙ ቡድኑ የመጨረሻ ዘመኑ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ነው ።

“አርቲስት ደበበ እንደሚለው፤ የህወሓት ቡድን በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ የፈፀመው ክህደትና ጭካኔ የውጭ አገር ጠላትና ወራሪ እንኳን ያላደረገው ነው። ጣሊያን አላደረገውም፣ ደርቡሾች አላደረጉትም፣ እንግሊዞች ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስን ለመያዝ በመጡበት ጊዜ እንዲህ አይነት አፀያፊ ድርጊት አልፈጸሙም። የራሳችን ወገን የተባለው ግን እንዲህ አይነት ዘግናኝ ድርጊት ፈጸመ። የሠራዊቱ አባላት ሲወጣ ‹‹ለማን ጥላችሁን ነው የምትሄዱ፣ እባካችሁ ቆዩልን›› ያለ አካል ይሄን ክህደት መፈጸሙ የግድያ ቀን እያመቻቸ ነበር ማለት ነው።

ሠራዊቱ ይህ ክህደት እንደሚፈጸምበት ቢያውቅ ጥሪውን ሳይቀበል ይወጣ ነበር። የወገን ጥሪ ሆኖበት ግን ቆይልኝ ሲባል እዚያው ቆየ። ወገን በወገኑ ላይ እንዲህ ሲጨክን ቅስም ይሰብራል።ኢትዮጵያዊ መሆኑንም እንድንጠራጠር አድርጎናል ብሏል።

‹‹እንዲህ አይነት የአውሬነት ባህሪ ያላቸው ሰዎች ነበሩ ለካ ሲመሩን የቆዩት›› ያለው አርቲስት ደበበ፤ እነዚህ ሰዎች የፈጸሙት አጸያፊ ተግባርም መላውን ኢትዮጵያዊ ያሳዘነና ያስቆጣ መሆኑንም ጠቁሟል።

እንደ አርቲስት ደበበ አስተያየት፤ ጁንታው የህወሓት ቡድን ሥልጣን ላይ በቆየባቸው ዓመታት ለጥፋት የሚሆኑትን ገንዘብና ሌሎች ነገሮችን ቢያከማችም ሊያዛልቀው ግን አይችልም። አቅም ይሳነዋል። አሁን ላይ ማድረግ የሚችለው የመሰረተ ልማት ውጤቶችን ማውደም ብቻ ነው። ከአዲስ አበባ ጋር ግንኙነቱ ስለተቋረጠ የገንዘብ ምንጩም ይደርቃል። እስከ አሁን ግን ከዚህ በፊት በሰበሰበው ገንዘብ አፈ ቀላጢዎችን ቀጥሮ በውጭ መገናኛ ብዙኃን ብዙ እያስወራ ነው።

Report Page